TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀዋሳ

በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የደኢህዴን አመራሮች ክልል አቀፍ ጉባኤ ዛሬ እንዲቀጥል ሙከራ የተደረገ ቢሆንም፣ ከመሰብሰቢያ አዳራሹ ፊት ለፊት በተነሳ #ተቃውሞ ጉባኤው ሳይደረግ ቀርቷል።

በከተማው ውስጥ ወጣቶች ተደራጅተው የተሰቀሉ የደቡብ ክልል #ባንዲራዎችን ሲያወርዱ እንደተመለከቱ የአይን እማኞች ነገርውናል። (ከሀዋሳ በተጨማሪ በአንዳንድ የሲዳማ ዞን ከተሞች በተመሳሳይ የደቡብ ክልልን ባንዲራ የማውረድ እንቅስቃሴ ታይቷል)

በትላንትናው ዕለት የሲዳማ ብሔር ተወላጅ የደኢህዴን አመራሮች ለመወያያ ቀርቧል በተባለ ሰነድ ሳቢያ ስብሰባውን ረግጠው እንደወጡ ይታወቃል።

ከተማውን ተዘዋውሮ የተመለከተው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል (W) በአሁን ሰዓት ምንም የፀጥታ መደፍረስ እንደማይስተዋል ገልፆል።

@tsegabwolde @tikvahethiopua