TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FDREDefenseForce

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ከግልገል በለስ እስከ አባይ ግድብ የሚደርሠውን መንገድ ስራ ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ዋና መምሪያው 210 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለውን ሶስተኛ ደረጃ የጠጠር መንገድ ወደ ከፍተኛ ደረጃ የጠጠር መንገድ በማሳደግ ነው ስራውን ሰርቶ ያጠናቀቀው።

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶች ሲጓጓዙ በመንገድ ላይ እስከ ሁለት ሳምንት ይቆዩ የነበረ ሲሆን በተከናወነው መንገድ የማሻሻል ጥገና ስራ የግድቡ የግንባታ ግብዓቶች #በአንድ_ቀን ለመድረስ ይችላሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #GERD

" አሁን ላይ በተገኘው አንፃራዊ ሰላም የኮንቮይ ጉዞ ያለምንም ችግር #በአንድ_ቀን መድረስ ችሏል " - ኢ/ር በላቸው ካሳ

የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እየተካሄደ በሚገኝበት ቀጠና በተገኘው ሰላም የግድቡ ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑ ተገልጿል።

የግድቡ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት ኢንጂነር በላቸው ካሳ ፤ " በቀጠናው የተገኘው አስተማማኝ ሰላም የግድቡን የግንባታ ሂደት #እያፋጠነው ይገኛል " ሲሉ አሳውቀዋል።

" የፀጥታው ጉዳይ ለግድቡ ግንባታ መሠረታዊ ፍላጎት መሆኑን በመገንዘብ #የሀገር_መከላከያ_ሰራዊት ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ ተልዕኮውን በጀግንነት በመፈፀም በቀጠናው የከፈለው መስዋዕትነት የኢትዮጵያን ህዝብና መንግስት ያኮራ በታሪክ የሚኖር ነው  " ብለዋል።

ኢ/ር በላቸው፤ በቀጠናው በነበረው የሰላም ችግር ምክንያት ወደ ግድቡ የሚመላለሱ ተሽከርካሪዎች ከሁለትና ከሶስት ቀን በላይ በመቆም መስተጓጎል ይፈጥር እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ የኮንቮይ ጉዞ በተገኘው አንፃራዊ ሰላም ያለምንም ችግር #በአንድ_ቀን መድረስ መቻሉን አስረድተዋል።

የግድቡን ግንባታ ዳር ለማድረስ ሌት ተቀን ሃያ አራት ሰዓት ያለ ዕረፍት የሚተጉ የግንባታዉ ሰራተኞች የአካባቢውን የሙቀት ሁኔታ ተቋቁመው ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን በደማቅ ሞራል እየተወጡ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።

በስፍራው ከሚገኙ የሀገር መከላከያ አባላት የቀጠናውን ዘላቂ ሰላም በአስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ በማረጋገጥ ሰራዊቱ የተሰጠውን ግዳጅ በሞራል እየተወጣ እነደሆነ ተናግረዋል።

ሰራዊቱ የሀገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ ፀረሠላም የሆኑ ኃይሎችን ፍላጎት በማምከን የግድቡን የፍፃሜ ትንሳኤ ለማብሰር ደከመኝ ሳይል ሀገራዊ ተልዕኮዉን እየተወጣ ነው ብለዋል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia