TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GERD

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 3ኛ ዙር ሙሌት ከመጪው ሐምሌ ወር አንስቶ መከናወን እንደሚጀምር አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልወደዱ የግድቡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊን ዋቢ አድርጎ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ ወደ ግድቡ የሚፈሰው የውኃ መጠን ከሰኔ አጋማሽ ጀምሮ ከፍ እያለ ከሄደ በኋላ ወደ ግድቡ የሚገባውን ውኃ በመያዝ በሐምሌ ወር ሙሌቱ ይጀመራል ብለዋል ኃላፊው።

በዚህ ዓመት ወደ ግድቡ እንዲገባ የሚጠበቀውን የውኃ መጠን ለመያዝ የግድቡን ቁመት የመጨመር ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ገልፀዋል። የውኃ ሙሌቱ ሲጀመር የግድቡ ቁመት በሚፈለገው መጠን እንደሚደርስ አስረድተዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት በሰኔ ወር መጨረሻ ሲጀመር በነሐሴ ወር አጋማሽ እንደሚጠናቀቅ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ በዓመቱ በነበረው ከፍተኛ መጠን ያለው የዝናብ ፍሰት የተነሳ መጠናቀቁ የተበሰረው ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ነበር።

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ፦ " ወልድያ ገብርኤል በእሳት እየተቃጠለ ነው የሚለው መረጃ የተዛባ መረጃ ነው። ከማንም ይምጣ ተራራ በሰተሰሜን አቅጣጫ አባው ተራራ አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል። የአካባቢው መኅበረሰብ እና የጸጥታ አካሉ እሳቱ ቃጠሎው እንዳይስፋፋ የማድረግና የማጥፋት ስራ በመስራት ይገኛል። ሆኖም ወልድያ ገብርኤል በእሳት እየተቃጠለ ነው የሚለው መረጃ የተዛባ መረጃ ነው። በተራራው…
#Update #Woldia

ፖሊስ ደን በማቃጠል ተሳትፈዋል ያላቸውን 59 ሰዎችን በሕግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

ታሪካዊውንና ጥንታዊውን የምንም ይምጣ የተራራ ደንን በእሳት በማቃጠል ተሳትፈዋል ያላቸውን 59 ሰዎችን የወልድያ ከተማ ፖሊስ በሕግ ቁጥጥር ስር አውሏል።

ትላንት የወልድያ ከተማ መስራች የታላቁ ራስ ዓሊ ቤተ መንግሥት የነበረበት አካባቢ ደን ለቃጠሎ የተዳረገ ሲሆን አጥፊዎቹ በአቀዱት ልክ ወደ ሌላ አካባቢ ሳይዛመት በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

ከተማ አስተዳደሩ ቃጠሎው ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይዛመት ላደረጉ ሁሉም የጸጥታ አካላት እና የአካባቢው ነዋሪዎች ምስጋና አቅርቧል።

ምንጭ፦ ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን

@tikvahethiopia
#Burji

በንፁሀን ገበያተኞች ላይ በተፈፀመ ጥቃት በርካቶች ተገደሉ።

በቡርጂ ልዩ ወረዳ በ " ሶያማ ቡርጂ " ገቢያ ለመሸጥ በወጡ ንጹሐን ዜጎች ላይ በተፈጸመ አሰቃቂ ጥቃት የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ሱሮ ቡርጉዳ ወረዳ አስታውቋል።

ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ሰዎች ገበያተኞች እንደሆኑና ወደ ቡርጂ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ '' የዚህን ሀገር ሰላም መረጋጋት በማይወዱ የ2ቱን ህዝቦች አንድነት በማይፈልጉ '' ባላቸው ሰዎች መፈጸሙን ወረዳው አስታውቋል።

በጥቃቱ እስካሁን ህይወታቸው እንዳለፈ ከተገለጸው 9 ሰዎች በተጨማሪ በ21 ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶ በቡሌ ሆራ ሆስፒታል እና በሶሮቲ ጤና ጣቢያ ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል ብሏል።

ወረዳው '' በዚህ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ህዝባችን ላይ በተፈጸመው ድርጊት ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች በፍጥነት ተጣርቶ በህግ ሊጠይቁ ይገባል '' ያለ ሲሆን ሲሆን ህዝቡም ጉዳዩን በማስተዋልና በመረጋጋት እንዲከተተልና የህግ የበላይነት እንዲከበር የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቋል።

የቡርጂ ልዩ ወረዳም ባወጣው ሀዘን መግለጫ ጥቃቱ መፈጸሙን ገልጿል።

'' የሸኔ ኦነግ እና የአጀንዳቸው ተሸካሚዎች አገራችንን የመበታተን አጀንዳ አንግበው በሕዝቦች መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር በአዋሳኝ አከባቢዎች በቡርጂ አርሶ አደሮች እንድሁም ሰላማዊ የጉጂ አርብቶ አደሮች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት ቢያደርሱም ሰላም ወዳዱ ሕዝባችን እስካሁን ሰላሙን ጠብቆ ቆይቷል፡፡ '' ሲል መግለጫው ይጠቅሳል።

የትላንት ( 27/09/2014 ዓ.ም) ጥቃት '' የፀረ ሰላም ኃይሉ በማሳቸው በነበሩ አርሶ አደሮች ላይ ጥቃትና ግዲያ በመፈፀሙ ምክንያት የቡርጂን ባሕል እና ዕሴት በፍጹም በማይወክል አግባብ የሰላም መኖር የሚያንገሸግሻቸው ጥቅት ቡድኖች በገበያተኞች ላይ ላይ አሰቃቂ ግዲያ እና ጉዳት አድርሰዋል፡፡'' ብሏል።

ጥቃቱ ታስቦ በነበረበት ልክ እና መጠን ቢሆን ኖሮ አሁን ከደረሰው በላይ ጉዳት ልደርስ ይችል ነበር ያለው መግለጫው '' አብዛኛው ሕዝባችን ሰላም ወዳድነቱን በተግባር በማሳየት ወንድም ሕዝብ የሆነውን የጉጂ ሕዝብ ሸሽጎ በጉያው አቆይቶ ሸኝቷል '' ሲል ጠቅሷል።

እስካሁን ድረስ ንፁሃንን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደሉ አካላት ስለመያዛቸው የተገለፀ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
#Monkeypox #እንድናውቀው

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) በተለያዩ ሀገራት እየተሰራጨ ነው። ጎረቤት ኬንያም ከዚህ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪ አግኝታ ናሙናዎችን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሴኔጋል ልካለች።

ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር በተያያዘ ማወቅ ያለብን ጉዳዮች ፦

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው ?

በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዙ ሰዎች መጀመሪያ ላይ ሙቀት፣ራስ ምታት፣ የጀርባ ሕመም፣ የጡንቻ ሕመም፣ የሰውነት ማበጥ እና በማንኛውም ነገር ላይ ፍላጎት ማጣት ይታይባቸዋል።

ሙቀቱ ጋብ ሲል ሰውነት ከፊት ጀምሮ ማሳከክ ይጀምራል። መላው ሰውነትን ቢያሳክክም ክንድና እግር የበለጠ ያሳክካሉ።

የሚከሰተው እከክ በጣም የሚያምና በተለያየ ደረጃ የሚያልፍ ነው።

ቆዳ ላይ የሚከሰተው እብጠት ኋላ ላይ ቆዳ እንዲቆስልና እንዲረግፍም ያደርል። ጠባሳ ጥሎም ሊያልፍ ይችላል። ሕመሙ በራሱ ጊዜ የሚጠፋ ሲሆን ከ14 - 21 ቀናት ይወስድበታል።

በሽታው እንዴት ይይዛል ?

በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ሰዎች ተጋላጭ ናቸው። በቆዳችን ክፍተቶች በኩል፣በዓይን፣ በአፍንጫ ወይም በአፍ በኩል ቫይረሱ ወደ ሰውነታች ይገባል።

በወሲብ ወቅት ባለ ንክኪም ቫይረሱ ይተላለፋል።

በቫይረሱ ከተያዙ ዝንጀሮዎች፣ አይጦች ወይም ሌሎች እንስሳት ጋር ንክኪ ከተደረገ ቫይረሱ ወደሰው ይተላለፋል። ቫይረሱ በልብስ/በሌሎች ንክኪ ባላቸው ጨርቆች በኩል ይተላለፋል።

ምን ያህል አስጊ ነው ?

አብዛኞቹ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ለከፋ ሕመም አይዳረጉም።

ልክእንደ ፈንጣጣ በተወሰኑ ሳምንታት ውስጥ ይጠፋል። ሆኖም ግን በሽታው ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስም ይችላል።

በምዕራብ አፍሪካ በበሽታው ሳቢያ የሞቱ ሰዎች አሉ።

ሕክምና አለው ?

ሕክምና የለውም። ስርጭቱን ግን መቆጣጠር ይቻላል።

Via BBC/WHO

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ ፦

#ሳዑዲ_አረቢያ ፦ ሳዑዲ አረቢያ የሃጅ ተጓዦችን እየተቀበለች ትገኛለች። ከቀናት በፊት የመጀመሪያው የሃጅ ተጓዦች ቡድን ከኢንዶኔዥያ ወደ ሳዑዲ መግባቱ ይታወሳል። ዛሬ ባገኘነው መረጃ እስከ ትላንት እሁድ ድረስ ከተለያዩ ሀገራት ለሃጅ ጉዞ ሳዑዲ የገቡ ተጓዦች 955 ደርሰዋል። ሳዑዲ አረቢያ ዘንድሮ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ 1 ሚሊዮን የሃጅ ተጓዦችን እንደምታስተናግድ ይታወቃል።

#ጀርመን ፦ የጀርመኑ መኪና አምራች ኩባንያ መርሴዲስ-ቤንዝ 1 ሚሊዮን ገደማ አሮጌ መኪናዎችን ለጥገና ጠርቷል። ኩባንያው እኚህ መኪናዎች ፍሬናቸው ችግር አለባቸውና ጠግኜ ልመልስላችሁ ብሏል። ኩባንያው መኪኖቹ ከፍተኛ በሆነ ዝገት ምክንያት የፍሬን ሰርዓታቸው ተገቢውን ሥራ ላይሰራ ይችላል ብሏል። ጀርመን ያሉ 70 ሺህ መኪናዎችን ጨምሮ ከ993 ሺህ በላይ መኪናዎች መጠገን አለባቸው።

#UK ፦ ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመርያ ጊዜ ኤም 270 የተባሉ ረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ለዩክሬን ልትሰጥ ነው። እነዚህን እጅግ ዘመናዊ ሮኬት ማስወንጨፍያ መሣሪያዎች መቼ እና በምን ያህል መጠን ወደ ዩክሬን እንደምትልክ አልገለጸችም።

#ሩስያ ፦ የሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአሜሪካ ማስጠንቀቂያ ልከዋል። ሀገሪቱ ለዩክሬን የጦር መሣሪያ ልገሳ እንድታቆም ያስጠነቀቁ ሲሆን ይህ የማይሆን ከሆነ ሩሲያ በዩክሬን የምታደርሰው ጥቃት መጠኑ እየሰፋ እንደሚመጣ ገልፀዋል። አሜሪካ ባለፈው ሳምንት ዘመናዊ ተወንጫፊ ሚሳኤል ሲስተምን ወደ ዩክሬን ልካለች። አሜሪካ መሣሪያውን ብትሰጥም ዩክሬን ይህን መሣሪያ ወደ ሩሲያ ግዛት እንዳትተኩስ አሳስባ ነው።

#ቢቢሲ #ሳዑዲጋዜቴ #ኤፒ

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#USA

ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ በአሜሪካ የተለያዩ ከተሞች በተከፈቱ ተኩሶች እና ጥቃቶች 9 ሰዎች ሲገደሉ ፤ በርካቶች ቆስለዋል።

1. ቅዳሜ ምሽት በርካታ ሰዎች በሚበዙበት በፊላደልፊያ ሳውዝ ስትሪት ላይ መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች ተኩስ ከፍተው 3 ሰዎች ሲሞቱ ከ10 በላይ ሰዎች በጥይት ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል።

2. ቅዳሜ ከእኩለ ሌሊት በኋላ በቻታኖጋ፣ ቴነሲ ውስጥ በሚገኝ ባር አቅራቢያ ተኩስ ተከፍቶ 3 ሰዎች ሲሞቱ 14 ቆስለዋል።

3. በእሁድ ረፋድ ላይ በሳጊናው ሚቺጋን በነበረ የተኩስ እሩምታ 3 ሰዎች ሲገደሉ ሁለቱ ቆስለዋል። ፖሊስ አምስቱም ሰዎች በድርጊቱ የተሳተፉ መሆናቸውን አመልክቷል።

(እስከ ትላንት ድረስ ከሁሉም ጥቃቶች ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋለ የለም)

4. ባለፈው ረቡዕ ዕለት በኦክላሆማ ቅዱስ ፍራንሲስ ሆስፒታል ' አላዳነኝም ' በሚል አንድ ታጣቂ በከፈተው ተኩስ ቀዶ ጥገና ያደረገለትን ጨምሮ 3 ሀኪሞችን ገድሏል። ተጠርጣሪው ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ራሱን በጥይት ማጥፋቱ ነው የተገለጸው፡፡ ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ ወደ ሆስፒታሉ ሲገባ ኤአር-15 የተሰኘ ጠብመንጃ እና ሽጉጥ ይዞ እንደነበር ፖሊስ አረጋግጧል።

እንደ Gun Violence Archive ድረገፅ መረጃ በአሜሪካ ሀገር ከጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ (በመሳሪያ እራሳቸውን የሚያጠፉትን ጨምሮ) በየዓመቱ 40,000 ሰዎች ይሞታሉ።

ቪድዮ ፦ ፊላደልፊያ (Jack Posobiec)

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ፦

" ምናባዊ ንብረትን (ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ) ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ያልተሰጠው ድርጊት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ሕገ-ወጥ ተግባር እራሱን ይጠብቅ።

የኢትዮጵያ የገንዘብ መደብ ብር እንደሆነና በብሔራዊ ባንክ በሌላ አኳኋን ካልተፈቀደ በስተቀር በሀገሪቱ የሚከናወኑ ማናቸውም የገንዘብ ግንኙነቶች ሁሉ የሚከፈሉት በብር እንደሚሆን የብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 በግልጽ ይደነግጋል።

በተጨማሪም በክፍያ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 718/2003 መሠረት በየትኛውም የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድም ሆነ ሥርዓት ያለ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የገንዘብ ዝውውርም ሆነ ገንዘብ ነክ አገልግሎት መስጠት አይቻልም፡፡

ነገር ግን ከጥናት ለመረዳት እንደተቻለው በአሁኑ ወቅት ከህግ እውቅና ውጪ የክሪፕቶ ከረንሲ፣ እንደ ቢትኮይን እና የመሳሰሉት የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ አገልግሎት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ መጥቷል።

በተጨማሪም ይህ ተግባር ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ውጪ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር የሚደረግበት እና በተለይ በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

ይህ እየተስተዋለ ያለው የዲጂታል መገበያያ ገንዘብን ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ያልተሰጠው ድርጊት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ሕገ-ወጥ ተግባር እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል።

ይህን ፈጽመው በሚገኙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ሲሆን ህብረተሰቡ ይህንን ህገወጥ ተግባር የሚሠሩ አካላትን ሲመለከት ለብሔራዊ ባንክ እና ለሚመለከታቸው ሕግ አስከባሪ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባለን ። "

#የኢትዮጵያ_ብሄራዊ_ባንክ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ። በምስራቅ ሐረርጌ ዞን " ቀርሳ ወረዳ " ከቀኑ 8፡30 አካባቢ የጭነት አይሱዙ ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ አለፈ። የዞኑ ፖሊስ መምሪያን ዋቢ አድርጎ ኤፍ ቢሲ እንደዘገበው ፤ አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ሲሚንቶ ጭኖ እየተጓዘ ባለበት ወቅት ቀርሳ ከተማ ሲደርስ ፍሬን አልታዘዝ ብሎት ወደገበያ በመሄድ…
#Update

በቀርሳ ወረዳው የትራፊክ አደጋ የሟቾች ቁጥር 16 ደርሷል።

ከትላንት በስቲያ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን " ቀርሳ ወረዳ " የጭነት አይሱዙ ተሽከርካሪ ወደገበያ በሚሄዱ መንገደኞች ላይ ባደረሰው አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉና በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ድሬደዋ ተልከው ህክምና እየተደረገላቸው እንደነበር መገለጹ ይታወሳል።

በአደጋው ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ከነበሩ ሰዎች መካከል የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል። ይህም የሟቾችን ቁጥር 16 አድርሶታል።

የአደጋ መንስኤ ከፍጥነት ወሠን በላይ ማሽከርከርና ፍሬ ለመያዝ አለመቻል እንደነበር መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

Be A Legend!

Pay with your BoA Visa card like Drogba!

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
TIKVAH-ETHIOPIA
#Burji በንፁሀን ገበያተኞች ላይ በተፈፀመ ጥቃት በርካቶች ተገደሉ። በቡርጂ ልዩ ወረዳ በ " ሶያማ ቡርጂ " ገቢያ ለመሸጥ በወጡ ንጹሐን ዜጎች ላይ በተፈጸመ አሰቃቂ ጥቃት የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ሱሮ ቡርጉዳ ወረዳ አስታውቋል። ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ሰዎች ገበያተኞች እንደሆኑና ወደ ቡርጂ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ '' የዚህን ሀገር ሰላም መረጋጋት በማይወዱ የ2ቱን…
#Update

ዛሬ በደቡብ ክልል ቡርጂ ቅዳሜ የተፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ የሚያወግዝ ሰልፍ መደረጉ ተሰምቷል።

የቡርጂ ልዩ ወረዳ ፤ " የቡርጂ ህዝብ በጉጂ ወንድምህዝቦች ላይ የተደረገውን የግፍ ግድያ በሠላማዊ ሠልፍ አወገዙ " ሲል አሳውቋል።

በሠልፉ ሁሉም የህብረተሰብ አካላት መገኘታቸውን ነው ያመለከተው።

ባለፈው ቅዳሜ በቡርጂ ልዩ ወረዳ በ " ሶያማ ቡርጂ " ገቢያ ለመሸጥ በወጡ ንጹሐን ዜጎች ላይ በተፈጸመ አሰቃቂ ጥቃት 9 ሰዎች ሲገደሉ 21 ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል።

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ሱሮ ቡርጉዳ ወረዳ '' ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ህዝባችን ላይ በተፈጸመው ድርጊት ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች በፍጥነት ተጣርቶ በህግ ሊጠይቁ ይገባል '' ማለቱ ይታወሳል።

የቡርጂ ልዩ ወረዳ የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለሕግ የማቅረብ ሥራዎች መጀመራቸው ዛሬ ያሳወቀ ሲሆን የጥቃቱ ዋና ታሳታፊ የሆኑ ሰዎች እየተለዩ መሆኑንና እስከአሁን 10 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba | የታሪፍ ማማሻያ ሊደረግ ነው።

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሸከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

በመዲናዋ ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች #አዲስ_የትራንስፖርት_ታሪፍ ማሻሻያ ነገ እለተ ማክሰኞ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ለሚዲያ ተቋማት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

የታሪፍ ማሻሻያው ከሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ እንደሆነ ተገጿል።

ህብረተሰቡ ከሰኔ 1 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነውን ትክክለኛ ታሪፍ አውቆ በመክፈልና ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን በማጋለጥ በኩል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በራይድ እና ዛይ ራይድ መካከል ውዝግብ ተነስቷል! በራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት እና ዛይ ራይድ ሜትር ታክሲ መካከል ከንግድ ስም ባለቤትነት እና ከፈጠራ ባለቤትነት መብቶች ጋር በተያያዘ በተነሳው ውዝግብ ራይድ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት በንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ምርመራ ተጀመረ። ከአራት ወራት በፊት ራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት የስያሜው የባለቤትነት መብት ይገባኛል በሚል ለኢትዮጵያ…
#Update

ከዚህ ቀደም በሃይብሪድ ' ራይድ ' እና በ " ዛይራይድ " መካከል ከንግድ ስያሜ ጋር ተያያዞ ውዝግብ መነሳቱን መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።

ይኸው ውዝግብ ወደ ፍርድ ቤትም አምርቶ እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ ግንቦት 29/2014 ዛይራይድ ህጋዊነቱ በፍ/ቤት ውሳኔ እንደተረጋገጠለት ገልጿል።

ድርጅቱ ፤ " ሃይብሪድ ' ራይድ ' የሚለውን የጋራ ቃል ለብቻዬ ካልተጠቀምኩ ብሎ ዛይራይድን ከሶ ባንክ አካውንታችንን ላለፉት 2 አመታት አሳግዶ ነበረ " ብሏል።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት በሰጠው ውሳኔ ዛይራይድ አሸናፊነቱንና ህጋዊነቱን አረጋግጧል ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia