TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

አጫጭር መረጃዎች #1፦

- የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ ጀምሯል፤ ነገር ግን በተሟላ አቅሙ ወደ ስራ አልገባም። አሁን ላይ የድንገተኛ ህክምና ፣ የተኝቶ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው። ሆስፒታሉ የመብራት መቆራረጥ፣ የመድሃኒት እጥረትና የአምቡላንስ ችግር አለበት። የነበረው አንድ አምቡላንስ ለህልውና ዘመቻ ሄዶ እስካሁን ያልተመለሰ ሲሆን የአምቡላንስ አለመኖር በታካሚዎች ላይ ትልቅ ችግር ይፈጥራል ተብሏል። ሆስፒታሉ የጎደሉት እንዲሟሉለት ጥሪ ቀርቧል።

- ህወሓት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ሳቢያ ከሰሜንና ደቡብ ወሎ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደብረብርሃን የቆዩ ወገኖች ወደ መኖሪያ ቀያቸው ሲመለሱ የደ/ብርሃን ህዝብና ሌሎች አካላት ስላደረጉላቸው መስተንግዶ አመስግነዋል። ደ/ብርሃን በጦርነት የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ያስጠለለች ከተማ ስትሆን አብዛኛው ተፈናቃዮች አሁን ወደቀያቸው ተመልሰዋል።

- በሰሜን ኢትዮጵያ የጤና ተቋማት ላይ የደረሰውን ውድመት ተከትሎ ዶ/ር ጥላሁን ጎሹ (Mihret Medical Supply) ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን ከነትራንስፖርታቸው 4.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጡ የህክምና መሳሪያዎችን፣ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ ቪታሚኖችና አንድ ኮንቴነር ሙሉ መድሀኒቶችን በመርከብ ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል።

- በሰሜን ወሎ ዞን የመቄት ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ላይ በደረሰው ውድመት ምክንያት የረሀብ አደጋ ማንዣበቡን ገልፀዋል። ከመፈናቀል እየተመለሱ ያሉትን ለመደገፍ በወር 1.2 ሚልየን ኲንታል እህል እንደሚያስፈልገው የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ገልፆ ሁኔታው ከአቅሙ በላይ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እጆቻቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርባል።

#AMC #AmbFitsumArega #VOA

@tikvahethiopia