#OLF50
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የ50ኛ ዓመቱን ለማክበር ዝግጅት ላይ ይገኛል።
ኦነግ ፤ እኤአ 1973 ሐምሌ 01 የተመሰረተ ሲሆን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች በአንጋፋነቱ ይጠቀሳል።
ድርጅቱ 50ኛ ዓመቱን በአገር ውስጥና በተለያዩ አገራት በድምቀት ለማክበር ማቀዱን አሳውቋል።
ይህንን የ50ኛ ዓመት ክብረ በዓል አስመልክቶ ከቀናት በፊት ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚህ ወቅት አቶ ዳውድ ኢብሳ ፤ በፓርቲው የትግል ሂደት ውስጥ የተሰው ጓዶቻቸውን አስታውሰው አመስግነውአቸዋል፡፡
ስለወቅታዊ አገራዊ ፖለቲካ እና የፓርቲያቸው ይዞታ ማብራሪያም ሰጥተዋል። ለአሁናዊው በተለይም የኦሮሚያ አለመረጋጋት መነሻ ያሉትንም ሃሳብ አስቀምጠዋል፡፡
አቶ ዳውድ ምን አሉ ?
" በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና የኢትዮጵያ መንግስት መካከል በእኤአ ነሐሴ 07 ቀን 2018 ሰምምነት ተደርሶ ነበር፡፡
በዚህ ስምምነት መሰረት ጦርነት ቆሞ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ) በህዝቡ መሃል ሆኖ በነጻነት የፖለቲካ እንቅስቃሴውን እንዲያከናውን፤ ለዚህም ሙሉ መብት አለው የሚል ነበር፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ ለኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ተመሳሳይ ነገር እንደሚፈቅድ ነው የተስማማው፡፡ የስምምነታችን አስኳሉ ይህ ነው፡፡
ከዚህ ጋር የተያያዙ የሰራዊታችንና ሰላም ጉዳይም በስምምነቱ ውስጥ ነበር፡፡
አሁን ላይ ይህ መከዳቱ ነው ላለፉት አምስት (5) ዓመታት በኦሮሚያ የቀጠለውን ጦርነት ያስከተለው፡፡ ለትግራይ ጦርነት እና አሁን በአማራ ክልል እየተስፋፋ ላለውም ቀውስ መሰረት የሆነው።
ስምምነቱ ላይ ተግዳሮት መግጠሙን ተከትሎ ፓርቲያችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ወከባ ደርሷል።
...ስምምነታችንን በመሻር ነው መንግስት በደቡብ እና ምዕራብ እንዲሁም በመሃከለኛው አከባቢ ያሉ የኦነግ ሰራዊት ላይ ትጥቅ ለማስፈታት በሚል ተኩስ የከፈተው፡፡
ይህን በማድረግ ሂደት ውስጥ ሽማግሌዎችም በመሃል ገብተው ፤ የቴክኒክ ኮሚቴ በሚባልም ጥረቶች ሲደረጉ የነበረው፡፡ ያም አልሆነም ጦርነቱ ቀጠለ፡፡ መንግስት በተለያዩ ጊዜያት ይህን ሰራዊት አጠፋዋለው በሚል በተደጋጋሚ መግለጫ ሲያወጣ ነበር፡፡ ያ እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡
ያ ጦርነት ጫካ ብቻ ሳይሆን እዚህ ከተማ ውስጥ የኦነግ ጽ/ቤቶችን በመዝጋትና አመራሮቹን በማሰር የፓርቲውን እንቅስቃሴ በመግታትም ጭምር የተደረገ ነበር፡፡
አሁንም እንደ እኛ እምነት በኦሮሚያ ሰላም የሚሰፍነው መንግስት ከዋናው ባለጉዳይ ከእኛ ጋር ተቀምጦ ያ ስምምነታችን ሲከበር ነው ብለን እናምናለን፡፡ "
Credit : ዶቼ ቨለ
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OLF50
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አለው ?
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ፤ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን አስመልክቶ በሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ አማካኝነት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ወቅት ፓርቲው መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ ስለሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) የታጠቀ ቡድን ጋር ግንኙነት ያለው እንደሆነ ማብራሪያ ሰጥቷል።
አቶ ዳውድ ኢብሳ ምን አሉ ?
" የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር አሁን ላይ ግንኙነት አለው ወይ ለሚለው፤ ያ ሰራዊት የፖለቲካ ጥያቄ ያለው ሰራዊት ነው፡፡
አባላቶቹን ለምን እንደሚታገል አስተምሮ ነው ወደ ጦር የሚያሰማራው፡፡
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ደግሞ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ ይህን ትግል #በሰላማዊ መንገድ እያካሄደ ነው፡፡
ይህ መንግስት አለመግባባቱ በተፈጠረ ጊዜ ኦነግን ገመድ ውስጥ አስገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን ነው የጠየቀው፡፡ ትጥቅ አልፈታም ያለው ያ ሰራዊት የኔ ነው ወይስ አይደለም እንድንል፡፡
በወቅቱ ከአባገዳዎች ጋር ሆነን በኦሮሞ ባህል ማዕከል ባደረግነው ጉባኤ መንግስት ስምምነቱን አፍርሷል ብለን በማመናችንና ጦሩን ማስገባት ስርዓት ስላለው እኛ በወቅቱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ለአባገዳዎች ሰጥተን ነው ከመሃል የወጣነው፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከጦሩ ጋር ግንኙነት የለውም፡፡
ያን ተከትሎ በምርጫ ቦርድ በሕጋዊ መሰረት ብንንቀሳቀስም ይሄው ቤት ውስጥ እስከመታገት የሚደርስ ጫና ደርሶብናል፡፡ የኦነግ እንቅስቃሴ ግን በተለያየ መንገድ ቀጥሏል እንጂ አይገታም፡፡
አሁንም የምንጠይቀው መንግስት ሰላም እንዲወርድ ተቀምጦ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ግደታውን ይወጣ።
በኦሮሚያ ለሁሉም ዜጋ እኩል ክብር እንዲሰጥና መከባበር እንዲሰፍን እንጠይቅላለን። "