TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም‼️

ትውልዱ ብሔርን መሰረት አድርጎ መፈራረጅና #መጠላላትን እንዳይወርስ መጠንቀቅ እንደሚገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ ወይዘሮ #ኬሪያ_ኢብራሂም አሳሰቡ።

አፈ ጉባዔዋ ይህን ያሉት ዛሬ በምስራቅ ኢትዮጵያ ያሉ ክልሎች የተሳተፉበት በድሬደዋ እየተካሄደ ባለ #የሰላም ኮንፍረንስ ላይ ነው።

ለሁለት ቀናት ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው በኮንፍረንሱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር እንዳሉትም በአገሪቷ ”የእከሌ ብሔር ካንተ በላይ ተጠቃሚ ሆኗል፣ የእከሌ ብሔር የበላይ ሊሆንብህ ነው” የሚሉ ጥላቻ ሰባኪና ጥርጣሬን የሚዘሩ ቃላት ሥር እየሰደዱ ነው።

በዚህ ምክንያትም በብሔር መፈራረጅና ጥላቻ እየሰፋ መጥተዋል ብለዋል።

በዚህም ምክንያት በርካቶች በአሰቃቂ መንገድ እየተገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉ፣ ለፍተው ያካበቱትን ጥሪት እያጡ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ምንጭ ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደሬሽን ምክር ቤት‼️

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ምክንያት የሚከሰቱ ግጭቶችን ለመከላከል የሚያስችል #ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጥ ገለጸ።

ምክር ቤቱ በማንነት ጉዳዮችና የጥያቄዎች አፈታት ላይ የሚያተኩር ስልጠና እየሰጠ ነው።

የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ #ኬሪያ_ኢብራሂም እንደገለጹት፤ የ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ምላሽ አሰጣጥ ውስንነት ነበረው።

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በማንነት ጥያቄዎች ላይ የማይመለከታቸው አካላት እጃቸውን በማስገባት ግጭት እንዲፈጠር እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

”ህገ-መንግስታዊ ስርዓት እንዲሰፍንና የህግ የበላይነት እንዲከበር በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 62 በተሰጠን ስልጣን መሰረት ለጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን” ብለዋል።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት እስካሁን 76 ብሔሮች ዕውቅና ያገኙ መሆኑን የገለጹት ወይዘሮ ኬርያ በቀጣይ የ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ምላሽ እንደሚያገኙ አረጋግጠዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia