TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ከሰሞኑን - ሰሜን ኢትዮጵያ !

ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት ከኢፌድሪ መንግስት ፣ ከአሜሪካ መንግስት ፣ ከተመድ ፣ ከአውሮፓ ህብረት እንዲሁም ከአፍሪካ ህብረት የተሰጡ መግለጫዎች እና ወቅታዊ መረጃዎች ፦

➦ አሜሪካ ባወጣችው መግለጫ ፤ በባለፈው ዓመት ነሃሴ ወር አጋማሽ ላይ " ህወሓት / TPLF " በአማራ ክልል በ " ቆቦ " አካባቢ ዘመቻ ማካሄዱንና በዚህም ጦርነቱ #ዳግም_ለመቀስቀሱ አስተዋፆ ማድረጉን ይህን ተከትሎ ተጨማሪ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ግፎች ተጋላጭነት ከፍ እንዳደረገ ገልፃለች። አሜሪካ የኢትዮጵያ መከላከያ እና የኤርትራ መከላከያ በጋራ የሚያካሂዱትን ወታደራዊ ጥቃት እንዲያቆሙ እና ኤርትራ ጦሯን ከ " ሰሜን ኢትዮጵያ " እንድታስወጣም ጥይቃለች።

                           --------------------

➦ የአፍሪካ ህብረት ( #AU ) ኮሚሽን ሊቀ መንበር ፤ ሙሳ ፋኪ በሰሜን ኢትዮጵያ ውጊያ ውስጥ ያሉ አካላት " ያለምንም ቅድመ ሁኔታ " የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ አሳስበው የሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎቶች ወደ ነበሩበት አንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት በደቡብ አፍሪካ ወደ ተጠራው " የሰላም ድርድር " እንዲመጡ ፋኪ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

                          --------------------

➦ የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፤ " በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ ነው። " ሲሉ ተናግረው ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

" አሁን በኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ የማህበራዊ ትስስር እየተበጣጠ ነው ፤ የሲቪሎች ህይወት እየቀጠፈና ውድመት እያስከተለ ያለው ጦርነት ማብቃት አለበት ብለዋል።

" የኤርትራ ኃይሎች ከኢትዮጵያ መውጣት አለባቸው " ያለቱ ጉተሬዝ በትግራይ ክልል ያለው ግጭት አሁኑኑ ማብቃት አለበት ብለዋል።  አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ወታደራዊ መፍትሄ የለውም ሲሉ ተናግረዋል።

ጦርነቱ እንዲያበቃ ተመድ (UN) የአፍሪካ ህብረትን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑ አረጋግጠው " ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሁን ለሰላም መሰባሰብ አለበት ። " ብለዋል።

በተመሳሳይ የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከኤርትራ ሰራዊት ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል እያካሄዱት ያለውን  የጋራ ጥቃት እንዲያቆሙ ጠይቋል ፤  የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ሙሉ በሙሉ ለቀው እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

ህብረቱ ህወሓት በአማራ እና አፋር አጎራባች ክልሎች ያለውን ጦርነት እንዲያቆሙና ከወታደራዊ ዘመቻ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

                        --------------------

➦ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ " በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከቁጥጥር ውጪ የወጣ ነገር የለም፤ ሁሉም ነገር በታቀደው መሰረት እየሄደ ነው " ብለዋል።

መንግስት የአፍሪካ ሕብረት ( #AU ) የሰላም ውይይቱ የሚካሄድበትን ቀን እስኪያሳውቅ በመጠባበቅ ላይ ይገኛልም ብለዋል።

" አንዳንዶች በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት ከቁጥጥር ውጪ ሆኗል በሚል እየተጠቀሙበት ያለው አገላለጽ ከእውነት የራቀ ነው " ሲሉ  ገልፀዋል።

" ግጭቱ ወደ አማራና አፋር ክልሎች ተስፋፍቶ ነበር አሁን ያ ነገር የለም፤ የመከላከል እርምጃው በታሰበው መልኩ እየሄደ ይገኛል " ያሉ ሲሆን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትና #መሰረታዊ_አገልግሎት እንደሚጀመር አሳውቀዋል።

                        --------------------

➦ ዛሬ ጥቅምት 8 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት ባወጣው መግለጫ የመከላከያ ሠራዊት በከተሞች ውስጥ ምንም ዓይነት ጦርነት ሳያካሂድ ፦
- ሽሬ፣ 
- አላማጣ
- ኮረም ከተሞችን እንደተቆጣጠረ ገልጿል።

በመግለጫው ላይ ፤ " የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተከተለው ጥብቅ ወታደራዊ ዲሲፕሊን፣ የሕወሐትን ፕሮፓጋንዳ ሲያስተጋቡ የነበሩ አካላትን ሟርት ያመከነ ነው። " ሲልም ገልጿል።

ከልዩ ልዩ የርዳታ ድርጅቶች ጋር በመሆን መከላከያ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ላይ ርዳታ እንዲደርስ በቂ ዝግጅት መደረጉን የገለፀው መንግስት እርዳታ የማድረሱ ስራ የሽሬ አውሮፕላን ማረፊያን መጠቀምን እንደሚጨምር ገልጿል።

በተጨማሪ በሰሜን ጎንደር ወደ ሽሬ የሚወስደውን እና ከኮምቦልቻ - ደሴ- ወልድያ- ቆቦ- አላማጣ ያለውን መንገድ ለመክፈት እየሠራ መሆኑም አሳውቆ ይሄንን ሥራ የሚያሣልጥ ኮሚቴ ከሚመለከታቸው አካላት ተወጣጥቶ ሥራ ጀምሯል ብሏል።

እነዚህ ሥራዎች ቴክኒካዊ የሆኑ ጥናቶችን እና ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች አገልግሎቶችን ለማስጀመር የሚያስችሉ መሠረታዊ ሥራዎችን ይጨምራል ሲልም አሳውቋል።

                             --------------------

➦ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ህወሓት ለ3ኛ ተከታታይ ጊዜ " ጦርነቱን ሆን ብሎ " በመቀስቀሱ ​​በሰሜን ኢትዮጵያ ላለው ወቅታዊ ሁኔታ ብቸኛ ተጠያቂ ነው ያለ ሲሆን ህወሓት ጊዜ እና ቦታ ከተሰጠው ይህን እንደገና ያደርጋል ብሏል።

በሌላ በኩል መንግስት ከ " ህወሓት " ነፃ ባወጣቸው እና በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ላይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ ከድጋፍ ከሚያደርጉ አካላት ጋር አብሮ እንደሚሰራ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ሰራተኞችን ደህንነት እንደሚያረጋግጥ አሳውቋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት ፣ የአፍሪካ ህብረት ትዊተር ገፅ ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድረገፅ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የመንግስት ኮሚኒኬሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

@tikvahethiopia