TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በጎመን ተጠቅልሎ የተያዘው የጥይት ካዝና !

በሀገራችን በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ከተሞች እና ቦታዎች ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች፣ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ይሰማል።

ህገወጥ የጦር መሳሪያ ለጥፋት ዓላማ የሚውል ሲሆን በተለይ በዚህ ድርጊት ውስጥ ያሉ አካላት መሳሪያውን ለማዘዋወር የተለያዩ መንገዶችን ሲጠቀሙ ይስተዋላል።

ከዚህ በፊት በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ከተሰሙት መካከል #በምግብ_እህል_ውስጥ ጥይት በመቅላቀል ለማዘዋወር ሲሞከር፣ በመኪና በሮች ላይ ሻግ በማድረግ ለማሳለፍ ሲሞከር፣ በኩርሲ ወንበር ውስጥ በመደበቅ ለማሳለፍ ሲሞከር ... ብዙ ብዙ ነው ተይዘው ታይተዋል።

ትላንትና ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ በሰማነው መረጃ በከተማው ማናኸሪያ 60 የጥይት ካዝና በጎመን ተጠቅልሎ ለጥፋት ዓለማ በህገወጥ መንገድ ለማዘዋወር ሲሞከር በህበረተሰብ ጥቆማ ተይዟል።

ከጠዋቱ 5 ሰዓት አከባቢ ከሲዳማ ክልል ፤ ጩኮ አከባቢ የተነሳ አንድ ግለሰብ #በ3_እስር_ጎመን ውስጥ በመደበቅ ለጥፋት አካላት ሊደርሰው የነበረ 60 የጥይት ካርታ በቁጥጥር ስር መዋል መቻሉን ፤ መዳረሻውም ያቤሎ እንደነበር ያገኘነውም መረጃ ያሳያል።

የህገወጥ ጦር መሳሪያ ዝውውር በተለያየ መንገድ እየተፈፀመ የሚገኝ በመሆኑ የደህንነት አካላት የተጠናከረ ፍተሻ እንዲሁም ህብረተሰቡ መሰል ድርጊቶችን በመጠቆም ተባባሪ መሆን ሲችል የህገወጥ መሳሪያ አዘዋዋሪዎችን ድርጊት በእጅጉ መቀነስ ፤ የሁሉንም ዜጋ ደህንነት ማረጋገጥ ይቻላል።

ፎቶ ፦ አስቹ (ከቡሌሆራ Tikvah Family) እና የቡሌ ሆራ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia