TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ቅዳሜ የመጨረሻው ገንዘቡን የመመለሻ ቀን ነው " - ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ወይም ወደተለያየ ሂሳቦች ያስተላለፉ ግለሰቦች እስከ መጪው ቅዳሜ መጋቢት 14 ድረስ በፈቃዳቸው እንዲመልሱ አሳስቧል። ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነውም ብሏል። በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተጠቅመው አላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦች ላይ…
የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ምን አለ ?

የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር መጋቢት 6 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ተፈጥሮ የነበረውን የሲስተም ችግር ተገን በማድረግ #ተመዝብሯል ያለውን " የህዝብ ገንዘብ " አስመልክቶ መግለጫ አወጣ።

ማኅበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቴክኖሎጂ ሥርዓት ላይ ችግር በተፈጠረበት ቅፅበት የነበረውን ክፍተት እንዴት እንዳገኙ ለጊዜው ባልተረጋገጠ ሁኔታ መረጃ የደረሳቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ሌሊቱን በሙሉ በመደዋወል ከአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖች (ATM) ገንዘብ በመውሰድና ልዩ ልዩ ገንዘብ መክፈያና ማስተላለፊያ ማዕቀፎችን በመጠቀም የራሳቸው ያልሆነውንና በሂሳባቸው ውስጥ ያልነበረን ገንዘብ " ዘርፈዋል " ብሏል።

ከዚህ ባለፈ ደግሞ ፤ " የተፈጸመውን #ምዝበራ እንደ በጎ ተግባር ሁሉ በሁሉም የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች በጀብድ መልክ ሲዘዋወር መመልከታችን ከፍተኛ ኃዘን አሳድሮብናል " ሲል ገልጿል።

የባንኮች ማህበሩ ፤ " ከማኅበረሰቡ በተሰበሰበ አንጡራ ገንዘብ በመንግሥት ከፍተኛ ወጪ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ወደ ከፍተኛ ተቋማት /ዩኒቨርስቲ/ የተላኩ አፍላ #ወጣቶች ኢትዮጵያዊ ከሆነው ነባር ዕምነት እና ባህል ባፈነገጠ ሥነምግባር ላይ ወድቀው መገኘታቸው ልብ የሚሰብርና አገራችን ካለባት ጊዜያዊ ችግሮች በላይ የሚያሳስብ አሳዛኝ ድርጊት ሁኖ አግኝተነዋል  " ብሏል።

ድርጊቱንና የድርጊቱን ፈጻሚ እና ተባባሪ የሆኑትን አካላት ሁሉ ማኅበሩ በጽኑ #እንደሚያወግዝው ገልጾ ፤ እነዚህን መሠል ወጣቶች በተመሳሳይ ውድቀት ውስጥ እንዳይገኙ ለመከላከል ሁሉም አካላት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ትኩረት ሰጥተው እንዲፈጽሙ ጥሪ አቅርቧል።

በንግድ ባንክ ላይ የተፈጠረው ችግር እና ችግሩን ተገን አድርገው በባንኩ፣ በባንኩ ደንበኞችና በኅብረተሰቡ ላይ ጉዳት ባደረሱ አካላት ላይ እየተደረገ ባለው ሕጋዊ ማጣራት እና በቀጣይነት ወደ ህግ በማቅረብ በቂ ተመጣጣኝና አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ረገድ ፤ ሁሉም አባል ባንኮች አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ጠቁሟል።

ሁሉ አቀፍ ትብብር ለህግና ጉዳዩ ለሚመለከታው ተባባሪ አካላት ለመስጥትም ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia