TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ስልክአምባ

" 12 ሰዎች ናቸው የተገደሉት፤ .. ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከብቶችም እየተነዱ ተወስደዋል " - ነዋሪዎች

" 11 ሰዎች ስለመገደላቸው መረጃ ደርሶናል መረጃውን የማጣራት ስራ እየሰራን ነው " - ኢሰመኮ

️በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ስልክ አምባ ከተማ ባለፈው ሠኞ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ በ5 ቀበሌዎች ጥቃት መፈጸሙን ይህን ያደረጉት ደግመ የሸኔ ታጣቂዎች (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት) እንደሆኑ ገልጸዋል።

ከሟቾች አብዛኛዎቹ የአማራ ብሔር ተወላጆች መኾናቸውን ተናግረዋል።

ወደ 60 ቤት እህል ጭምር የያዘ መቃጠሉን እና በርካቶች ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሸሻቸውን ገልጸዋል። ከ100 በላይ ከብቶችም እየተነዱ ተወስደዋል።

አንድ ነዋሪ በሰጡት ቃል ፥ ጥቃቱ ከተፈፀመ በኃላ ዘግይተው የደረሱት የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከታጣቂዎቹ ጋር ተኩስ ገጥመው እንደነበር አስረድተዋል።

ሌላ ነዋሪ ፤ " ኦነግ ሸኔ ነው የሚባለው ቁጥራቸው የበዛና ከባድ መሳሪያ ጭምር የታጠቁ ናቸው በተኛንበት 12 ሰዓት ላይ መጥተው ነው ጉዳት ያደረሱት " ብለዋል።

" እኛ ገበሬዎች ነን ምንም ኃይል የለን አቅም የለን በጣም ነው ጉዳት የደረሰብን " ያሉ ሲሆን ሴቶችን፣ አዛውንቶችን ከብቶችን በማሸሽ ወደጫካ ማስመለጥ እንደተቻለ አቅም የሌላቸው አዛውንቶች ግን መገደላቸውን እነሱንም ሲቀብሩ እንዳመሹ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፥ በአካባቢው በታጣቂዎች ግጭት ተነስቶ 11 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ከአካባቢው መረጃ እንደደረሰው ገልጾ መረጃውን ለማጣራት ጥረት ላይ መሆኑን አመልክቷል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል በነዋሪዎች የቀረበበትን ክስ አስተባብሎ፤ " እኛ እንዲህ ዓይነት ድርጊት ውስጥ እጃችን የለበትም " ብሏል። " ጉዳዩ በገለልተኛ አካል ምርመራ ሊደረግበት ይገባል " ሲልም ገልጿል።

ክልሉ እስካሁን በይፋ የሰጠው መረጃ የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ስልክአምባ " 12 ሰዎች ናቸው የተገደሉት፤ .. ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከብቶችም እየተነዱ ተወስደዋል " - ነዋሪዎች " 11 ሰዎች ስለመገደላቸው መረጃ ደርሶናል መረጃውን የማጣራት ስራ እየሰራን ነው " - ኢሰመኮ ️በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ስልክ አምባ ከተማ ባለፈው ሠኞ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።…
#ኦሮሚያ #ኖኖ #ስልክአምባ

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ሰርገኞችን ዒላማ ባደረገ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ኮማንድ ፖስት እና ነዋሪዎች ገለጹ።

የኖኖ ወረዳ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል ፥ ጥቃቱ ቅዳሜ ሰኔ 8 ንጋት ላይ ነው የተፈጸመው።

ጥቃት አድራሾቹ " ጽንፈኛ የአማራ ታጣቂዎች  ናቸው " ብለዋል።

ኃላፊው " ሰርገኞቹ ቤት ውስጥ እያሉ በር ዘግተውባቸው ቦምብ ወረወሩባቸው። ቤት ውስጥ ከነበሩት አንድም በሕይወት የወጣ የለም። እዚያው ተቃጥለው አልቀዋል "  ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ ታጣቂዎቹ ሰርግ ቤቱ ላይ ከአንድ በላይ ቦምብ ወርውረው ሙሽሮቹን እና አብረዋቸው የነበሩ ሰዎችን መግደላቸውን ተናግረዋል።

የኮማንድ ፖስት ኃላፊን ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ቃል ፥ በሰርግ ቤት ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የመጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በታጣቂዎቹ የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።

የአካባቢው ነዋሪ የሟቾች ቁጥር ከ30 እስከ 50 ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል።

በጥቃቱ ሙሽሪት እና ሙሽራውን ጨምሮ የሰርጉ ታዳሚዎች የሆኑ ሰዎች በሙሉ ሕይወታቸው ማለፉን ነዋሪው ተናግረዋል።

የወረዳው የኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ፥ " በእሳት ተቃጥለው የሞቱ ሰዎችን ቁጥር መለየት አስቸጋሪ በመሆኑ ትክክለኛውን የሟቾች ቁጥር መለየት አልተቻለም " ሲሉ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ በዚህ ወረዳ በ5 ቀበሌዎች በተፈጸመ ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ፤ ቤቶች መቃጠላቸውን ፣ ከብቶችም እየተነዱ መወሰዳቸውን ነዋሪዎች መግለጻቸው ይታወሳል።

ኢሰመኮም መረጃውን የማጣራት ስራ እየሰራ እንደነበር መግለጹ አይዘነጋም።

ከሟቾች አብዛኛዎቹ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንደነበሩ ፤ ጥቃት ፈጻሚዎችም የ " ሸኔ (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት) ታጣቂዎች " እንደሆኑ ነዋሪዎች መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia