TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አይ ኤስ አይ ኤስ 700 የሚደርሱ #የአሜሪካ እና #የአውሮፓ ሀገራት ዜግነት ያላቸውን ሰዎች በሶሪያ አግቷል፡፡ ከታጋቾቹ ውስጥም 10 የሚደርሱትን እንደገደላቸው ታውቋል፡፡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአካባቢው ያለውን የአሜሪካ ጦር ‹‹አስፈሪ ውድቀት›› ሲሉ ተችተውታል፡፡

ምንጭ፦ አር ቲ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሜሪካ

#የአሜሪካ_መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎቹ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ ስለተጠራ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፏል።
-----------------------------------------------
የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቷል የሚለውን መረጃ ከየት እንደተገኘ ባይታወቅም የከተማ አስተዳደሩ ወይም የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እውቅና የሰጠው ሰልፍ ግን የለም።
-----------------------------------------------
ነገር ግን "ለአዲስ አበባ ምን ይደረግ?" በሚል በባልደራስ አዳራሽ ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር ህዝባዊ ውይይት እንደሚደረግ ለማውቅ ችያለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በነገራችን ላይ...

ዛሬ #በተከሰከሰው አውሮፕላን ህይወታቸውን ካጡ ዜጎች መካከል 8 #የአሜሪካ_ዜጎች ይገኙበታል። በማህበራዊ ሚዲያ አሜሪካ ሆን ብላ ዜጎቿን #አስቀርታለች፤ ምንም የአሜሪካ ዜጋ አልሞተም እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ መሰረተቢስ ነው።

ፎቶ፦ ከቢቢሲ እና ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሀይቲ ፕሬዝዳንት ተገደሉ። የሀይቲው ፕሬዝዳንት ጆቭኔል ሞይስ ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ በግል መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ መገደላቸው ተሰማ። የፕሬዜዳንቱ ባለቤት ጉዳት ደርሶባቸዋል። - ፕሬዚዳንቱ የተገደሉት መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነው። - የፕሬዜዳንቱን ግድያ ያሳወቁት የሀገሪቱ ጊዜያዊ ጠ/ሚ ናቸው። - በሀገሪቱ የፖለቲካ አለመረጋጋት ፣ ከ2018 ጀምሮ ደግሞ በሙስና መበራከት ስልጣናቸውን እንዲለቁ የሚጠይቅ…
የሄይቲውን ፕሬዜዳት ማን ገደላቸው ?

የሄይቲ ፕሬዜዳንት ጆቭኔል ሞይስ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተፈፀመባቸው ጥቃት መገደላቸው መገለፁ ይታወሳል።

ፕሬዝደንቱ የገደሉት 28 አባላት ያሉት ቅጥረኛ የገዳዮች ቡድን መሆኑ የሀገሪቱ ፖሊስ ስለማስታወቁ ቢቢሲ ዘግቧል።

ከእነዚህ መካከል 26ቱ #ኮለምቢያዊያን ናቸው 2ቱ ደግሞ #የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሄይቲያዊያን ናቸው ሲል የሀገሪቱ ፖሊስ ለመገናኛ ብዙሃን አሳውቋል።

2ቱ አሜሪካዊያንን ጨምሮ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ ስምንቱ ደግሞ እየታሰሱ እንደሆነ ተሰምቷል።

በሕይወት ካሉት ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ዋና መዲናዋ ፓርቶፕሪንስ ውስጥ ከፖሊስ ጋር በነበረ የተኩስ ልውውጥ የሞቱ እንዳሉም ታውቋል።

ጥቃቱን ማን እንዳቀደውና ዓላማው ምን እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

ባለፈው ረቡዕ ነው የታጠቁ ሰዎች ወደ ፕሬዝደንት ጆቭኔል ሞይስ መኖሪያ ቤት ገብተው ጥቃት የፈፀሙት።

በጥቃቱ ፕሬዝደንቱ ሲገደሉ ባለቤታቸው ማርቲን ቆስለው ፍሎሪዳ ወደሚገኝ ሆስፒታል ለሕክምና ተወስደው አሁን መልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተሰምቷል።

#BBC

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" የጦር አውሮፕላኖቹ የሩሲያን ድንበር ከመጣስ ተገትተዋል " - የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር

በጥቁር ባህር በኩል #የሩሲያን ድንበር አቋርጠው ሊገቡ የነበሩ #የፈረንሳይ እና #የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች በSU-27 የሩሲያ ጄቶች ተጠልፈው መመለሳቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

እኤአ ታህሳስ 9 የሩሲያ የኤሮስፔስ መቆጣጠሪያ ሲስተም በራሪ አካላት ጥቁር ባህርን አልፈው ወደ ሩሲያ ድንበር እየበረሩ እንደሆነ ማመላከታቸውን ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ተጠቅሷል።

የሩሲያ ኤርክራፍት በረራ ቡድን ወደሩሲያ ድንበር አቅጣጫ ሲበሩ የነበሩት Mirage-2000 ጀትና ከፈረንሳይ አየርና ስፔስ ሃይል የመጣች የፈረንሳይ Rafale ጄት እንዲሁም የአሜሪካ ጦር CL-600 ያሳተፈ የጥናት እንቅስቃሴ ነበር ተብሏል፡፡

የፈረንሳይ KC-135 አውሮፕላን ነዳጅ የምትሞላ እና እጀባ የምታደርግ በጥቁር ባህር ላይ ሲበሩ እንደነበር መግለጫ አመልክቷል፡፡

የጦር ጄቶች አማካኝነት የጦር አውሮፕኖቹ የሩሲያን ድንበር ከመጣስ ተገትተዋል ያለው መግልጫ የሩሲያ ውጊያ ጄቶች የጦር አውፕላኖቹን ከድንበር ወደ ኋላ ከመለሱ በኋላ በሰላም መመለሳቸው ተገልጿል።

መረጃው የአል ዓይን ኒውስ ነው።

ቪድዮ : የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአሜሪካ ወረራ ... የቀድሞ የአሜሪካ መሪ ኢራቅን ለመውረር ትዕዛዝ ከሰጡ ዛሬ እሁድ 20 ዓመት ደፈነ። የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ኢራቅን ለመውረር ትዕዛዝ ከሰጡ ዛሬ 20 ዓመት ሞልቶታል። የዛሬ 20 አመት ጦርነቱ ሲጀመር አስደንጋጭ እና አስፈሪ የቦምብ ጥቃት ዘመቻ ባግዳድን አቀጣጥሏት ነበር። በዚህ ወረራ የአሜሪካ ጦር በስልጣን ላይ የነበረውን የሳዳም ሁሴን መንግስት አፍርሶ ሳዳምን ከስልጣን…
#ኢራቅ

ዛሬ የቀድሞ #የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ቡሽ ኢራቅ ላይ ወረራ እንዲፈፀም ካዘዙ 20 ዓመት የሞላው ሲሆን በወቅቱ ለወራር ምክንያት የተባለው ኢራቅ ውስጥ አለ የተባለው የጅምላ ጨራሽ የጦር መሳሪያ ነው።

ነገር ግን ይህ " አለ " የተባለው የጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አልተገኘም።

እኤአ በ2003 ወረራው ከመፈፀሙ ከወራት በፊት በወቅቱ የኢራቅ ፕሬዜዳንት የነበሩት እና ከወራራው በኃላ #በስቅላት የተገደሉት ሳዳም ሁሴን በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ (መስከረም 19/2002) ላይ እንዲህ ሲሉ ተናግረው ነበር ፦

" ኢራቅ ከኒውክሌር፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል መሳሪያዎች ሁሉ የጸዳች መሆኗን ከዚህ በፊት አውጃለሁ።

#የአሜሪካ_አስተዳደር የመካከለኛው ምስራቅን ዘይት ለመቆጣጠር ኢራቅን ለማጥፋት ይፈልጋል ፤ ይህን ተከትሎ ፖለቲካውን እንዲሁም የመላው ዓለምን የዘይት / ነዳጅ እና የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ይቆጣጠራል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IGAD ዛሬ በኡጋንዳ፣ ኢንቴቤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ይደረጋል። ስብሰባው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው። ሌላው የሱዳን ጦርነት ነው። ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እስካሁን ድረስ በታወቀው ፦ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዜደንት ኢሳሜል ኦማር ጌሌህ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት…
#IGAD

" ... ማንኛውም #ስምምነት ወይም #ዝግጅት በሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት #ፈቃድ መሆን አለበት " - ኢጋድ

የምሥራቅ አፍሪካ ልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ዛሬ ኡጋንዳ ኢንቴቤ ውስጥ አስቸኳይ የመሪዎች ስብሰባውን አድርጎ ነበር።

ይህ አስቸኳይ ስብሰባ የኢጋድ መስራቿ ኢትዮጵያን ጨምሮ የኤርትራ እና የሱዳን መንግሥት ተወካዮች / መሪዎች ባልተገኙበት የተካሄደ ነው።

ስብሰባው ትኩረት ያደረገው ስለ ወቅታዊው የኢትዮጵያ እና ሱማሊያ ግንኙነት ጉዳይ እንዲሁም ስለ ሱዳን ጦርነት ነው።

ከኢጋድ አባል ሀገራት የትኞቹ መሪዎች ተገኙ ?

🇩🇯 የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢማኤል ኦማር ጌሌህ (ስብሰባውን የመሩት እሳቸው ናቸው/ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ናቸው)
🇰🇪 የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ
🇸🇴 የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ
🇸🇸 የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪየር ማያርዲት
🇺🇬 የኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ተገኝተው ነበር።

ሌሎችስ እነማን ተገኙ ?

- የኢጋድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፤
- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ የሱዳን የግል መልዕክተኛ ራምታኔ ላምራ፣
- የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሌድ አልኩራጂ
- የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች / #UAE የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ካሊፋ ሻሂን አል ማራርት
- የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔታ ዌበር፤
- #የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር፤
- የአረብ ሀገራት ሊግ ረዳት ዋና ፀሀፊ ሆሳም ዛኪ
- የኢጋድ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ መሐመድ አብዲ ዋሬ
- የደቡብ ሱዳን የኢጋድ ልዩ መልዕክተኛ እና የሱዳን የሰላም ሂደት የኢጋድ ተወካይ አምባሳደር እስማኤል ዋይስ
- የኢጋድ የቀይ ባህር፣ የኤደን ባህረ ሰላጤ እና የሶማሊያ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር መሀመድ አሊ ጉዮ
- #በቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቱትኩ ኢናም
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ቺክ ኮንዴ ተገኝተው ነበር።

ኢጋድ ከስብሰባው በኃላ ባወጣው መግለጫ ምን አለ ?

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግኙነት መካከል የተፈጠረው ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

በዋነኛ መርህነት የሶማሊያ ሉዓላዊነት ፣ አድነት እና የግዛት አንድነት ሊከበር ይገባል ሲል አረጋግጧል። ማንኛውም ተሳትፎ ይህንን መርህ ባከበረ መልኩ ሊሆን ይገባል ብሏል። ማንኛውም #ስምምነት ወይም #ዝግጅት በሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት #ፈቃድ መሆን አለበት ብሏል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው ያለውን ውጥረት በማርገብ በምትኩ ገንቢ የሆነ ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

ኢትዮጵያ ስብሰባው ላይ ለምን አልተገኘችም ?

ኢትዮጵያ ከዛሬው የአስቸኳይ ስብሰባ ቀደም ብላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል " በተደራራቢ መርሃ ግብር " ምክንያት በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት እንዳማትችል ለጂቡቲ የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ትብብር እና ኢጋድ በድብዳቤ አሳውቃለች።

ኢጋድ ከጠራው ጉባኤ ቀደም በሎ ከተያዘ መርሃ ግብር ጋር የሚጋጭ በመሆኑ እና የተቀመጠውም ጊዜ አጭር በመሆኑ በስብሰባው ላይ መገኘት እንደሚያስቸግራት በዚሁ ደብዳቤ አሳውቃ ነበር።

ነገር ግን " ኢጋድ በሚመራበት ደንብ መሰረት " በተለዋጭ ቀን ለመወያየት ዝግጁ መሆኗን አሳውቃቸዋለች።

(ሙሉ የኢጋድ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ኢራን ለሊቱን እስራኤልን በድሮን ፣ በሚሳኤልና ሮኬቶች ስትደበድብ ከቆየች በኃላ " እስራኤልን የመቅጣቱ ተግባር #ተጠናቋል " ብላለች። እስራኤል ማንኛውም አፀፋዊ ምላሽ ሰጣለሁ ካለች ግን ከአሁኑ እጅግ በጣም የከፋው ቅጣት ይጠብቃታል ሲትል አስጠንቅቃለች። ኢራን የትኛውም ህዝባዊ ይሁን ኢኮኖሚያዊ ዒላማዋች እንዳልነበሯት ዒላማዋ የእስራኤል ወታደራዊ ስፍራዎችና አቅም ላይ እንደነበር ገልጻለች።…
#Update

በኢራን " ኢስፋሃን ከተማ " ዛሬ ማለዳ ፍንዳታዎች የተሰምተው ነበር።

ይህች ከተማ የአገሪቱ አየር ኃይል መቀመጫ ፣ በርካታ ወታደራዊ ተቋማት ያሉባት ናት።

የኢራን መገናኛ ብዙኃን በደፈናው 3 ድሮኖች በኢራን የአየር መከላከያ ሥርዓት ወድመዋል ሲሉ ገልጸዋል።

#የአሜሪካ ባለልስጣናት እስራኤል ቅዳሜ ለተፈጸመባት ጥቃት ኢራን ላይ የሚሳኤል የአጸፋ ጥቃት ፈጽማለች ብለዋል።

የኢራን በይፍ የሰጠችው ማብራሪያ ባይኖርም የተሰማው ፍንዳታ ጥቃትን የማክሸፍ እንደነበር አሁን ላይ ከተማዋ በመደበኛ እንቅስቃሴ እንደምትገኝ ገልጸዋል።

የደረሰ አንዳች ጉዳት እንደሌለ ጠቁመዋል።

በኑክሌር ተቋማት ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን ተነግሯል።

ምንም እንኳን በመገናኛ ብዙሃን እና በአሜሪካ ባለስልጣናት እስራኤል የጸፋ እርምጃ መውሰዷ ቢነገርም ሀገሪቱ እስካሁን በይፋ " ኃላፊነት እወስዳለሁ " አላለችም።

ኢራንም ፥ " እስራኤል ናት ይህንን ያደረገችው ቀጣይ እርምጃዬ ይሄ ነው " የሚል ይፋዊ ቃል አልሰጠችም።

ነገር ግን ጉዳዩ አሁንም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን እንደደቀነ ይገኛል።

ሀገራት ከወዲሁ በእስራኤል ላሉ ዜጎቻቸው ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ናቸው።

ኢራን እስራኤልን ከቀናት በፊት መደብደቧን ተከትሎ እስራኤል የአፀፋ እርምጃ እንደማይቀርላት ተናግራለች።

ኢራንም እስራኤል የአጸፋ እርምጃ እወስዳለሁ ካለች እስከ ዛሬ ጥቅም ላይ ያልዋለ መሳሪያ እንደምትጠቀምና እርምጃዋ ከመጀመሪያው እየከፋ እንደሚሆን አስጠንቅቃለች።

ኢራን ፥ ጦርነቱ እንዲስፋፋ እንደማትፈልግ ነገር ግን ደፍሮ የሚያጠቃት የትኛውም አካል ካለ " እጁን እንቆርጥለታለን " ስትል ነው ከሰሞኑን የዛተችው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #Ethiopia አሜሪካ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ያለቻቸው የፋኖ ኃይሎች " ውይይትን አልቀበልም " ማለታቸውን በመግለጽ ይህ " ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " አለች። ሀገሪቱ ይህን ያለችው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ኢርቪን ማሲንጋ አማካኝነት ነው። አምባሳደሩ ፤ " በአማራ ክልል ውስጥ ውጊያ እያደረጉ የሚገኙት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ኃይሎች ' ውይይትን አንቀበልም…
#የአሜሪካ_አቋም!

" ግጭት የኢትዮጵያውያንን #ስቃይ_ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም " - አሜሪካ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ አሜሪካ ስለ ኢትዮጵያ ያላትን ፖሊሲ በተመለከተ ምን አሉ ?

- በትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት፣ ግጭት አቁመው በንግግር ሰላምን ሊያሰፍኑና የሰብአዊ መብቶችን ማክበር አለባቸው።

- የታጠቁ ቡድኖች ፖለቲካዊ ዓላማዎቻቸውን በአመፅ ለማሳካት እየገፉ ናቸው ፤ መንግስትም ይህን ለመከላከል የሚወስዳቸው ርምጃዎች፣ በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የማይካድ ተጽእኖ አለው። ውይይትን ወደ ጎን ያለው ይህ አካሔድ የመብት ጥሰቶች እንዲቀጥሉ አድርጓል።

- ሰላማዊ ዜጎች፣ በተለያዩ ኀይሎች ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የዘፈቀደ እስራት፣ አስገዳጅ ስወራ፣ ከግጭት ጋራ የተያያዘ ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎችም ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው መሆኑን የሚገልጹ ዘገባዎችን ማየቱ እጅግ ያሳዝናል።

- የተፈጸሙ ጥፋቶች እውነተኛና ግልጽ የሽግግር ፍትሕ ሒደት በተከተለ የተጠያቂነት አሰራር በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል።

- ሽፍታዎች፣ የታጠቁ ቡድኖች፣ አንዳንዴም የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች፤ በህይወት የመኖር፣ የሰብዓዊ ክብርን፣ መከበርን በመሰሉ መብቶች ላይ ያለምንም ተጠያቂነት ጥሰቶች ይፈጽማሉ።

- በጦርነት እና ግጭት ወቅት እንኳ የሰብዓዊ መብቶች ሊረሱ አይገባም።

- ሁሉም ሀገር ራሱን የመከላከል ህጋዊ መብት አለው፤ ሆኖም ሀገራት ራሳቸውን የሚከላከሉበት መንገድ ያለምንም ጥርጥር የወደፊት ግጭቶችን አካሄድ የሚወስን ነው።

- ሀገር የመከላከያ መንገዶቹ በዛሬው እና በወደፊቱ የማህብረሰብ ትስስር ላይ ይበልጡኑ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው።

- የታጠቁ ወገኖች የፖለቲካ ግባቸውን ከውይይት ይልቅ በግጭት ለማሳካት ሲሞክሩ፤ ለሚፈጸሙ በደሎች ሁኔታዎች የተመቻቹ ይሆናሉ።

- በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ታጣቂ ቡድኖች ንግግር / ድርድር አንቀበልም ማለታቸው እራሳቸውን ነው የሚጎዳቸው። በአማራ ያሉ በርካታ ሰዎች " የቆሙለት ዓላማ ፍትሃዊ ነው " የሚል እምነት/አላቸው ይህንኑ መከራከሪያቸውን ከግጭት ይልቅ በውይይት ማቅረብ አለባቸው።

- በአማራ ክልል ውጊያዎች የሚቀጥሉ ከሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች እንዳለው በውጤቱ የሚሰቃዩት ሰላማዊ ሰዎች ናቸው።  

- ህወሓት በኀይል ወሰን ለማስመለስ ከሚደረግ እንቅስቃሴ መቆጠብ አለበት።

- የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ኃይሎች በድርድር ተስፋ ሳይቆርጡ መተማመን ለመገንባት የሰላም ውይይትን ሊቀጥሉ ይገባል።

- ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በውስጣዊ ግጭቶች እየታመሰች ትገኛለች።

- የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን ችግሮች በኀይል ለመፍታት ከሚያደርገው ጥረት መቆጠብ አለበት። በእስር ላይ የሚገኙ ቁልፍ የፖለቲካ ሰዎችን መፍታቱ ጠቃሚ ነው፤ ያን ተፈጻሚ ማድረግ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ውይይት ሊያግዝ ይችላል።

- ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈጸም ይገባል።

- ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች፣ በመላ አገሪቱ አዲስ የሕዝብ መፈናቀልን ጨምሮ ለሰዎች ስቃይ ምክንያት ከመሆን መገታት አለባቸው።

- የታጣቁ ኃይሎች ት/ቤቶችን፣ ጤና ተቋማትንና የውኃ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረግ ማቆም አለባቸው። የተሟላና ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት ሊኖር ይገባል። ይህም ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ማድረግን ይጨምራል።

- ግጭት የኢትዮጵያውያንን ሥቃይ ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም። ውይይት ትኩረት ሊደረግበት ይገባል።

- ምንም እንኳን ፍጹም ሊሆን ባይችልም፣ ሁሉም ወገኖች የአገራዊ ምክክሩን ዕድል ሊጠቀሙበት ይገባል።

#USEmbassyAddisAbaba
#VOA
#EthiopiaInsider

@tikvahethiopia
አምባሳደር ማይክ ሐመር ከነማን ጋር ተገናኙ ?

በአፍሪካ ቀንድ #የአሜሪካ_ልዩ_መልዕክተኛ የሆኑት ማይክ ሐመር ከሰመኑን በኢትዮጵያ ቆይታ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ የመጡት ፦
° የፕሪቶሪያን ስምምነት አፈጻጸም ለመገምገም፤
° በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ግጭቶች በድርድር እልባት እንዲያገኙ ለማድረግ፤
° የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መመርመር አስፈላጊነት ላይ ለመወያየት ነው።

በዚህም ወቅት ፦

- ከፌዴራይል ባለስልጣናት ጋር መክረዋል።

- ከአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ወደ #መቐለ አምርተው ከትግራይ ክልል አመራሮች ጋር መክረዋል።

- ከአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

- ከኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ጋር መክረዋል።

- ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እና ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ጋር  ተወያይተዋል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር የፕሪቶሪያው ግጭትን በዘላቂነት የማስቆም ስምምነት እንዲፈረም ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል የሚባልላቸው የአሜሪካ ባለስልጣን ናቸው።

@tikvahethiopia