TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አጠቃላይ_40_60_ቤት_ፕሮግራም_አሸናፊዎች_ዝርዝር_xls_min_1.pdf
የ20/80 እና 40/60 ባለዕድለኞች ውል እንዲፈፅሙ ጥሪ ቀረበ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የ14ኛ ዙር 20/80 እና 3ኛ ዙር 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት እድለኞች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ከጥር 1ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሉት 60 የሥራ ቀናት ውስጥ ባለእድለኛው ወይም ወኪሉ ቀርበው ውል መዋዋል እንደሚጠበቅባቸው አሳስቧል።

ከተማ አስተዳደሩ በ14 ኛ ዙር የ2080 የቤት ልማት ፕሮግራም 18 ሺ 930 ቤቶች፣ በ40/60 ደግሞ 6 ሺ 843 ቤቶች እንዲሁም ተጨማሪ 18 ስቱዲዮ ቤቶች በድምሩ 25 ሺ 791 ቤቶችን እጣ የማውጣት መርሃ ግብር በማካሄዱ የሚዘነጋ አይደለም።

ውል የመዋዋያ ቦታው #መገናኛ በሚገኝው የቦሌ ክፍለ ከተማ ቅጥር ግቢ የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
20/80 እና 40/60 ውል ፦ የቤት እድለኞች #ውል_ለመዋዋል_ሲመጡ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምንድናቸው ? - እጣው የደረሰው ግለሰብ ውል ለመፈፀም በአካል መቅረብ፤ - በውጭ የሚኖሩ ጉዳያቸውን በውክልና ለማስጨረስ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ (አውታንቲኬት) ሆኖ የመጣ ውክልና ማቅረብ፤ - የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ዋና እና 2 ፎቶ ኮፒ፤ - የጋብቻ የምስክር ወረቀት ዋና…
#ማስታወሻ

ከነገ ከጥር 1 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለዕድለኞች ውል ማዋዋል ስራ ይጀመራል።

የውል መዋዋያው " #መገናኛ " በሚገኘው በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ነው።

በሁለቱም የቤት ልማት መርሀ-ግብር ባለድለኞች #በአካል እየተገኙ ውል እንዲዋዋሉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የውል ማዋዋሉ ፕሮግራም ለ60 የስራ ቀናት ወይም ለሁለት ወር ብቻ የሚቆይ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ተዋዋዬች ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በአንድ ማእከል የአገልግሎቱ መስጫ ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

በተጨማሪ ቅድመ ሁኔታዎቹን በቢሮና በኮርፖሬሽኑ ዌብሳይት እንዲሁም በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ያልተዋዋለ እድለኛ #በመመሪያ_ቁጥር 3.3/2011 መሰረት ቤቱን እንዳልፈለገው ተቆጥሮ ተመላሽ እንደሚደረግ ተገልጿል።

የቤት ባለ እድለኞች #ውል_ለመዋዋል_ሲሄዱ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች በዚህ መመልከት ይቻላል 👇

https://t.iss.one/tikvahethiopia/75662

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አካል ጉዳተኛ በመምሰል ስትለምን የነበረች ተጠርጣሪ ከእነ ግብረአበሯ መያዟን አስታወቀ።

ግለሰቦቹ በቀን እስከ 500 ብር ድረስ እንደሚያገኙ ታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዋ ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሳይኖራት ነው አካል ጉደተኛ በመምሰል ወገቧን በጎማ በማሰር ዊልቸር ላይ በመሆን ስትለምን ትላንት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው " #መገናኛ " አካባቢ በህብረተሰቡ ጥቆማ የተያዘችው።

ግለሰቧን ከቦታ ወደ ቦታ ሲያንቀሳቅሳት የነበረው ተጠርጣሪም ተይዟል።

ተጠርጣሪዎቹ ዊልቸሩን በቀን 35 ብር ተከራይተው ለ8 ወር እንደተጠቀሙና በቀን እስከ 500 መቶ ብር እንደሚያገኙ ከሰጡት ቃል ማወቅ እንደተቻለ ፖሊስ አስረድቷል።

ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሳይኖርባቸው ጉዳተኛ በመስምሰል የሚያታልሉ እንዳሉ ህብረተሰቡ ሊገነዘብ ይገባል ሲል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#መገናኛ

" የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ ተጀምሯል ፤ ለገንቢው እንዲያጠናቅቅ የተሰጠው 45 ቀናት ነው " - አቶ ጥራቱ በየነ

ከፍተኛ መጨናነቅ ባለበት " መገናኛ ' አካባቢ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መስመር ግንባታ መጀመሩ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ፣ መኪና የሚበዛበትና የሚገናኝበት ፣ እጅግ በርካታ እግረኞችም የሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ነው " መገናኛ " አካባቢ።

በዚህ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት ያግዛል የተባለ የመሬት ውስጥ ለውስጥ የእግረኛ መተላለፊያ መሰራት ጀምሯል።

ይህ ፕሮጀክት ከቦሌ ኤርፖርት እስከ መገናኛ ባለው የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ አንዱ አካል እንደሆነ ተመላክቷል።

ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ምን አሉ ?

" መገናኛ በጣም ብዙ ሰዎች ተሽከርካሪዎችም የሚገናኙበት በመሆኑ ከፍተኛ መጨናነቅ አለ።

ቀድም ብሎ የቀለበት መንገድ የሚባለው ስለነበር መንገዱ ለእግረኞች ማቋረጫ በቂ አልነበረም። በዚህም ህብረተሰቡ በርካታ ችግር እንዲያሳልፍ ሆኗል።

ይሄ ትልቅ ጎዳና እንደመሆኑ የሚሰራው እግረኞች ደህንነታቸው ተጠብቆ ምንም ሳይቸገሩ በመሬት ውስጥ መሻገር የሚችሉበት ነው።

የታክሲ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናልም ይገነባል በማዶ በኩል። በሙልጌታ ህንጻ ስርም ሁለት ወለል ያለው ተርሚናል ይገነባል።

እግረኞች ከአንዱ ተርሚናል ወደሌላኛው ተርሚናል የሚገናኙት በመሬት ውስጥ ይሆናል።

ከላይ ምንም አይነት የሰው እንቅስቃሴ በማይኖርበት ወይም በኒቀንስበት ሁኔታ ነው እየሰራን ያለነው።

ገንቢው ተቋራጭ ይህንን ስራ እንዲያጠናቅቅ የተሰጠው ጊዜ 45 ቀን ነው።

ትንሽ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል። ለ45 ቀናት መንገዱን ስንዘጋው የነዋሪዎች እና የመኪና እንቅስቃሴ በተለይ
መገናኛ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት እንደመሆኑ ጫና መፍጠሩ አይቀርም።

ዛሬ የምንወስነው ውሳኔ ምናልባት ለወደፊቱ ለበርከታ ረጅም አመታት ዘላቂ መፍትሄ ይሆናል።

ለ45 ቀናት በ3 ሺፍት ነው የምንሰራው። ከዛም ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ከሚሰሩት ኮንትራክተሮች ጋር ተግባብተናል " ብለዋል።


የግንባታ ስራውን የሚያማክረው ማነው ? ስራውን የሚያማክረው የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ነው።

ኮርፖሬሽኑ " የመገናኛ እግረኛ መተለለፊያ ስራ በአይነቱ የተለየ እና ዘመናዊ ነው " ብሎታል።

ሱቆችን ጨምሮ የተለያዩ የፅዳት ቦታዎችም ይሰራሉ ብሏል።

" ፕሮጀክቱን በተባለው በ45 ቀናት እንደሚያልቅ እርግጠኞች ነን ፤ 24 ሰዓት ነው የሚሰራው  ፣ በቂ ማሽነሪ አለ፣ በተጓዳኝ ብረትና ሌሎች ዥግጅቶች እየተደረጉ ነው " ሲል ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኤኤምኤን ቲቪ መውሰዱን ይገልጻል።

@tikvahethiopia