TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Gambella የጋምቤላ ክልል ፤ ጋምቤላ ከተማን ማረጋጋት መቻሉን አሳወቀ። ክልሉ ፥ " ተኩስ ከፍተው በነበሩ የሸኔና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ላይ በፀጥታ አካላት በተወሰደ ጠንካራ እርምጃ ከተማዉን ማረጋጋት ተችሏል " ሲል አሳውቋል። አክሎም በተወሰደዉ እርምጃ በታጣቂ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ሰበአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሷል ሲል አመልክቷል። ክልሉ የከተማው ህብረተሰብ ከቤት ባለመውጣት ለፀጥታ…
#Update #Gambella

የጋምቤላ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ገለፁ።

ፕሬዝዳንቱ ይህን የገለፁት የከተማውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

" በክልሉ የሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች ባካሄዱት ቅንጅታዊ ማጥቃት ከተማውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል " ያሉት አቶ ኡሞድ " በጥቃቱ በጠላት በኩል ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሷል ፤ ከወገን ጦር በኩልም መጠነኛ ጉዳት ደርሷል " ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ኡሞድ ፤ በጋምቤላ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን ገልፀው በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የርዕሰ መስተዳድሩን ጽህፈት ቤት ተቆጣጥረዋል [ ታጣቂዎቹን ማለታቸው ነው ] በሚል የተናፈሰው ወሬ #ሀሰተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል።

" ነዋሪዎች በአሁኑ ሰዓት በከተማው በአንዳንድ አካባቢ ተደብቆ የሚገኝ የጠላት ሀይል ካለ በአቅራቢያቸው ለሚገኝ የፀጥታ ሀይል ጥቆማ ይስጡ " ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ በተለይም #ከምሽቱ_2_ሰዓት ጀምሮ በቤቱ በመቀመጥ ለሠላሙ ተባባሪ መሆን ይኖርበታልም ብለዋል።

የጋምቤላ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ " በጥቃቱ ህይወታቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባቸው አካላት በክልሉ መንግስት እና ህዝብ ስም መጽናናትን እመኛለሁ " ማለታቸውን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬተሪያት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia