TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሶማሌክልል በሶማሌ ክልል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ እስካሁን 28 ሰዎች ሲሞቱ ከ300,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተጠቆመ። በሶማሌ ክልል ከ33 ወረዳዎች በላይ ተከሰተ የተባለውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው እርዳታ እያደረገ የሚገኘውን Save the Childrenን ጠይቋል። የድርጅቱ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ…
#ሱማሌ_ክልል

" እስካሁን ከ700 በላይ ሰዎች በኮሌራ ተጠቅተዋል። 23 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። ከ23ቱ ወደ 11 የሚሆኑት #ህፃናት ናቸው " - አቶ አብዲሪዛቅ አህመድ

በሱማሌ ክልል በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ የከፋ ኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን፣ ወረርሽኙን ለመከላከል የመድኃኒት እጥረት ፈተና በመሆኑ ርብርብ ካልተደረገ ከ500,000 በላይ ተፈናቃዮች በወረርሽኙ የመጠቃት ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን ሴቭ ዘ ችልድረን (Save the children) የሱማሌ ክልል ቅርንጫፍ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

የሱማሌ ክልል ሴቭ ዘ ችልድረን ቅርንጫፍ ዳይሬክተር አቶ አብዲሪዛቅ አህመድ ምን አሉ ?

- እስካሁን #ከ700 በላይ ሰዎች በኮሌራ ተጠቅተዋል። 23 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። ከ23ቱ ወደ 11 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው። ከ700ዎቹ ተጠቂዎች መካከል 319ኙ ህፃናት ናቸው።

- በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ምክንያት ብዙ መጸዳጃ ቤቶች ወድመዋል። የተፈናቀሉ ሰዎች መጸዳጃ ቤት የላቸውምና ይሄ ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ሆኗል። ተፈናቃዮቹ የሚኖሩበት ቤት የላቸውም።

ኮሌራ የተከሰተው መቼ ነው ?

- ኮሌራ ከተከሰተ ከሁለት እስከ ሦስት ወራት አስቆጥሯል። ሆኖም ግን ዝናብ መዝነብ ከጀመረ በኋላ ነው ኬዞቹ በጣም እየበዙ የመጡት።

- ሕክምና ካላገኙ #ይሞታሉ። ኮሌራ በጣም መጥፎ ተላላፊ በሽታ ነው። መድኃኒት እንዴት ይገኛል የሚለው ግን አሁንም አጠያያቂ ጥያቄ ነው። 

- በተለይ ቀላፎ ወረዳ መንገዱ ስለተጎዳ አክሰስ የለም፣ የመድኃኒት እጥረት ሲያጋጥም ለማድረስ እንኳ ለትራንስፖርት ያስቸግራል። ተፈናቃናቃዮቹ በጠባብ መጠለያ ውስጥ ከአሥር ሰዎች በላይ ሆነው ተጣበው ነው የሚኖሩት። መጸዳጃ ቤት የላቸውም፣ ኮሌራው የመዛመት ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

በጎርፍ ሳቢያ የተፈናቃዮችና የተጎጂዎች ቁጥር  ጨመረ ወይስ ቀነሰ ?

-የተፈናቃዮች ቁጥር ከ300,000 ወደ #500,000፣ የተጎጂዎች ቁጥር ከ600,000 ወደ #1.4 ሚሊዮን ደርሷል። ካሉበት ቦታ እስከመቼ እንደሚቀመጡ አይታወቅም፣ ምክንያቱም ጎርፉ እስካሁን እንደቀጠለ ነው።

- ከእነዚህ ተጎጂዎች መካከል እስካሁን ድጋፍ ያገኙት #10 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው። ቀሪዎቹ #90 በመቶዎች አፋጣኝ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

- የጎርፍ አደጋው እስካሁን እየተስፋፋ ነው። ብዙዎች እየተጎዱና እየተፈናቀሉ ነው።  ሰሞኑን ዝናቡ ስለቀነሰ ምናልባት ከዚህ በኋላ አደጋው ሊቀንስ ይችላል የሚል ተስፋ አለ።

ምን ተሻለ ?

ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ስላለ ማኅበረሰቡ የሚዛመትበትን መንገድ እንዲያውቅ አዌርነስ እንዲፈጠር፣ መድኃኒትና ነርስ በቂ ስላልሆነ እንዲጨመር፣ ኬዙ ያለባቸው ቦታዎች ኮሌራ ትሪትመንት ሴንተር እንዲገነባ፣ የታመመ ሰው ቶሎ ወደ ሆስፒታል እንዲደርስ የሚያስችል ቲም እንዲቋቋም አቶ አብዲሪዛቅ ጠይቀዋል።

የተከሰተው ኮሌራ ዋና ምንጩ ምን እንደሆነ መለየትና በአፋጣኝ ከምንጩ ማድረቅ ዋነኛው ተግባር መሆን እንዳለበት ጠቁመው፣ ንጹህ የውሃ ችግር ስላለ ተፈናቃዮች የተበከለ ውሃ እንዳይጠቀሙ የውሃ ሳኒታይዘር እንደሚያስፈልግም አክለዋል።

ድጋፍ ካልተገኘ በቀጣዮቹ ሳምንታት ብዙ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ችግሩ ሰፊና የከፋ፣ ከመንግሥት አቅም በላይ ስለሆነ አለም አቀፍ ኤጀንሲዎች ጋር ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ነው።

@tikvahethiopia