TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ግድያ አስመልክቶ በሚቀጥለው ሳምንት መግለጫ ይሰጣል። እንደ ኢዜአ ዘገባ የእስካሁኑ የምርመራ ውጤት በሚቀጥለው ሳምንት ለህዝብ #ይፋ ይደረጋል።

@tsegabwolde @tikahethiopia
#update አዲስ አበባ ጉድሽን ስሚ⬆️

አዲስ አበባ ውስጥ እያካሄደ ባለው የማጣራት ሥራ #ባለቤት የሌላቸውን #ሕንፃዎችና ታጥረው የተቀመጡ #መሬቶችን ማገኘቱን የከተማዋ አስተዳደር አስታውቋል።

ምክትል ከንቲባው ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ቃለ-ምልልስ ባደረጉበት ወቅት ሲናገሩ እስከ ፊታችን አዲስ ዓመት ድረስ የማጣራት ሥራው ተጠናቅቆ ውጤቱ ለሕዝብ #ይፋ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

@tseabwolde @tikvahethiopia
#update

📌የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ገና #አልተወሰነም፡፡
📌የ10ኛ ክፍል ማለፊያ ዉጤት እስከ ዓርብ ጳጉሜን 2/13/2010 ዓ.ም #ይፋ ይደረጋል፡፡

@tsegawolde @tikvahethiopia
የ10ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆኗል⬇️

የሀገር አቅፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የ2010 የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት #ይፋ ሆኗል። በዘንድሮው የአስረኛ ክፍል ፈተና ከሰባት ሽ በላይ ተማሪዎች አራት ነጥብ አምጥተዋል። ከነዚህ ውስጥ 2375ቶቹ ሴቶች ናቸው።

📌ተማሪዎች ዛሬ ከ12:00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

©ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና⬆️የ2011 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ(ዩኒቨርሲቲ) ውጤት ነጥብ #ይፋ ተደርጓል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ወንጀለኞቹን መያዝ ብቻ በቂ አይደለም። ማን እንዳሰማራቸው፤ እንዴት እንደተደራጁ፤ ምን አይነት ውይይት እንዳደረጉ፤ በግልፅ ለህዝብ #ይፋ ይውጣና እንደ ህዝብ እንማርበት።" ሰለሞን ደቻሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦዴፓ እና ኦዴግ ተዋሀዱ‼️

በአቶ #ሌንጮ_ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ODF) ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ODP) ጋር መዋሃዱ እየተነገረ ነው።

ይኸው የሁለቱ ፓርቲዎች ውህደት በዛሬው ዕለት ለህዝብ #ይፋ እንደሚደረግም ተሰምቷል።

የአርትስ ቴሌቪዥን ምንጮች እንደጠቆሙት የሁለቱን ፓርቲዎች ውህደት በተመለከተ የፓርቲዎቹ አመራሮች አቶ ለማ መገርሳ እና አቶ ሌንጮ ለታ ዛሬ ከቀትር በኋላ በኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ቢሮ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መከፋፈል በኋላ የቀድሞ አመራሩ አቶ ሌንጮ ለታ አሁን ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ጋር ሊዋሃድ መሆኑ የተነገረውን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) መስርተው መንቀሳቀስ መጀመራቸው ይታወሳል።

በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወደሃገር ቤት ከገቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀዳሚውም ይኸው የአቶ ሌንጮ ፓርቲ ኦዴግ ነው።

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከመንግስት ጋር በተደረገ ድርድር ትጥቅ ፈትቶ በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ በመወሰን ወደኢትዮጵያ መግባቱም አይዘነጋም።

ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ‼️

ጥር 17 አፄ #ቴዎድሮስ_ግቢ በ6 የተማሪ መኖሪያ ህንፃዎች በተደረገ #ድንገተኛ ፍተሻ፦

•395 ያልታደሰ፣ ሃሰተኛ እና ፎቶ የሌለው መታወቂያ ተይዟል።

•ከተማሪ መኖሪያ ክፍሎች ጩቤ፣ ድንጋይ፣ ብረት እና ዱላ ተገኝቷል።

•አንድ ተማሪ 9 ሲም ካርድ፤ ሌላ አንድ ተማሪ 7 ሲም ካርድ ይዘው ተገኝተዋል።

•8 ተማሪዎች አካውንት ላይ እያንዳንዳቸው ከ30 ሺ ብር እስከ 86 ሺ ብር ተገኝቷል።

•መታወቂያ ያልያዙ 37 ተማሪዎች ተይዘዋል።

•በቀን ጥር 16/2011 ዓ.ም. 3 ተማሪዎች 4 ጀሪካን ዘይት ጫካ ውስጥ ይዘው እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፤ 3 ተማሪዎች ሴቶች ህንፃ ሲገቡ ተይዘዋል።

🔹ተጠርጣሪዎች ላይ ተገቢው ማጣራት እየተደረገ ይገኛል፤ በቅርቡ #እርምጃ ተወስዶ #ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
.
.
ትምህርት የተቋረጠባቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ፋሲል ግቢዎች ከሰኞ ጥር 20 ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። ትምህርት የማይጀምሩ ተማሪዎች ግቢውን #ለቀው እንዲወጡ #ጥብቅ_ማሳሰቢያ ተላልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE የዩኒቨርሲቲ መግቢያ #የመቁረጫ ነጥብ #ይፋ ተደርጓል እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰረጫ ያለው መረጃ ሀሰት ነው። #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር  ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን መቼ ለመስጠት እቅድ ይዟል ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰውና በትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተሰራጨ አንድ ደብዳቤ የዚህ ዓመት የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ሊሰጡ #የታቀደበትን ጊዜ ያመለክታል። የደብዳቤውን ትክክለኝነት ቲክቫህ…
#MoE #ይፋዊ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ #ይፋ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ ፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ #በመንግስት_ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል ብሏል።

ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

@tikvahethiopia