TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba #ጋብቻ #ፍቺ #ልደት #ሞት

በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት አፈፃፀም ከባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ቁጥር የላቀ የኩነት እና የዲጂታል ምዘገባ መመዝገቡን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ኤጀንሲው ፤ ከ393 ሺህ በላይ የዲጂታል ምዝገባ እና ከ210 ሺህ በላይ የኩነት ምዘገባ መደረጉን ነው የገለጸው።

ከተመዘገበው ጠቅላላ ኩነት ፦

181 ሺ 983 ልደት፣
16,933 ጋብቻ፣
2,813 ፍቺ
8,761 ሞት ሲሆን ከዚህም ውስጥ በአንድ ዓመት ገደብ ውስጥ የተመዘገበው ፦
* አዲስ ጋብቻ 5,171
* በፍርድ ቤት በተከናወነ በአንድ ዓመት ግዜ ውስጥ የተመዘገበ ፍቺ 1,296
* ሞት 2,312 መሆኑ ታውቋል።

ከ2015 ዓመት በንፅፅር ሲታይ ፦ አዲስ ልደት በ65%፣ ፍቺ በ106.7% እንዲሁም ሞት በ25.29% ጭማሪ ብልጫ ያሳየ ሲሆን ጋብቻ በ5% የቀነሰ መሆኑ ተገምግሟል።

በነዋሪነት አገልግሎት ዘርፍ ለ393,303 ነዋሪዎች በአዲስ፣ በምትክ፣ በእርማት እና በእድሳት የመታወቂያ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን 311 ሺ 446 (93%) የዲጂታል  መታወቂያ መሆኑ በአፈፃፀሙ የተሻለ አድርጓታል።

በተጨማሪም በዚሁ ዘርፍ 76,299 የያላገባ  ማስረጃ እንዲሁም 15,369 የመሸኛ (Clearance ) አገልግሎት በከተማዋ ተሰጥቷል።

ከተመዘገበው ኩነት ትንተና በዕድሜ ሲታይ ፦

ልደት
6% ከ1 ዓመት በታች፣
28% ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት፣
26% ከ6 ዓመት እስከ 17 ዓመት እንዲሁም
40% ከ17 ዓመት በላይ መሆናቸው ትንተናው ያመላክታል፡፡

ጋብቻ
72.8% የሚሆነው ተገቢ ከ18 - 40 ዓመት
27.2% የሚሆነው ከ41 በላይ መሆኑ ትንተናው አሳይቷል።

ሞት
0.01% ከተወለደ ከ28 ቀን እስከ 1 ዓመት የተከሰተ ሞት፣
0.6% ከተወለደ ከ2 ዓመት እስከ 17 ዓመት የሞተ፣
22.9% ከተወለደ  ከ18 ዓመት እስከ 40 ዓመት የሞተ፣
28.5% ከተወለደ ከ41 ዓመት እስከ 60 ዓመት የሞተ፣
35% ከተወለደ 61 ዓመት እስከ 80 ዓመት የሞተ፣
12% ከተወለደ 81 ዓመት እስከ 100 ዓመት የሞተ፣
0.9% ከተወለደ ከ100 ዓመት በላይ የሞተ መሆናቸው ያመላክታል፡፡ 

በስድስት ወራት አፈፃፀም በከተማው የዲጂታል ምዝገባ እና ልደት ምዝገባ የተሻለ አፈፃፀም የታየባቸው መሆኑ ተነግሯል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ምንም እንኳን የተሻለ አፈፃፀም ቢኖርም ፤ አገልግሎቱን በጥራት ከመስጠት አንፃር የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን ከአፈፃፀሙ እኩል ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የቀሪ ወራት አቅጣጫ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia