TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማስታወሻ📌የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ በሰኔ 16ቱ #የሽብር ጥቃት፣ በኢንጅነር #ስመኘው ሞት፣ በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል እና በከባድ ሙስና ወንጅሎች ዙሪያ ዛሬ ጳጉሜ 01 ቀን 2010 ከቀኑ 8:00 በፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስለ ሰኔ 16ቱ ጥቃት ሪፖርተር እና EBC⬇️

በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት በተጠረጠሩ 5 ግለሰቦች ላይ #የሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተ።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች ላይ በሽብር ወንጀል #ክስ መሰረተባቸው።

ጠቅላይ ዓቃቢ ህግ በሽብር ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው ጌቱ ግርማ ፣ብርሃኑ ጁፋር ፣ጥላሁን ጌታቸው ፣ባህሩ ቶላና ደሳለኝ ተስፋዬ ላይ ነው፡፡

ዓቃቢ ህግ ሁሉንም ተከሳሾች ሰኔ 16 በነበረው የድጋፍ ሰልፍ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ላይ ጥቃት ለማድረስ ብሎም በሀገሪቱ እየታየ ያለውን ለውጥ ለማደናቀፍ በጠቅላይ ሚንስትሩ የሚመራ መንግስት መኖር የለበትም የሚል ዓለማ ይዘው እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል።

እንደ ክሱ ገለፃ ከሆነ ይህ ዓለማ ቀድሞ በተደራጀ በኦነግ ስም በሚንቀሳቀሱና የቦንብ ጥቃት ማድረስ በሚችሉ አባላት አማካኝነት መሆን እንዳለበትም የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ ነው።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ተቀባይነት የሌላቸው በተለይም በኦሮሞ ብሔር ዘንድ አንደማይፈለጉ አድርጎ ለማሳየት በሚረዳ መልኩ ጥቃቱን ለመፈፀም ዐቅደው መንቀሳቀሳቸውም በክሱ ተጠቁሟል።

ለዚህ ደግሞ በኬንያ የምትኖር ገነት ታምሩ ወይንም በቅፅል ስም #ቶሎሺ ታምሩ በምትባል የቡድኑ አባል አማካኝነት ተልዕኮ እንደተሰጣቸው በክሱ ተገልጿል።

አንደኛ ተከሳሽ ጌቱ ግርማ ከዚች ሴት ጋር ሰኔ 2010 በስልክ በመገናኘት ' ለጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፍ መካሄድ የለበትም'፣' መሰረታዊ ለውጥ አልመጣም '፣ ' ሰልፉን የጠራው ገለልተኛ ወገን ሳይሆን ኢህአዲግ ነው '፣ ' HR128 የተባለውና በአሜሪካ ኮንግረንስ የተላለፈው ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይሆን ያደርጋል' በሚል ሰልፉ እንዲበተን አድርጉ የሚል ተልኮ እንደተቀበለም ክሱ አመልክቷል።

አንደኛ ተከሳሽ ጌቱ ግርማ ከሁለተኛ ተከሳሽ ብረሃኑ ጁፋር ጋር በሰኔ ሱሉልታ ላይ ስለ ተልኮው በመነጋገር ቦንብ እዲያዘጋጅ፣ ቦንቡን የሚወረውርን እንዲያፈላልግ ተነጋግረው ለሶስተኛ ተከሳሽ ጥላሁን ጌታቸው ደውሎ ቦንብ የሚወረውር ሰው እንዲፈልግ ተልኮ
መስጠቱም ክሱ ያሳያል።

ሁለተኛ ተከሳሽ ያዘጋጀውን ሁለት ኤፍ 1 ቦንብ እንዲሁም አንድ የጭስ ቦንብ በአንደኛ ተከሳሽ ቤት በማስቀመጥ ከሱሉልታ በመነሳት ሰልፉን በመቀላቀል በኛው ተከሳሽ አመካኝነት ቦንቡን በማፈንዳት ሙሳ ጋዲሰና ዬሴፍ አያለው የተበሉ ግለሰቦች ላይ የሞት 165 የሚሆኑ ሰዎች ላይ ከባድ ና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውም በክሱ ተጠቁሟል። በዘህም መሰረት ዓቃቢ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል

ምንጭ፦ EBC

ሪፖርተር፦

ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች #የሽብርተኝነት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት ዓርብ መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ክሱን ያቀረበው ዓቃቤ ሕግ፣ የቦምብ ጥቃቱ የተፈጸመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) #ለመግደል መሆኑን በክሱ አስታውቋል፡፡

በቦምብ ጥቃቱ ክስ የተመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች አቶ ጌቱ ግርማ፣ አቶ ብርሃኑ ጃፋር፣ አቶ ጥላሁን ጌታቸው፣ አቶ ባህሩ ቶሎሳና አቶ ደሳለኝ ተስፋዬ ናቸው፡፡

ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ክስ እንደገለጸው፣ ተከሳሾቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ላይ ግድያ ለመፈጸም ያነሳሳቸው በእሳቸው የሚመራ መንግሥት #መኖር ስለሌለበት ነው፡፡ የአገሪቱ መንግሥት መመራት ያለበት ቀድሞ በተመሠረተው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ነው የሚል ዓላማ ተከሳሾቹ እንዳላቸው ዓቃቤ ሕግ በመሠረተው #ክስ ጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም በማለትም፣ ተጠርጣሪዎቹ ለግድያ መነሳሳታቸውን ዓቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሜሪካ ኮንግረስ የፀደቀውን ኤችአር 128 ለማስፈጸምና በስመ ሕዝበኝነት የራሳቸውን ዓላማ የሚያራምዱ መሆናቸውን፣ በዚህም ምክንያት የኦሮሞን ሕዝብ ፍላጎት ስለማያስፈጽሙ ተጠርጣሪዎቹ ጥቃቱን ለመፈጸም መነሳሳታቸቸውን ዓቃቤ ሕግ
በክሱ አክሏል፡፡

የሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የመስቀል አደባባይ የወንጀል ድርጊት ያቀነባበረችው በኬንያ ናይሮቢ የምትገኝ ገነት ታምሩ (ቶለሺ ታምሩ) የምትባል መሆኗን፣ ዓቃቤ ሕግ በክሱ አመልክቷል፡፡

በመስቀል አደባባይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፍና ምሥጋና በተደረገ ሥነ ሥርዓት ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ሁለት ግለሰቦች ሲሞቱ፣ ከ150 በላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቡራዩና አከባቢው ጥቃት‼️

ከመስከረም 2 እስከ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ በቡራዩ ከተማና አካባቢው በተፈጸመ ግድያ፣ የንብረት ቃጠሎና ዘረፋ ጋር በተያያዘ ታስረው ከነበሩት በርካታ ተጠርጣሪዎች ውስጥ፣ የ38 ግለሰቦች ድርጊት #የሽብር_ወንጀል ድርጊት ነው በመባሉ የ28 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ፡፡

የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ዓርብ ኅዳር 21 ቀን 2011 ዓ.ም. በፀረ ሽብር ሕጉ ድንጋጌ መሠረት 28 ቀናት የምርመራ ጊዜ የፈቀደባቸው ተጠርጣሪዎች፣ በቡራዩ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው ሲታይ የከረመና ፈጽመውታል የተባለው ድርጊት የሽብር ድርጊት መሆኑን በምርመራ የተገኙ ማስረጃዎች አመላካች ሆነው በመገኘታቸው ወደ ፌዴራል ፍርድ ቤት የተዛወሩ ናቸው፡፡ በተጠረጠሩበት የግድያ፣ የንብረት ቃጠሎና ዘረፋ፣ እንዲሁም ከባድና ቀላል የአካል ማጉደል ወንጀል ምርመራ እንደሚቀረው በመግለጽ፣ ፍርድ ቤቱ 28 ቀናት እንዲፈቀድለት የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ጠይቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከሁለት ወራት በላይ በቡራዩ ወረዳ ፍርድ ቤት መታሰራቸውን በመግለጽ፣ መርማሪ ቡድኑ ምርመራውን በማጠናቀቁ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪዎቹን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ፣ ፖሊስ የጠየቀውን 28 ቀናት በመፍቀድ ለታኅሳስ 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍላተ ከተሞች ከመስከረም 5 እስከ 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በተፈጠረ ብጥብጥ ሰው በመግደል፣ አካል በማጉደልና ንብረት በማውደም በተጠረጠሩ 14 ግለሰቦች ላይ ዓቃቤ ሕግ በአሥር ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሠርት ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ላለፉት ሁለት ወራት በ14 ተጠርጣሪዎች ላይ ሲያጣራ የቆየውን የምርመራ ሒደት ማጠናቀቁንና ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማስረከቡን የፌዴራል ፖሊስ በማሳወቁ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ዓቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሠረት አሥር ቀናት ፈቅዷል፡፡

በቡራዩና አካባቢው፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ ክፍላተ ከተሞች በተቀሰቀሰ ረብሻና ብጥብጥ የ30 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
በአዲስ አበባ የተጠራ ሰልፍ የለም‼️

በአዲስ አበባ ከተማ ነገ የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍ አለመኖሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ በነገው እለት በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጭው መረጃ ትክክል አለመሆኑን አስታውቀዋል።

ለነገ ህጋዊ መስመርን ተከትሎ እና ባለቤትነቱን ወስዶ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ ያቀረበ አካል #እንደሌለም አስታውቅዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ አክለውም ብህረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚጠሩ ህጋዊ ባለቤትነት ከሌላቸው ሰልፎች ሊቆጠብ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

ምክንያቱም ይህንን አጋጣሚ እንደ ምቹ ሁኔታ የሚጠቀሙ ኃይሎች በኅብረተሰቡ ላይ #የሽብር ተግባራት ለመፈጸም የሚያስችል እንቅስቃሴ ስለሚኖር ከወዲሁ ይህንን ተገንዝቦ #ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

#በመዲናዋ ያለ ፈቃድ ሠልፍ የሚያካሄዱ አካላትም ኃላፊነት እንዳለባቸው በመረዳት ግን ህጋዊ አሰራሩን መከተል አለባቸው ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ9/11 የሽብር ጥቃት #USA!

ዘጠኝ አስራ አንድ ተብሎ በሚታወቀው የአሜሪካው #የሽብር ጥቃት አቀነባባሪነት የተጠረጠረው ግለሰብ ሳዑዲ አረብያን በተመለከተ ቃሉን ሊሰጥ እንደሆነ ተገለፀ። ከ18 ዓመታት በፊት በሁለቱ የአሜሪካ የንግድ ህንፃዎች ላይ የደረሰውን የሽብር ጥቃት አቀነባብሯል በሚል የሚጠረጠረው እና የአል ቃይዳ ቁልፍ ሰው እንደሆነ የሚነገርለት ካሊድ ሼክህ ሞሃመድ የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት የማይበይንበት ከሆነ በጉዳዩ ዙሪያ ቃሉን እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪው ይህንን አማራጭ ያቀረበው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አርብ ሲሆን በአሜሪካ ማንሃታን ወረዳ ፍርድ ቤት በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ባለሀብቶች እና ግለሰቦች ጠበቆች ባዘጋጁት ደብዳቤ ላይም ፍቃደኝነቱን በመሙላት ማረጋገጡ ነው የተገለፀው፡፡

ግለሰቡ በሳዑዲ አረብያ ላይ ሊመሰክር ቃል ይግባ እንጂ ሀገሪቱ በተደጋጋሚ ጊዜ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት እንደሌላት ስትገልፅ ቆይታለች። ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘው እና የሳዑዲ አረብያ መንግስት ጠበቃ ሚሼል ኬሎጅ ግን በጉዳዩ ላይ ሀሳብ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡ ግለሰቡ ጠበቆቹ ያቀረቡት ደብዳቤ ላይ ሀሳቡን እንዲያሳርፍ የተለያዩ የህግ ባለሙያዎች በታዛቢነት መሳተፋቸውም ተገልጿል፡፡

ካሊድ ሼክ ሞሃመድን ጨምሮ 3 ተጠርጣሪዎች የሞት ክሱ ተመስርቶባቸው ጥብቅ ቁጥጥር በሚደረግበት እስር ቤት እንደሚገኙ ጠበቆቹ ገልፀዋል፡፡

Via #አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

ትላንት ታጣቂዎች በሩስያ ፣ #ሞስኮ በሚገኘው የክሮከስ አዳራሽ የሙዚቃ ዝግጅት ለመታደም በተሰበሰቡ በርካታ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ የተገደሉ ሰዎች 115 የደረሱ ሲሆን 100 ሰዎች መቁሰላቸውን የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።

ከተገደሉት ውስጥ ህፃናትም እንደሚገኙበት ተነግሯል።

4 ታጣቂዎችን ጨምሮ 11 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሩስያ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተፈፀመውን ድርጊት " #የሽብር_ጥቃት_ነው " ሲል ጠርቶ አውግዟል።

ለጥቃቱ #IS ኃላፊነቱን መውሰዱን በበይነ መረብ የወጣ አንድ ያልተረጋገጠ መግለጫ አመልክቷል።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት ፤ IS ሩሲያን ለማጥቃት እንደሚፈልግ የሚያሳይ መረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

አሜሪካ በሞስኮ ከተማ " ሕዝብ በሚበዛባቸው ስፍራዎች " ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሩሲያን አስጠንቅቃ ነበር።

ከ2 ሳምንታት በፊት በሩሲያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ በርካታ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ሕዝባዊ ስፍራዎች እንዳይሄዱ ማስጠንቀቂያ አስተላልፎ ነበር።

በማስጠንቀቂያው ላይ " ጽንፈኞች በሞስኮ ሕዝብ በሚሰባሰቡባቸው ስፍራዎችን (የሙዚቃ ኮንሰርትን ጨምሮ) የጥቃት ዒላማ ለማድረግ ዕቅድ አላቸው " የሚል ሪፖርትን እየተከታተልኩ ነው ሲል ገልጾ ነበር።

ኤምባሲው ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ ወደደረሰበት ስፍራ ዜጎቹ ዝር እንዳይሉ ምክር ማስተላለፉን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#RUSSIA ሩስያ ባለፈው ሳምንት ማንኛውም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንቀስቃሴን #ሕገወጥ በማለት ፈርጃለች። የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዓለም አቀፍ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዷል። ይህ እገዳ ይፋ ከተደረገ በኃላ ባለፈው አርብ ምሽት የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦ ° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች)…
#ሩስያ

ከዚህ ቀደም ማንኛውም አይነት #የግብረሰዶም እንቀስቃሴን #ሕገወጥ እና #ጽንፈኛ በማለት ፈርጃ የነበረችው ሩስያ አሁን ደግሞ የግብረሰዶም እንቅስቃሴን #የአክራሪነት እና #የሽብር ድርጊት ዝርዝር ውስጥ አካታዋለች።

በዚህም ማንኛውም ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም እንቅስቃሴ በሩስያ በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ዝርዝር ውስጥ ተካቷል።

ውሳኔው የተደረሰው የሩስያ የፍትህ ሚኒስቴር የቀረበለትን አቤቱታ ተከትሎ የግብረሰዶም ተከራካሪዎች #አክራሪ እና #አሸባሪ ተብለው እንዲጠሩ በህዳር ወር ላይ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ነው።

በቅርቡ የሩስያ ፍርድ ቤት በ " አክራሪ ድርጅት " ውስጥ ሚና አላቸው በሚል በመወንጀል ሁለት የመጠጥ ቤት / ባር ሰራተኞችን በእስር ቤት እንዲቆዩ እና እዛው እስር ቤት ሆነው ፍርዳቸውን እንዲከታተሉ ወሷል።

የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከዚህ በፊት ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዶ ነበር።

በወቅቱም የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦
° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች)
° የተመሳሳይ ፆታ ፓርቲዎችን ያዘጋጃሉ በተባሉ ባሮች
° የወንዶች ሳውና ቤቶች ላይ ዘመቻ አካሂደው ተጠርጣሪዎችን አስረው እንደነበር ይታወሳል።

በሩሲያ የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት እውቅና #የለውም

በሩሲያ #ትዳር ማለት የወንድ እና የሴት ጥምረት ማለት ስለመሆኑ ትርጉም ለመስጠት የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ከ3 ዓመታት በፊት ተቀይሮ ነበር።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia