#DawitNega
በትግርኛ የሙዚቃ ስራዎች በእጅጉ የሚታወቀው አርቲስት ዳዊት ነጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ።
አርቲስት ዳዊት ህመም አጋጥሞት ያለፉትን ቀናት በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበር ተነግሯል።
የአርቲስት ዳዊት ነጋ የሙዚቃ ስራዎች የትግርኛ ቋንቋ ከሚያደምጡ ሰዎች ባለፈ ቋንቋውን በማያዳምጡትም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበሩ ናቸው።
ከሙዚቃ ስራዎቹ መካከል ፦ ባባ ኢለን፣ ዘዊደሮ፣ ወዘመይ፣ ቸቸኮላታ፣ ኣጆኺ ትግራይ፣ ቕዱስ ፀባያ የሚሉት ይጠቀሳሉ።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#DawitNega በትግርኛ የሙዚቃ ስራዎች በእጅጉ የሚታወቀው አርቲስት ዳዊት ነጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ። አርቲስት ዳዊት ህመም አጋጥሞት ያለፉትን ቀናት በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበር ተነግሯል። የአርቲስት ዳዊት ነጋ የሙዚቃ ስራዎች የትግርኛ ቋንቋ ከሚያደምጡ ሰዎች ባለፈ ቋንቋውን በማያዳምጡትም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበሩ ናቸው። ከሙዚቃ ስራዎቹ መካከል ፦ ባባ ኢለን፣…
#DawitNega
የአርቲስት ዳዊት ነጋ ቤተሰቦች እና ጓደኞች ለቢቢሲ ትግርኛ የሰጡት ቃል ፦
" ባደረበት ድንገተኛ ህመም ዓርብ ዕለት ነው አዲስ አበባ አዲስ ህይወት ሆስፒታል የገባው።
ባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት በጉንፋን መልክ የጀመረ ህመሙ ከተባባሰ በኋላ ዓርብ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ እስከ ቅዳሜ ድረስ ህክምና ሲደረግለት ቆይቷል።
ትናንት እሁድ ከሰዓት በኋላ ህመሙ ሲጸናበት ወደ ጽኑ ህሙማን ክትትል ክፍል ገብቷል ማታ 1፡ዐዐ ሰዓት አካባቢ ህይወቱ አልፏል።
ወደሆስፒታሉ ከመምጣቱ በፊት ህመሙን ለማስታገስ በቤት ውስጥ ግሉኮስ ይወሰድ ነበር።
ህመሙ ሲበረታበት ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ የስኳር መጠኑ መጨመሩን እና ህመሙ ወደ የሳንባ ምች (ኒሞኒያ) መቀየሩን ተነግሮታል።
የዳዊት አስከሬን ላይ ተጨማሪ ምርመራ ይደረጋል። "
Via BBC Tigrinya

አርቲስት ዳዊት ነጋ ማን ነው ? - ተወልዶ ያደገው በትግራይ ክልል ፤ መቐለ ከተማ እንዳማርያም ነው። - ትምህርቱን የተከታተለው በዓይደር ት/ቤት ነው ፤ የሙዚቃ ስራንም አንድ ብሎ የጀመረው በመቐለ ሲሆን በ15 ዓመቱ የሙዚቃን ስራ መጀመሩን በአንድ ወቅት ተናግሯል። - በመጀመሪያ ለመዝፈን ' ሰርከስ ትግራይ ' የሄደው ዳዊት አንዳልተቀበሉት ፤ በኃላም ወደ ማርሽ ባንድ ገብቶ በድራመርነት ለ6 ዓመት…
#DawitNega
የአርቲስት ዳዊት ነጋ የቀብር ስነስርዓት ነገ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስትያን እንደሚፈፀም ታውቋል።
አርቲስት ዳዊት ነጋ በህይወት ሳለ " ካሌብ ሾው ' በተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ቃለመጠይቅ በሰጠበት ወቅት ለወጣቶች ያስተላለፈው መልዕክት ፦
" ... ስኬት አጠገብህ ነው ያለው። በጣም ሩቅ መስሎ የሚታያችሁ ፣ በጣም ጨለማ መስሎ የሚታያችሁ ነገር ከናተ ጋር ነው ያለው።
ለምንም ነገር መሸነፍ የለብህም። ማንም ሰው የፈለገውን ማድረግ እንደሚችል በእኔ መማር አለበት።
እኔ ትልቅ ነገር ሰርቼ ሳይሆን በአቅሜ የምችለውን ነገር እየሰራው ነው፤ ቢያንስ ትላንት የምተኛበት ቤት አልነበረኝም፤ ለረጅም ጊዜ የእራት መብያ እንኳን አልነበረኝም እንደኔ ያጣ ኢትዮጵያዊም ያለ አይመስለኝም።
ተስፋ አልቆርጥም። አንድ ጊዜ ሰው ሆናለሁ ብዬ አልሸነፍም ነበር። የ200 ብር የቤት ኪራይ መክፈል ሲያቅትህ አስበው ...
ወጣቱ በእኔ እንዲማር እፈልጋለሁ። የሚፈልገውን ስራ ዶክተር ፣ መሃንዲስ ሊሆን ይችላል የፈለገውን አይነት ሞያ ያለው ሰው እኔ ሰርቼ እቀየራለሁ ብሎ እራሱን ማሳመን አለበት ፤ ከዛ ለራሴ ሆኜ ለሀገሬ ፣ ለህዝቤ ሆናለሁ ብሎ ማሰብ አለበት ፤ ተስፋ ካልቆረጠ ማንም ሰው ምንም ማደረግ ይችላል። "