TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update 10ኛ ክፍል⬇️

በ2010 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የፈተና ውጤት እስከ #አርብ ድረስ ይፋ እንደሚሆን የሀገር ዓቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።

የተማሪዎችን እርማት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ መረጃውን በአጭር ጽሁፍ እና በድረ-ገጽ በጥራት ለማሰራጨት ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ መሆኑን የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሔር ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው እስካሁን ውጤት በየትኛውም የውጤት ማሳወቂያ ዘዴ እንዳላወጣና ተማሪዎች በኤጀንሲው ስም በሚወጡ #የተሳሳቱ መረጃዎች እንዳይታለሉም አቶ አርአያ አሳስበዋል፡፡

ውጤቱን ይፋ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸውንና እስከ መጪው አርብ ድረስ ውጤቱ እንደተለመደው በኤጀንሲው ድረ-ገፅና በአጭር የፅሁፍ መልእክት ይፋ ይደረጋል፡፡

ተማሪዎች የለፉበት ውጤት እንዳይሳሳት በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ዳይሪክተሩ የ2010 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል የፈተና ውጤትን ተማሪዎች #በትእግስት እንዲጠባበቁም ጠይቀዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰተኛ መረጃዎች‼️

"በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎችን #በማጥራት መጠቀም ይገባል" ተማሪዎች

በማህበራዊ ሚዲያ በሚለቀቁ #የተሳሳቱ መረጃዎች #ሳይደናገጡ ትምህርታቸው ላይ ብቻ ለማተኮር መዘጋጀታቸውን የኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገለጹ፡፡

ከጎንደር የመጣው ተማሪ ደጀን እንዳለው ዩኒቨርሲቲው ባደረገላቸው አቀባበል መደሰቱን ገልጾ በቆይታው ከተራ አሉቧልታ፣ #ዘረኝነትና ከፖለቲካ ወገንተኝነት #ርቆ ትምህርቱን ለመከታተል ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ከቦንጋ ዞን የመጣችው ገነት ጌታቸው በበኩሏ በትምህርቷ ውጤታማ የምትሆንበትን መንገድ ከመከተል ባለፈ በተለያየ መንገድ ለሚሰራጩ ሀሰተኛ ዘገባዎች ጆሮ እንደማትሰጥ ገልጻለች፡፡

ለዚህም ከነባር ሴት ተማሪዎች የምክር አገልግሎት አግኝታለች፡፡ በትምህርት ቆታዋ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በመከባበር፣ በመቻቻልና በትብብር ሰርታ ውጤታማ ለመሆን  ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጣለች፡፡

ከአምቦ የመጣው  ተማሪ ኤልያስ ዳባም ዩኒቨርሲቲው ከመናኸሪያ ጀምሮ ስለተቀበለው ምንም አይነት እንግልት እንዳልደረሰበት ገልጾ በትምህርቱ ውጤታማ ሆኖ ሀገርንና ህዝብን ለማገልገል እንደሚተጋ ተናግሯል፡፡

በልዩልዩ የመገናኛ ዘዴዎች በሚናፈሱ ወሬዎች መደናገጥና መዘናጋት ሳያስፈልግ ተማሪዎች የመጡበትን ዓላማ ለማሳካት ተግተው መስራት እንዳለባቸውም ጠቁሟል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የሁለኛ ዓመት የስፖርት ሳይንስ ተማሪው ለሚ ጌታ እንዳው  በሀገር ደረጃ  በተፈጠረው ለውጥ  ተረጋግቶ ትምህርቱን ለማመር ተዘጋጅቷል፡፡

የሁለተኛ አመት የታሪክ ተማሪዋ  አበራሽ ግርማ በበኩሏ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች በአንድ ክፍል ውስጥ መኖራቸው መልካም አጋጣሚ እንዳለው ሁሉ ለአለመግባባት ምንጭ ሊሆን እንደሚችል ተናግራለች፡፡

ለዚህም አብሮ የመኖር የጋራ እሴቶችን በማጎልበት በመቻቻልና በፍቅር ለመኖር መዘጋጀት እንደሚገባ ነው የገለጸችው፡፡

የተማሪዎች ህብረት ሰብሳቢው  ተማሪ ባምላኩ ዱኩ እንዳለው ተማሪዎቹ እንዳይንገላቱና ለስርቆት እንዳይጋለጡ ከመናኸሪያ ጀምሮ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ተማሪዎቹ በቆይታቸው በማህበራዊ የትስስር ገጾች የሚለቀቁ ሀሰተኛ መረጃዎችን በአግባቡ መጠቀም እንዲችሉ ግንዛቤያቸውን የማሳደግ ስራ ይሰራልም ብሏል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዘዳንት ወይዘሮ ሂሩት አበበ እንዳሉት ተማሪዎችን ለመቀበል በተደረገው ልዩ ዝግጅት ቀድመው የመጡ  ተማሪዎች ጭምር የምግብና የመኝታ አገልግሎት  እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

አብዛኞቹ ተማሪዎች ከተለያዩ ክልሎች እንደመምጣታቸው መረበሽና እንግድነት እንዳይሰማቸው  ከተማሪዎች ህብረት ጋር በመቀናጀት  የኒቨርሲቲው ከመናኸሪያ ጀምሮ  ትራንስፖርት በማቅረብ ተማሪዎችን መቀበሉንም ተናግረዋል፡፡

የመማር ማስተማር ስራውን ጤናማ ለማድረግ ለነባር ተማሪዎች ግንዛቤ መሰጠቱንና አዲስ ተማሪዎች ላይም መሰል የግንዛቤ ማጎልበቻ ስራዎች እንደሚሰሩ ምክትል ፕሬዝዳንቷ አስታውቀዋል፡፡

ከዩኒቨርሲቲው ሴኔት ጋር በመወያየት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን በቅርበትና በፍጥነት ለማረም ከወዲሁ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉንም ነው የገለጹት፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahuniversity
'TIKVAH-ETH ለ20,000 ኢትዮጵያውያን የNOKIA ስልክ ለበዓል ስጦታ ሊሰጥ ነው፣ ይህ ቻናል ተቀላሉ' እየተባለ ዛሬ ምሽቱን ለብዙ ሺዎች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

የቲክቫህ ኢትዮጵያን ስም በመጠቀም የተለያዩ የቴሌግራም፣ የትዊተር፣ የፌስቡክ ገፅ በመክፈት በርካታ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ ስለሆነ ጥንቀቄ አድርጉ።

ከዚህ ባለፈ የTIKVAH የአፃፃፍ መንገዶችን በመከተል ብዙ አካላት መረጃዎችን ያሰራጫሉ ፤ ላለፉት 2 ዓመታት መላው ቤተሰባችን የሚታወቅበትን አቀራረብ በመከተል #የተሳሳቱ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ሰዎችን በህግ የምናስጠይቅ ይሆናል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia