TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ከ60 በላይ የጤና ባለሙያዎች ፤ " ጤና ሚኒስቴር በሕግ የተወሰነልንን ልዩ አበል አልከፈለንም " አሉ። የጤና ባለሙያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት፤ የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ / ም መከሰቱን ተከትሎ የጤና ማኒስቴር ባወጣው ጥሪ መሠረት የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ / ም ባወጣው መመሪያ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ለመላው ሀኪሞች በቀን…
#ጤና_ሚኒስቴር #ክስ

የፍርድ ቤት ውሳኔን በተደጋጋሚ ጣሰ የተባለው " ጤና ሚኒስቴር " ለ70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ -19 ልዩ አበል እንዲከፍል ፍርድ ቤት በድጋሚ ለንግድ ባንክ ትዕዛዝ አስተላለፈበት።

70 የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ ወረርሽኝ #ልዩ_አበል እንዲሰጣቸው በመሰረቱበት ክስ መሠረት ገንዘቡን እንዲከፍል ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በተደጋጋሚ ጥሷል የተባለው " ጤና ሚኒስቴር " አሁንም ከንግድ ባንክ አካውንቱ #እየቆረጠ_እንዲከፍል ፍርድ ቤት በድጋሚ ለንግድ ባንክ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጤና ባለሙያዎቹ ገለጻና ከተጻፈው ደብዳቤ መረዳት ችሏል።

የጤና ባለሙያዎቹ ተወካይ የፍርድ ሂደቱ በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

* ፍርድ ቤት ለባንክ ሲያዝ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

* የፋይናንስ ክፍሉ ኃላፊ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ድክመት ለፍርድ ቤት #ታስረው ቀርበው እንዲያስረዱ ቢታዘዝም ጉዳዩን እንዲያስፈፅም የታዘዘው የፌደራል ፖሊስ መስሪያ ቤቱ ድርስ በመሄድ ቢጠይቅም እረፍት እንደወጡና እስከ ሰኞ (ያለፈው ሳምንት ሰኞ) እንደሚመጡ አሳውቀው ነበር። ከዚያ በኋላም ፍርድ ቤት መጥተው አያውቁም።

* ታስረው እንዲቀርቡም #ከሁለት_ጊዜ_በላይ ነው የታዘዘው።

* ፍርድ ቤት በራሳቸው እንዲፈፅሙ ግን በተደጋጋሚ (ከአምስት ጊዜ በላይ) ትዛዝ ሰቶ ነበር።

* ሰዎቹ በፍፁም ለህግ ተገዢ አለመሆናቸውን እና እምቢተኝነታቸውን በተደጋጋሚ ጊዜ አሳይተውናል።

* ለፍርድ ቤት ውሳኔ ያላቸው ንቀት በቃላት የሚገለፅ አይደለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ይሄንን የጤና ባለሞያዎች መረጃ በማደራጀት ሂደት የጤና ሚኒስቴርን ምላሽ እና ማብራሪያ ለማካከት ብዙ ቢደክምም ምላሽ ሰጪ አላገኘም።

አሁንም #በአካልም ይሁን #በስልክ ምላሽ ሰጣለሁ የሚል የሚኒስቴር መ/ቤቱን አካል ለማስተናገድ ዝግጁ ነው።

ዝርዝሩን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-14

የመረጃው ዝግጅት በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ሬዚደንት #JU

“ የ3 ወራት ያህል ደመወዝ አልተከፈለንም ” - የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሬዚደንት ሀኪሞች

“ ይህ ጉዳይ ጤና ሚኒስቴርን ነው የሚመለከተው ” - ዩኒቨርሲቲው

በ2016 ዓ/ም በጤና ሚኒስቴር #በጅማ_ዩኒቨርሲቲ  ተመድበው በሆስፒታሉ ሥራና ስፔሳላይዜሽን ስልጠና የሚወስዱ 70 የአንደኛ ዓመት ሬዚደንት ሀኪሞች የ3 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ቅሬታ አቅርበዋል። 

“ የ3 ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም። ከፍተኛ ችግርና ስቃይ ውስጥ ወድቀናል ” ያሉት ቅሬታ አቅርቤዎቹ፣ ጉዳዩ የሚመለከተውን አካል ቢያነጋግሩም ‘ መፍትሄ እየፈለግን ነው ፤ ዩኒቨርሲቲው በጀት የለውም ’ እንደተባሉ ገልጸዋል።

መጀመሪያ 100 ሬዚደንት ሀኪሞች እንደነበሩ ፤ በኋላ ግን ለቀው ለመሄድ በመገደዳቸው አሁን ላይ የቀሩት 70 ብቻ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ቤተሰብ ጭምር ይዘው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሄዱ ሬዚደንት ሀኪሞችም እንዳሉ ፤ የሚተዳደሩት ከደመወዝ በሚያገኙት ገቢ እንደሆነ ገልጸዋል።

“ በጣም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ያለነው። ደመወዙ በዚህ ሳምንት ሊገባልን ይገባል ” ሲሉ አሳስበዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ፣ “ ጤና ሚኒስቴርን ነው የሚመለከተው። እኛን አይመለከትም ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመጠየቅ ወደ #ጤና_ሚኒስቴር የተደረገው ሙከራ ኃላፊዎቹ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለጊዜው ቃላቸውን ማካተት አልተቻለም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ኦዲት የ2015 በጀት ዓመት የፌዴራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች የኦዲት ክንውን ላይ ማብራሪያ እየተሰጠ ነው። ሂሳብ አቅራቢ የነበሩት 173 የፌዴራል መንግስት ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች ሲሆኑ የ162 መ/ቤቶች እና 58 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በፌዴራል ኦዲተር መ/ቤት 11 ደግሞ በሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን ኦዲት ሊደረጉ ታቅዶ ነበር። 10 መስሪያ ቤቶች 4 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በጸጥታ…
#ኦዲት #ኢትዮጵያ

ጤና ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር  ከፍተኛ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከተገኘባቸው ተቋማት መካከል መሆናቸው ተሰምቷል።

ለውሎ አበል እና ለመጓጓዣ እንዲሁም ለግዥ የተሰጠ ክፍያ ሰራተኛው ስራውን አጠናቆ ከተመልሱ በኃላ በ7 ቀናት መወራረድ እንዳለበት መመሪያ አለ።

ነገር ግን በ124 መስሪያ ቤቶች በጠቅላላው ብር 14.1 ቢሊዮን በወቅቱ ያልተወራረደ ወይም ያልተሰበሰበ ተሰብሳቢ ሂሳብ መኖሩ በኦዲት ታውቋል።

ጊዜው ሲታይም ከ1 ወር በላይ እስከ 1 ዓመት 1 ቢሊዮን 193 ሚሊዮን ብር ፤ ከ1 ዓመት በላይ እስከ 5 ዓመት 10.9 ቢሊዮን ብር ፤ ከ5 ዓመት በላይ እስከ 10 ዓመት 1.7 ቢሊዮን ብር ፤ ከ10 ዓመት በላይ 139 ሚሊዮን ነው።

ቀሪው ሂሳብ በቆይታው ጊዜ ያልተተነተነ ነው።

ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከተገኘባቸው ተቋማት #ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት እነማን ናቸው ?

#ጤና_ሚኒስቴር 6 ቢሊዮን
የመስኖ ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር 1.1 ቢሊዮን
የትምህርት ሚኒስቴር 1 ቢሊዮን 12 ሚሊዮን
በፌዴራል መንግስት የህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት 970.9 ሚሊዮን
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚኒሊየም የህክምና ኮሌጅ 756.3 ሚሊዮን
የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 433.5 ሚሊዮን
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት 286.8 ሚሊዮን
የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን 272.4 ሚሊዮን
የመንግስት ግዥ አገልግሎት 265.2 ሚሊዮን
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 250.7 ሚሊዮን
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር 218.3 ሚሊዮን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

በተጨማሪ የፕሮጀክት ሂሳብ በታየባቸው 4 መስሪያ ቤቶች 514.5 ሚሊዮን በወቅቱ ያልተወራረዳ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ተገኝቷል።

እንደ የፌዴራል መ/ቤቶች የሂሳብ አያያዝ መመሪያ መሰረት የተሰብሳቢ ሂሳብ በቂ ማስረጃ ሲቀርብበት ብቻ  ነው በተሰብሳቢ ሂሳብነት የሚመዘገበው። የተሰብሳቢ ሂሳብ ክምችት እንዳይኖር ቁጥጥር መደረግ አለበትም ይላል።

ነገር ግን በ15 መስሪያ ቤቶች በጠቅላላው 363.1 ሚሊዮን ማስረጃ ባለመቅረቡ የሂሳቡን ትክክለኝነት ማረጋገጥ አልተቻለም።

የተሰብሰቢ ሂሳቡን ትክክለኝነት ማረጋገጥ ካልተቻለባቸው መስሪያ ቤቶች መካከል ፦

🔴 የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 253.3 ሚሊዮን
🔴 የመንግስት ግዥ አገልግሎት 39.1 ሚሊዮን
🔴 ጤና ሚኒስቴር 28 ሚሊዮን ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia