TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
አፍሮባሮሜትር ማነው ?

" አፍሮባሮሜትር " የተባለው ተቋም ከሰሞኑን እንዲሁም ከዚህ ቀደም #ኢትዮጵያን የሚመለከቱ የተለያዩ የጥናት ውጤቶችን ይፋ ሲያደርግ ነበር።

ለመሆኑ ይህ ተቋም ማነው ?

አፍሮባሮሜትር የተባለው ተቋም ፤ አፍሪካ ላይ ትኩረት አድርጎ ገለልተኛ የሆኑ የጥናት እና ምርምር ስራዎችን የሚሰራ መንግሥታዊም / ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም እንደሆነ ይገልጻል።

ይህ ተቋም ታማኝ የሆኑ መረጃዎችን በዋናነት በዴሞክራሲ፣ አስተዳደርና የኑሮ ጥራት ላይ በማሰባሰብ የካበተ ልምድ ማፍራቱን ይናገራል።

ተቋሙ ዘጠኝ ዙር ጥናቶችን እኤአ ከ1999 ጀምሮ በ42 ሀገራት ላይ መስራቱን ይገልጻል።

ጥናት የሚካሄደው በዋናነት በገፅ ለገፅ ቃለመጠይቅ መሆኑን የሚያስረዳው ተቋሙ፤ የጥናቱ መረጃ አሰባሰብ ሂደት የጥናቱ ተሳታፊዎች በመረጡት ቋንቋ እንደሆነ ያመለክታል።

ጥናቱ የሚካሄደው ወካይ የሆነ #ናሙና መጠን በመመደብ እንደሆነም ይገልጻል።

ይህ ተቋም ሰሞኑን ኢትዮጵያን በተመለከተ ይፋ ያደረገው ጥናት ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (USAID) በተገኘ ድጋፍ ሲሆን 2400 ቃለመጠይቆችን (ዕድሜያቸው 18ና ከዚያ በላይ የሆናቸውን) በማሳተፍ ያዘጋጀውና መረጃው ከግንቦት 17 እስከ ሰኔ 15 /2015 ዓ/ም የተሰባሰበ ነው።

ይኸው ጥናት የናሙናው መጠን በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰራቱንና ወካይነት ያለው መሆኑን ገልጾ የአስተማማኝነት ደረጃውም 95 በመቶ መሆኑን አስረድቷል።

አፍሮባሮሜትር ከዚህ ቀደም ጥናት ያካሄደው በ2012 ዓ/ም ነበር።

(ሰሞኑን ይፋ የተደረጉት የጥናት ውጤቶች ከላይ የተያያዙት ናቸው)

@tikvahethiopia