TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሰላም ኮንፈረንስ⬆️

ዓለም አቀፍ የሴቶች እና የወጣቶች የሰላም ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ ተካሄደ። በአዲስ አበባ ኢሲኤ አዳራሽ በተደረገው አለም አቀፍ የሴቶችና ወጣቶች የሰላም ኮንፈረንስ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ #ዳግማዊት፣ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ዶ/ር #ነጋሶ_ጊዳዳ፣ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ዳይሬክተር አቶ #ጃዋር_መሃመድ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ስለሰላም የሚያወሳ አጫጭር ጹሁፎችን አቅርበዋል።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሴቶች እና ወጣቶች ለሰላም መረጋገጥ ትልቅ ሚና ሲጫወቱ እንደቆዩና አሁንም የጎላ ሚና እናዳላቸው ገልጸው ወጣቶች ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ቁልፍ ድርሻ እንደሚጫወቱ መንግስት በጽኑ ያምናል ብለዋል። በዝግጅቱ ላይ ከተለያዩ የአገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች የተወከሉ ወጣቶችና ሴቶች መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮችና ሙሁራኖች ተሳትፈዋል።

©የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ፎቶ፦ ወ/ሮ ዳግማዊት እና DAVE
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዜና እረፍት🔝

የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ነጋሶ_ጊዳዳ በ75 አመታቸው ከዚህ አለም #በሞት ተለዩ። ዶ/ር ነጋሶ ለ7 አመታት ያህል ኢትዮጵያን በፕሬዚደንትነት አገልግለዋል። ነብስ ይማር!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia