TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አንዋር መስጂድ⬆️

ዛሬ በዕለተ ጁምአ ቀን የኮልፌ #ክርስቲያን ወጣቶች እጅ ለእጅ ተያይዘው ወደ ታላቁ አንዋር መስጂድ በማቅናት ‹‹ኢትዮጵያ የሁላችን #ሀገር፤ የሁላችን #ቤት ናት!›› ብለው #የፅዳት እና #የችግኝ ተከላ አድርገዋል፡፡

©ጋዜጠኛ ጌጡ ©ሄኖክ ፍቃዱ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ‼️

ጀሞ 1 አካባቢ ያሉ #ቤት_አልባ ውሾች ከአቅም በላይ ሆነውብናል፤ የሚመለከተው የአስተዳደር ክፍል አፋጣኝ እርምጃ ይውሰድ ሲሉ በአካባቢው የሚኖሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም ተግባር--አ/አ ኮተቤ🔝

በሀያት #መድሀኒአለም_ቤተክርስቲያን 1200 ሰዎች #ቤት_ፈርሶባቸው እንደተጠለሉ ይታወቃል፤ ዛሬ የኮተቤ አካባቢ ነዋሪዎች በቤተክርስቲያን ለተጠለሉት ወገኖች 1200 እንጀራ እና 53 ደርዘን ውሃ ይዘው በመሄድ እገዛ አድርገዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 2 ጉዳዮች ከጋምቤላ፦ ዛሬ የጋምቤላ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አጉቱ አዲንያግ በወቅታዊ ጉዳይ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በዚህም ክልሉ ንፁሃን ላይ የሚደርስን ጉዳት ለመቆጣጠር ከፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል። ኃላፊው በከተማይቱ ብሄርን መሰረት አድርጎ ጥቃት አልተፈፀመም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚነገረው ወሬ ሁሉ ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል። ነገር ግን…
ጋምቤላ ክልል ፡ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈጸሙ የኃይል እርምጃዎች

ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በጋምቤላ ከተማ፣ ጋምቤላ ክልል ከጠዋት እስከ ምሽት የቀጠለ ግጭት እና የፀጥታ እና የደኅንነት ችግርን ተከትሎ ለአንድ ቀን የከተማዋ የመንግሥት አገልግሎቶች፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች እና ሌሎችም አገልግሎቶች ተቋርጠው መዋላቸው ይታወሳል።

ጥቃቱ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) እና በጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች የተከፈተ እንደነበር እና ክስተቱ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የክልሉ መንግሥት አሳውቋል።

በዕለቱ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ የከተማዋ ፀጥታ የተረጋጋ እና በአሁኑ ወቅት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በከተማው የሚገኝ ቢሆንም እስከ አሁንም ድረስ የተሟላ መረጋጋት አለመስፈኑን፣ የነዋሪዎች የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ አለመጀመሩን እና በተለይም የንግድ አካባቢዎችን ጨምሮ በአንዳንድ ስፍራዎች ዘረፋ እንደተፈጸመ ነዋሪዎች ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስረድተዋል። 

በተጨማሪም ከሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች (በክልሉ ልዩ ኃይል እና መደበኛ ፖሊስ) በተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች ምክንያት ነዋሪዎች ለተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየተጋለጡ መሆናቸውን እና ከሕግ ውጭ ግድያ ስለመፈጸሙ ለኢሰመኮ መረጃዎች እየደረሱት ይገኛል።

በተለይም በጥቃቱ ተሳትፈዋል ወይም ተባብረዋል ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ #ቤት_ለቤት በመሄድ ጭምር ግድያዎች እንደተፈጸሙ ኢሰመኮ ከምስክሮችና የተንቀሳቃሽ ምስል ማስረጃዎች ጭምር ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል። 

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የሰዎችን ደኅንነትና የከተማዋን ሰላም ማረጋገጥ ቀዳሚው ተግባር መሆኑን አስታውሰው፣ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚወሰዱ እርምጃዎች በሙሉ የሰብአዊ መብቶችን መርሆች ሊከተሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተለይ የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ሊያጠፋ ከሚችል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡና በፀጥታ ኃይሎች የተወሰዱ ሕገ ወጥ ተግባራት ላይ በአስቸኳይ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ/ም

@tikvahethiopia
ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ !

የፌዴራል የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ፤ የክልልነት ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኙ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ጉዳዩን የአመጽና የሁከት መነሻ ለማድረግ በሚሞክሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በስሩ የሚገኙ ዞኖችን በአዲስ መልክ ለማዋቀር እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

ጌዲኦም በአዲስ መልክ ከሚዋቀሩ ዞኖች አንዱ ሲሆን፤ የኅብረተሰቡን ተሳትፎ በተጨባጭ ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ሰሞኑን የማወያያ ሰነዶች ተዘጋጅተው የዞኑ ነዋሪ እየመከረበት ነው።

ይሁንና የጌዲኦ ዞን የክልልነት ጥያቄ መፍትሔ የማይሰጠው ከሆን ጥያቄያችንን በኃይል እናስፈጽማለን የሚሉ አካላት በህቡዕ ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ በተጨባጭ ተረጋግጧል።

በህቡዕ የተደራጁት አካላት የጥፋት እቅዶቻቸውን ለማሳካት ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች በመክፈት የተዛቡና የፈጠራ መረጃዎችን እያሰራጩ ሲሆን ማኅበረሰቡንም በተሳሳቱ መረጃዎች ለማደናገር እየሞከሩ ይገኛሉ።

እነዚህ አካላት ያደራጇቸው ግለሠቦችና ቡድኖች #ቤት_ለቤት ጭምር እየተንቀሳቀሱ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ፤ ይህም ባግብረኃይሉ ተደርሶበታል።

ለዚህ እኩይ ዓላማ የተደራጁና የተሰለፉ ግለሠቦችንና ቡድኖችን በደኅንነትና በጸጥታ መዋቅር አማካኝነት ተለይተው ክትትል እየተደረገባቸው ነው። ይህን በማስገንዘብ፤ ከጥፋት ተልዕኳቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን።

ይህን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ እናስጠነቅቃለን። "

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Turkey ትላንት ምሽት ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ ተመታች። እጅግ አስከፊው የመሬት መንቀጥቀጥ (7.8) ከተከሰተ ከሁለት ሳምንት በኃላ ቱርክ ትላንት ምሽት በሬክተር ስኬል መለኪያ 6.3 በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መመታቷ ተሰምቷል። የመሬት መንቀጥቀጡ የመታው አካባቢ ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ከባድ ጉዳት ባጋጠመው በሃታይ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ደቡባዊዋ ሳማንዳግ ከተማ አቅራቢያ…
#ቱርክ

አንድ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ባለስልጣን በቱርክ ከሁለት ሳምንት በፊት በተከሰተው የመሬት መቀጥቀጥ 1.5 ሚሊዮን ሰዎች #ቤት_አልባ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪ እኚሁ ባለስልጣን ፤ ሀገሪቱ ውስጥ ወደ 500,000 የሚጠጉ ቤቶች እንደገና መገንባት አለባቸው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከትላንት ወዲያ በድጋሚ ቱርክን በመታት የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 8 ስለመድረሱ የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ የሀገሪቱን እና የዜጎችን ወቅታ ሁኔታ ግምት ዉስጥ ያላስገባ ነው " - ዶክተር እንዳለ ሀይሌ በአዲስ አበባ ዙሪያ ህገ-ወጥ ናቸዉ የተባሉ ቤቶች በዘመቻ መልክ እየፈረሱ እንደሆነ ይታወቃል። ቃላቸውን ለአሐዱ ሬድዮ እና ቴሌቪችን የሰጡት የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሀይሌ ፤ በአዲስ አበባ ዙሪያ እና ቡራዩ አካባቢ ቤት እየፈረሰባቸዉ…
የቀጠለው የቤት ማፍረስ ዘመቻ ...

በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚደረግ የቤት ማፍረስ ዘመቻ ጋር በተገናኘ ቤት የፈረሰባቸው ዜጎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገሩት ፦

• " ... #ቤት_ለመፈለግ እንኳን በቂ ጊዜ አልተሰጠም በዚህም እቃችንን ወደ ምናውቃቸው ሰዎች አሽሽተናል ፤ መጠለያ አጥተው ሜዳ ላይ የወደቁም ጎረቤቶችም አሉ። ቤት ለመከራየት እንኳን የቤት ኪራይ በዚህ ምክንያት ጨምሯል።"

• " የዚህኛው ዙር ይለያል ብዙ ቤቶች ናቸው የፈረሱት፥ በሺ የሚቆጠር ሰዎች ከቤታቸው ወጥተው ሜዳ ላይ ወድቀዋል፣ ድብደባም እስርም የተፈጸመባቸው ዜጎች አሉ "

የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እምባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ለባላጉሩ ቴሌቪዥን ከሰጡት ቃል ፦

" ... ጉዳዩን በሕገ-ወጥነት መነጽር ብቻ መመልከት አግባብ አይደለም” ያሉት ዋና እንባ ጠባቂዉ፤ ከዜግነት መብትና ከሰብዓዊነት አንፃር መንግስት ጉዳዩን መመልከት የሚገባው ቢሆንም ሃላፊነቱን አልተወጣም። "

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/ETH-02-23-4