TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ : እስካሁን ድረስ ከፍተኛ ነው የተባለ የሰብዓዊ ድጋፍ ኮንቮይ ትግራይ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) አሳውቋል።

ድርጅቱ በዚህ ሳምንት 308 ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ መግባታቸውን ያመለከተ ሲሆን 800 ሺህ ለሚደርሱ ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ በቂ ምግብ የያዙ ናቸው ብሏል።

በሌላ በኩል አሁን በአማራ እና አፋር ክልል እየተካሄደ ያለው የምግብ ስርጭት እንደተጠናቀቀ በቀጣይ የ6 ሳምንት ዙር የምግብ ስርጭት እንደሚጀመር አሳውቋል።

በሌላ መረጃ #ትግራይ ፦ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ዛሬ ከሰዓት ለስድስተኛ ጊዜ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ የውሃ ማጣሪያ ግብዓቶችን እና አስፈላጊ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን ይዞ መቐለ ገብቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በአዲስ አበባ ሀርመኒ ሆቴል ለዓለም ዓቀፉ የቁርዓን ውድድር ማጣሪያ ሲካሄድ ውሏል። የፊታችን እሁድ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የቁርኣን ሂፍዝ ውድድር እንደሚካሄድ ይታወቃል። በዚህ ልዩ ውድድር ላይ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የመጡ ተወዳዳሪዎች መካከል ዛሬ የማጣሪያ ውድድሩ እየተካሄደ ሲሆን ውድድሩ በዓለም ዓቀፍ ዳኞች የተመራ ነበር። በእሁዱ ውድድር የሶማሌ ክልሉ ተወላጅ…
#እጅግ_በጣም_አስቸኳይ

በነገው ዕለት የዓለምዓቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር መዝጊያ ፕሮግራም በስታድየም ይደረጋል ተብሎ የተገለጸ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁንና አንዳንድ ዶክመንቶች በጊዜ ባለማሟላታቸው እንዲሁም አዲስ አበባ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት የተቆፋፈረና ምቹ ባለመሆኑ የመዝጊያው ፕሮግራም ከስታዲየም ውጪ እንዲደረግ ተወስኗል።

ስለዚህም ህዝቡን ይቅርታ እየጠየቅን ከዚህ ጋር የተያያዙ ዝርዝር ጉዳዮችን በቀጣይ ጊዜያት የምናሳውቅ ይሆናል።

ማሳሰቢያ ፦ ከሀገሪቱ ጫፍ እስከ ጫፍ ወደ አዲስ አበባ እየመጣችሁ ያላችሁ እንግዶች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይህንን በመገንዘብ ሳትለፉ ባላችሁበት እንድትከታታሉ እንጠይቃለን።

(አዘጋጅ ፦ ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር)

የነገውን ፕሮግራም ተካፋይ ለመሆን ስትጠብቁ የነበራችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን የአዘጋጆቹን መልዕክት ያልሰሙ ካሉ #ሼር አድርጓቸው / ላኩላቸው።

@tikvahethiopia
#icog

iCog-ACC ልጆችን በለጋ እድሜያቸዉ መሠረታዊ የኮምፒዉተር እና ኮዲንግ ስልጠና በመሰጠት ለወደፊት ለሚጠብቃቸዉ በዲጂታል የጎለበተ አለም ዝግጁ ያደርጋቸዋል፡፡

በአሜሪካ፥ ካናዳ እና በአዲስ አበባ ብቻ ሲሰጥ የነበረው ይህ የክረምት ፕሮግራም አሁን ደግሞ በባህር ዳር፣ ሃዋሳ፣ ጅማ እና ሐረር ይሰጣል ፡፡

ልጆቻችሁን በዚህ ፕሮግራም እንዲሳተፉ የምትፈልጉ ወላጆች በስልክ ቁጥራችን +251904262728 በመደወል ይህንን ቦት @iCogACCBot ወይም ይህንንማስፈንጠሪያ በመጠቀም ከዛሬ ጅምሮ ማስመዝገብ ትችላላችሁ https://icogacc.com/register/summer+camp+program+2022
የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ እጅግ አስከፊ በነበረበት ወቅት በኮንትራንት ተቀጥረው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የጤና ባለሞያዎች ፦

" እኛ በጤና ሚኒስትር በኩል በኮቪድ ላይ በኮንትራት ተቀጥረን የምንሰራ ባለሙያዎች ነን።

ኮቪድ ከጀመረ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ ሆስፒታሎች ስናገለግል ቆይተናል።

የጤና ሚኒሰትር እና ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቋሚነት እንደተቀጠርን በደብዳቤ ገለፀው ነበር ከአንድ አመት በፊት ፤ አሁን ግን ኮንትራት ጨርሳችዋል ምንም የምናደርገው ነገር የለም ብለው ደብዳቤ ደረሰን።

ምንም አንኳን ባንመሰገን ሲያልቅ መወርወር አልነበረብንም።

ሰው እያገለለን ከቤተሰብ ተለይተን ህዝብ አገልግለን እንዲ መሆኑ ያሳዝናል።

ደብዳቤዎችን ከላይይ አያይዘናል፤ ህዝብ እንዲሰማው ብቻ ነው ምንፈልገው ፤ ጉዳዩን በተመለከተ በሲቪል ሰርቪስ በኩል ያለውን ምላሽ ሰምተን ወደ ፍርድ ቤት ለመሔድ በዝግጅት ላይ ባለንበት ሰዐት ነው የላኩት።

ከኮንትራት ደሞዝ 13k ወደ 9k ለውጠው ወጪ ለመቀነስ ነበር ፤ ነገር ግን በህጉ መሠረት ቋሚ ሠራተኛ ሳንሆን በኮንትራት እየሠራን ነው አመቱን የጨረስነው። የአሁን ምላሻቸው ግን አንገት ያስደፋል 520 ባለሙያ ከስራ ገበታው በደብዳቤ እየተባረረ ይገኛል።

መፍትሄ እንሻለን !!! "

[ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ስናገኝ እናሳውቃለን / እንልካለን]

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ እጅግ አስከፊ በነበረበት ወቅት በኮንትራንት ተቀጥረው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የጤና ባለሞያዎች ፦ " እኛ በጤና ሚኒስትር በኩል በኮቪድ ላይ በኮንትራት ተቀጥረን የምንሰራ ባለሙያዎች ነን። ኮቪድ ከጀመረ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ ሆስፒታሎች ስናገለግል ቆይተናል። የጤና ሚኒሰትር እና ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቋሚነት…
#ተጨማሪ

" የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሃገራችን ከተከሠተበት ጊዜ ጀምሮ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በኮንትራት የተቀጠርን ባለሙያዎች ተፈላጊውን ውጤት አስመዝግበናል።

ወረርሽኙን በሚገ’ባ ተቆጣጥረን ጉዳቱን ቀንሰናል።

የኮንትራት ጊዜያችን ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ሲያበቃ ማሠናበቱ አስቸጋሪነቱን በማመን (ወረርሽኙ ስላልተገታ እና የባለሙያዎችን ሞራል ለመጠበቅ) ጤና ሚኒስቴር አምኖበት ሐምሌ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ለየክልል ጤና ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ በ2014 በጀት ዓመት ቋሚ ቅጥር እንዲያዝልን ገልጾ ነበር።

ነገር ግን ላለፉት 11 ወራት የክልል ጤና ቢሮዎች ወደ ቋሚ ቅጥር አላዛወሩንም። ከሥራ ያሠናበቱም ክልሎች አሉ። ለምንጠይቀው የመብት ጥያቄም ተገቢ መልስ አልተሠጠንም።

አሁንም አበርክቶታችን ታይቶ በ2015 በጀት ዓመት የቋሚ ቅጥር በጀት ተይዞልን ቅጥር ይፈጸምልን ዘንድ እንጠይቃለን! "

[ በኮቪድ19 መከላከል በኮንትራት የተቀጠርን ባለሙያዎች ]

@tikvahethiopia
የDKT ሰራተኞች ቅሬታ !

የዲኬቲ (DKT) ኢትዮጵያ ሠራተኞች ተቋሙ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከ50 በመቶ በላይ ሠራተኞቹን በሕገወጥ መንገድ ከሥራ አፈናቅሏል ሲሉ ቅሬታቸውን ገለፁ።

🗣አንዲት ሥማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ ሠራተኛ፦

" በዚህ የኑሮ ውድነትና ሥራ አጥነት ባስቸገረበት ሰዓት፣ በሚያስደነግጥ ሁኔታ ከ50 በመቶ በላይ ሠራተኞቹን ከሥራ እንዲፈናቀሉ አድርጓል።

ተቋሙ ዓለም ዐቀፍ ተቋም በመሆኑ፣ ከሥራ የሚያባርርበት ምክንያት ለጋሽ (donor) የለም በሚል ነው። ሆኖም ለጋሽ ቢኖርም ባይኖርም በራሱ መቆም የሚችል ነው።

ሥራው ጤና ላይ ያተኮሩ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለሆስፒታሎች፣ ክሊኒኮችና ፋርማሲዎች መሸጥ ነው። በዚህ ወቅት በምርቶች ላይ አስደንጋጭ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ሕገወጥ ሥራ እየሠራ ነው።

ከአሽከሪካሪዎች ጀምሮ እስከ አስተዳደር ሠራተኞችም በመላ አገሪቱ በሚገኙ ሠራተኞች ላይ ሕገወጥ የሥራ ማፈናቀል እየደረሰባቸው ነው።

በተጨማሪም ይህን ተግባር እየፈጸሙ ያሉት በትውልድ ፓኪስታናዊ የሆነው አሜሪካዊ የማዕከላዊ ቢሮ ኃላፊ (country director) እና የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ኃላፊው (area office manager) በጋራ በመሆን ነው "

🗣 ሥማቸውን ሳይጠቅሱ ቅሬታ ያቀረቡ ሠራተኛ ፦

" ከ5 ዓመት በላይ በቋሚነት ሰርቻለሁ። ሆኖም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተነሳ ታስሬ ስመለስ ከሥራ ታገድኩ።

በዚህም ፍ/ ቤት ከስሼ የነበረ ቢሆንም ከዚህ በፊት ከሥራችን ውጪ በዓመት 10 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ ነበረን። አሁን በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ወደ 2 ሚሊዮን ዶላር ስለወረደ ሠራተኛ እየቀነስን፣ አዲስ መዋቅርም እየሠራን ነው የሚል ምላሽ አቅርበዋል...

ያንብቡ telegra.ph/Addis-Maleda-06-12

Credit : www.addismaleda.com

@tikvahethiopia
" እኔም የዕርቅ ሀሳብ አለኝ "

በ2012 ዓ/ም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከእርቀ ሰላም ኮሚሽን ጋር በመተባበር ''የእርቅ ሀሳብ አለኝ'' የተሰኘ ባህላዊ የእርቅ ሥርዓቶች ላይ ያተኮረ የገላጭ ጹሑፍ ውድድር ማዘጋጀቱ ይታወሳል።

በዚህ ውድድር ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ቁጥራቸው ከ370 በላይ ተሳታፊዎች ውድድሩን ያካሄዱ ሲሆን ወደ ሦስት መቶ የሚጠጉ የሀገራችን ባህላዊ የእርቅ ሥርዓቶችን ሰንደው አስቀምጠዋል።

ተሳታፊዎች የነበሩ ወጣቶች እነዚህን የሀገር በቀል እውቀቶች በነበር ከመስማት አልፈው በማንበብ፣ በመጠየቅና በመሳተፍ መረጃዎችን በማሰባሰብ ትልቅ ሥራ ሰርተዋል።

አነዚህን የተሰበሰቡ የጹሑፍ ሥራዎች ወደ እናንተ ወደ ቤተሰቦቻችን ከዛሬ ጀምሮ የምናደርስ ሲሆን በቀጣይ እነዚህን የእርቅ ሥርዓቶችን ወደ ዳበረ የጥናት መዝገብ እንዲሁም በይበልጥ ተደራሽ በሆኑ መንገዶች ለማድረስ የምንሰራ ይሆናል።

እነዚህ ጹሑፎች ወደ ህብረተሰቡ መድረሳቸው በየአካባቢው ያሉ የእርቅ እሴቶቻችን በመገንዘብና በማዳበር ሁሉን አካታች፣ አሳታፊና ማኅበራዊ መሰረታቸውን የጠበቁ የእርቅ ሥርዓቶቻችንን ማስተዋወቅና ከእነሱም ለመጠቀም ፤ ችግሮች ይፈቱ ዘንድ ድጋፍ ለማድረግ ነው።

@tikvahethiopia
ኦገት.pdf
379.8 KB
#እኔም_የዕርቅ_ሀሳብ_አለኝ

#ኦገት (የሀላባ ብሔረሰብ ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት)

አዘጋጅ :- ዬጎሬ ዳቆሮ ዲዶ

- የሀላባ ብሔረሰብ ባህላዊ የእርቅ ሥርዓት ኦገት ሲባል ይህ የዳኝነት ስርዓት ከዝቅተኛዉ የአስተዳደር እርከን ከሆነው ‹‹ቦኪ ኦገት›› (የቤተሰብ ሸንጎ) እስከ ከፍተኛው እርከን ‹‹ሀላቢ ኦገት›› ይደርሳል፡፡

- በሀላባ ባህላዊ የአስተዳደር ስርዓት አንድ ማዕከላዊ ስልጣን የለም፡፡ በየደረጃዉ የራሱ ስልጣን እና ኃላፊነት ያለዉ የአስተዳደር እርከን አለ፡፡

- ‹‹ጎጎቲ ኦገት›› ሀላባ ዉስጥ ከሚደረጉ የኦገት አይነቶች አንዱ ሲሆን ይህ ኦገት ሀላባን ከአጎራባች ብሔረሰቦች ጋር የሚያስተሳስር የኦገት አይነት ነዉ፡፡ በዚህ ጠቅላላ ሸንጎ ላይ ከሀላባ አጎራባች ህዝቦች ጋር የድንበር ጉዳዮችንና የድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን፣ የጋራ ሀብትን በሚመለከትና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ከጋራ ስምምነት የሚደረስበት ነዉ፡፡

- ከሀላባ ብሔረሰብ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት (ኦገት) ተግባራት ዉስጥ አንዱ ‹‹ጉምጉማ›› ነዉ፡፡ ጉምጉማ ማለት የኦገቴዉ ቆርቶዎች ጥፋተኛዉ ከተለየ በኋላ የቅጣት ዉሳኔ ላይ ከሸንጎዉ ተሳታፊዎች መካከል አስተያየት የሚቀበሉበት ስርዓት ነዉ፡፡

- በአሁኑ ወቅት ኦገቴ ዘመናዊዉን የህግ ስርዓት በበጎ ጎን የሚያግዝ ስሆን ጉዳዮችን ከፍርድ ቤት በመዉሰድ በሴራዉ መሰረት እየፈታም ይገኛል።

- ከዘመናዊዉ የህግ ስርዓት ጋር አብሮ ስለማይሄድ ተፈጻሚነታቸዉ ከቀሩ ባህላዊ የቅጣት አይነቶች መካከል አንዱ ያዩ (ማህበረሰባዊ ማግለል) ነዉ፡፡ ምንም እንኳን ዓላማዉ ጥፋተኛዉን ለሴራዉ ተገዢ እንዲሆን ማድረግ ቢሆንም ከሰብዓዊ መብት አንጻር ግን ገደብ የሚጣልበት ሆኗል፡፡

(በPDF የተያያዘውን ፋይል ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ወላጆች_ለልጆች_ጥንቃቄ_እንዲያደርጉ_አሳስቧቸው ! ትናንትና በአዲስ አበባ ከተማ በጣለው ዝናብ አንድ ተማሪ በጎርፍ እንደተወሰደ ተሰምቷል። የአዲስ አባባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ የኮሙኒኬሽን ተማሪው በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላዛሪስት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ተማሪ መሆኑን አመልክቷል። ተማሪው በጎርፍ የተወሰደው ትላንት 9 ሠዓት አካባቢ በጣለው ዝናብ መሆኑን የገለፀው ኮሚኒኬሽኑ በጎርፉ…
#Update

በአዲስ አበባ ከተማ አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው ላዘሪስት ትምህርት ቤት ወንዝ ውስጥ የገባው ማርኮን ይገረም አለመገኘቱን የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ ።

ኮሚሽኑ ለአል ዐይን ኒውስ አማርኛ በሰጠው ቃል ፤ የኮሚሽኑ ሰራተኞች አሁንም ፍለጋ ላይ ናቸው።

ህጻኑ ከጠፋ አምስት ቀናት ቢቆጠሩም እስካሁን አለመገኘቱ ተገልጿል። በጎርፍ የተወሰደውን ማርኮን ይገረም አካል ለማግኘት ፍለጋው ቀጥሏል ተብሏል።

ህጻኑ ረቡዕ ዕለት ወንዝ ውስጥ የገባው።

ዘንድሮ ትምህርትን " ሀ " ብሎ ሊጀምር በአዲስ አበባ አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው ላዘሪስት ት/ ቤት የገባው የ4 ዓመቱ ማርኮን ይገረም ባለፈው ረቡዕ ከት/ ቤት ሲወጣ ከት/ ቤቱ አጥር ውጭ ያለው ትቦ ውስጥ በመግባቱ በትቦ ውስጥ የነበረው የጎርፍ ውሃ ይዞት ሄዷል።

በትምህርት ቤቱ አካባቢ ካሉ ወንዞች ጀምሮ የአፍንጮ በር በቀበና በአቃቂ በአባ ሳሙኤልም ባሉ ወንዞች ጎረቤትና ዘመድ አዝማድ እንዲሁም የእሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ፍለጋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።

#አልዓይን_ኒውስ

@tikvahethiopia
የብርሃን ሞባይል ባንኪንግን ተጠቅመው :-

- የዋይፋይና ሌሎችም የኢትዮ ቴሌኮም ክፍያዎችን በቀላሉ ያከናውኑ
- የአየር ትኬትዎን ይቁረጡ!
- ቀሪ የብድር መጠንዎን ይወቁ
- (*881#) በመጠቀም ያለ ኢንተርኔት ገንዘብ ማስተላለፍ
- በሞባይልዎ የቼክ ደብተር ይዘዙ!
- የት/ቤት ክፍያዎን በቀላሉ ይክፈሉ!
ከራስዎ የባንክ ሂሳብ ወደ ሌሎች ባንኮች ሂሳብ ገንዘብ በማስተላለፍ
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
TIKVAH-ETHIOPIA
#እጅግ_በጣም_አስቸኳይ በነገው ዕለት የዓለምዓቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር መዝጊያ ፕሮግራም በስታድየም ይደረጋል ተብሎ የተገለጸ መሆኑ ይታወቃል። ይሁንና አንዳንድ ዶክመንቶች በጊዜ ባለማሟላታቸው እንዲሁም አዲስ አበባ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት የተቆፋፈረና ምቹ ባለመሆኑ የመዝጊያው ፕሮግራም ከስታዲየም ውጪ እንዲደረግ ተወስኗል። ስለዚህም ህዝቡን ይቅርታ እየጠየቅን ከዚህ ጋር የተያያዙ ዝርዝር…
#Update

ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድሩ ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።

ዓለም አቀፍ የቁርአን ውድድሩ በነገው እለት ጥዋት በአዲስ አበባ ስቴዲየም እንዲካሔድ በመንግስት ፍቃድ መሠጠቱ ተሰምቷል።

በዚህም መሠረት ነገ ሰኔ 6 ቀን 2014 ፕሮግራሙ እንደሚካሔድ አዘጋጆቹ ማሳወቃቸውን ሀሩን ሚዲያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia