TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወ/ሮ ሰናይት...‼️

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ ፅ/ቤት በቅርቡ ሸገር ሬድዮ ላይ ቀርባ ስለ #መታወቂያ አሰጣጥ አስተያየቷን የሰጠችው ወ/ሮ ሰናይት ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ጋር በነበራት ቆይታ ይህን ብላለች፦

"ብዙ ተወርቶ እንደነበረው አስተያየቱን ለሸገር ሬድዮ ከሰጠሁ በሁዋላ ወደ ስራ አልተመለስኩም ነበር። ትናንት ግን #ወደስራ_ተመለሺ የሚል ደብዳቤ ተፅፏል። አሁን ወደ ቢሮ እየሄድኩ ነው። ውጤቱን በሁዋላ እነግርሀለው። ሰዎች #እያስፈሯሯት ነው ተብሎ በሶሻል ሚድያ የተወራው ግን #ሀሰት ነው። እዛ ደረጃ ነገሮች ከሄዱ ወደ መንግስት አካላት እና ሚድያዎች እሄዳለሁ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SNNPRS

በደቡብ ክልል መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በ5 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግብ ጥሪ ቀረበ።

ይህ ጥሪ የተላለፈው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ትናንት ያካሔዱትን ውይይት መድረክ ተከትሎ ነው።

በዚህም መሰረት ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ አካል ከዛሬ ከጥቅምት 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በአካባቢው በሚገኙ የፖሊስ ጣቢያዎች ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ማንኛውም #መታወቂያ የሚሰጥ አካል አዲስ መታወቂያ መስጠት አልያም የመታወቂያ እድሳት ማካሔድ ክልክል መሆኑ ተገልጿል።

አስቸጋሪ ሁኔታ ቢፈጠር እና መታወቂያ ማግኘት ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ግን የክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ እዝ አውቆት ውሳኔ ሊሰጥበት ይችላል ተብሏል።

መረጃው ከደቡብ ክልል ኮሚኒኬሽን ያገኘነው ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba 🪪 " ላልተወሰነ ጊዜ አዲስ መታወቂያ መስጠት አቁመናል " - የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ላልተወሰነ ጊዜ " አዲስ መታወቂያ " የመስጠት አገልግሎት ማቆሙን አስታውቋል። ኤጀንሲው የመታወቂያ ፣ የልደት ፣ የጋብቻና የሞት ማስረጃዎችን ይመዘግባል ፤ ዜጎች በሚፈልጉበት ወቅትም አገልግሎቱን ይሰጣል፡፡ በአገልግሎት አሰጣቱ…
#መታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተበራከተ የመጣዉን ሰነድ እና የነዋሪነት መታወቂያ አስመስሎ የመስራት /ፎርጀሪ/ ወንጀል ተጋላጭነትን ለመከላከል አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ከሚያዚያ 21፣ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ግዜ እንዲቆም መደረጉ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እድሚያቸው 18 ዓመት ሞልቶ የነዋሪነት መታወቂያ ያላወጡ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመደቡ ተማሪዎች ፦

* በከተማዉ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ መሆኑን የሚያስረዳ የ12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ እና

* ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያለፉበትን ዉጤት በማቅረብ በነዋሪነት የቤተሰብ ቅጽ ዉሰጥ አስቀድሞ የተመዘገቡ መሆኑ ሲረጋገጥ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ተፈቅዷል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ወ/ኩ/ም/ኤጀንሲ

@tikvahethiopia
#መታወቂያ

በአዲስ አበባ ታግዶ የቆየው የመታወቂያ እድሳት በተያዘው ጥቅምት ወር መጨረሻ እንደሚጀመር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ ገልፀዋል።

አቶ ጥራቱ በየነ ለኢዜአ የሰጡት ቃል፦

- በመታወቂያ አሰጣጥና እድሳት ዙሪያ ለተስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች ዘላቂ እልባት በመስጠት ችግሩን ለመፍታት አገልግሎቱ በጊዜያዊነት እንዲቆም ተደርጎ ነበር።

- በብልሹ ተግባሩ ላይ ተሳታፊ የነበሩ አመራሮችና ሰራተኞችን በመለየት ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተከናውኗል።

- በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተለይም ችግሩ ጎልቶ በታየባቸው 37 ወረዳዎች በተደረገ ክትትል 90 አመራሮችና ባለሙያዎችን ተጠያቂ ተደርጓል።

- ታግዶ የቆየው #የመታወቂያ_እድሳት ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ በተያዘው ጥቅምት ወር መጨረሻ ይጀመራል። ከዚህ ጎን ለጎን የከተማዋ ነዋሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ እንዲሆንኑአሰራሩን የማዘመን ስራ ይቀጥላል ነው የተባለው፡፡

- በአሁኑ ወቅት የራሳቸው መለያና ምሥጥራዊነት ያላቸው መታወቂያ ለመስጠት የሚያገለግሉ ወረቀቶች በመታተም ላይ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይ ለነዋሪው የመስጠት ተግባር ይከናወናል ብለዋል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት በአዲስ አበባ ከ4 ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረዉ የመታወቂያ #እድሳት አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል። @tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" ነገ እና እሁድ ከጥዋት እስከ ምሽት መታወቂያ ማሳደስ ትችላላችሁ "

#መታወቂያ_ለማሳደስ እየተጠባበቁ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ነገ #ቅዳሜ እና #እሁድ ከጥዋት እስከ ምሽት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ነገ ቅዳሜ እና እሁድ ማለትም ህዳር 3 እና 4 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋት እስከ ምሽት ድረስ በየአካባቢው ባሉ የወረዳ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ  ፅ/ቤቶች ይሰጣል።

ነዋሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በየአቅራቢያቸው ባሉ ፅ/ቤቶች ተገኝተው መስተናገድ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት በአዲስ አበባ ከ4 ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረዉ የመታወቂያ #እድሳት አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል። @tikvahethiopia
#መታወቂያ

የአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ፤ የተፈቀዱ አዲስ የነዋሪነት ምዝገባ እና የመታወቂያ አገልግሎቶችን አሳውቋል።

በከተማ አስተዳደሩ ተቋርጦ የነበረዉ የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ከህዳር 1/2015ዓ.ም ጀምሮ የተፈቀደ መሆኑ ያስታወሰው ኤጀንሲው አሁን ደግሞ ፦

👉 በቤተሰብ ማህደር ተመዝግበው 18 ዓመት የሞላቸው ነዋሪዎች፤

👉 ለህክምና ክትትል የሚፈልጉ እና ህጋዊ የህክምና ማስረጃ የሚያቀርቡ ዜጎች፤

👉 በከተማዉ ፍ/ቤት መብት ለማስከበር የሚያበቃቸዉ የመብት ጉዳይ ኖሯቸዉ #የነዋሪነት_መታወቂያ ለሚያስፈልጋቸዉ ነዋሪዎች አሰራርን በመከተል አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች ሲያሟሉ አገልግሎት እንዲያገኙ መፈቀደኑን ገልጿል።

ይህ የተፈቀደው ከትላንት ዓርብ ህዳር 23/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን ተገልጋዮች ሊኖር የሚችለውን ጫና ከግምት በማስገባት በተረጋጋ ሁኔታ ቀርባድ አገልግሎት እንዲያገኙ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ፤ የአዲስ አበባ ከተማ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 24 #ሙሉ_ቀን በሁሉም የወረዳ ፅ/ቤቶች አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለፀ ሲሆን ነገ እሁድ ህዳር 25 አገልግሎት ዝግ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

የነዳጅ ግብይት #በመላው_ሀገሪቱ  በ " ዲጅታል " መንገድ ብቻ እንዲሆን በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ዛሬ ግንቦት 1/2015 ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

በክልሎች የነዳጅ ጉዳይ ከተነሳ አይቀር ...

በክልል ከተሞች ላይ #ነዳጅ በተለይም ቤንዚን እንደልብ ማግኘት የማይታሰብ ነው። ነዳጅ ሲገኝም ለሰዓታት ረጃጅም ሰልፍ መሳለፍ እና መንገላታት አይቀሬ ነው።

እንደ #ሀዋሳ ያሉ ትልቅ ከተሞች ውስጥ ነዳጅ በወረፋ ብቻ ሳይሆን በሳምንት ለተወሰነ ቀን ብቻ ነው መቅዳት የሚቻለው (ለከተማው ነዋሪ - በኩፖን) ። ይህም የሚከናወነው በታርጋ " #ሙሉ እና #ጎዶሎ ቁጥር " ነው የሚከናወነው። ማደያዎችም ከተመደበላቸው ተሽከርካሪ ውጭ ማስተናገድ አይችሉም።

" እንግዳ ነኝ ፤ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ አይደለሁም " ለሚሉት ደግሞ የነዳጅ ማደያዎች የሚኖሩበትን ከተማ የነዋሪ #መታወቂያ በማየት እንደሚቀዱ ለመረዳት ተችሏል።

ከምንም በላይ የሚገርመው እጅግ በርካታ ማደያዎች ባሉበትና አሁንም እየተሰሩባት ባለው ከኢትዮጵያ ግዙፍ ከተሞች አንዷ ሀዋሳ በየዕለቱ ነዳጅ የሚሸጡት እጅግ ውስን ቁጥር ያላቸው ማደያዎች ናቸው።

ይህ በእንዲህ እያለ ግን በከተማው ነዳጅ በጥቁር ገበያ ከፍ ባለ ብር እንደጉድ ነው የሚቸበቸበው። ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በሀዋሳ ዙሪያ ጭምር ነው ይህ የሚሆነው።

የከተማው የአስተዳደር አካላት ይህንን እያወቁ መፍትሄ እየሰጡ እንዳልሆነ ከተገልጋዮች ቅሬታ ይቀርባል።

እጅግ በጣም ብዙ ተሽከርካሪዎች በሌሉበት እና በርካታ ማደያዎች ባሉበት ከተማ ነዳጅ ለማግኘት በዚህ ደረጃ መቸገር ከምን የመጣ ነው ?

ከሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ ስላለው የነዳጅ ግብይት ጉዳይ የሲዳማ ክልል ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በድሶ አዲሳ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

አቶ በድሶ አዲሳ  ፦

" ችግሩ አለ ፤ ይህ የሆነው በቀን ከ3 ሚሊዮን ሊትር የማይበልጥ ቤንዚን ስለሚቀርብ በአገር ደረጃ የቤንዚን እጥረት በመኖሩ ነው።

ለዚህም ሲባል ተሸከርካሪዎችን በየቀኑ በተለያዩ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች መድበን ነው እንዲቀዱ የምናደርገው።

ችግሩ ያለው ቤንዚን ላይ ነው የነዳጅ ማደያዎችም ቤንዚን ለማግኘት አንድ ወር ይጠብቃሉ።

ነዳጅ በጥቁር ገበያ ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባም ይሸጣል ፤ ለዚህ ተብሎ ከሌላ ቦታ የሚገባ ነዳጅ አለ።

እንደዚህ ዓይነት ተግባር የሚፈጽሙ የተወሰኑ ማደያዎች መኖራቸው ታውቆም እርምጃ የተወሰደባቸው አሉ።

ግብይቱ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ሲሆን ችግሩ ይቀረፋል። "

ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይ በሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሻሸመኔ፣ በሌሎችም ከተሞች ያለ ጉዳይ ነው።

እንደ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን መረጃ ከሆነ " በሀገር ውስጥ በቂ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት አለ " ነገር ግን በክልል ከተሞች ያለው ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይና የጥቁር ገበያው ነገር መፍትሄ የሚያሻው ነው።

@tikvah_eth_BOT @tikvahethiopia
#አዲስአበባ #መታወቂያ

“ በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን ” - CRRSA

ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው አዲስ አበባ ከተማ ለመጡ ተገልጋዮች የመታወቂያ አገልግሎት በቅርብ ጊዜ መሰጠት ይጀመራል ተብሎ ነበር።

ነገር ግን እስካሁን አገልግሎቱ አልጀመረም።

ነዋሪዎችም መቼ እንደሚጀምር ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቼ ነው አገልግሎቱ መስጠት የሚጀምረው ? ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ አለማየሁን ጠይቋል።

እሳቸውም በሰጡት ምላሽ፣ “ በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን ” ብለዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው በዝርዝር ምን አሉ ?

➡️ ከመሸኛ ጋር ተያይዞ ፣ ከክፍለ አገር ለሚመጡ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎቱ #ዝግ አይደለም።

- በሕመም፣
- በትምህርት እድል፣
- ተጋቢዎች ሆነው ከሌላ ቦታ ሲመጡ እዚህ (አ/አ) አንዱ ተጋቢ ካለና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ከሆነ፣
- በሥራ ዝውውር ከሆነ እነዚህ ሁሉ አልተከለከሉም። የተፈቀዱ አገልግሎቶች ናቸው።

➡️ የተከለከለው፣ ያለ ምክንያት ዝም ብሎ ለሚመጣ ነዋሪ ነው። ያለ ምክንያት ስንል በእርግጥ በምክንያት የሚመጣ አለ። ግን አዲስ አበባ ውስጥ ያለውን አጠቃላይ ነዋሪ አገልግሎት ቁጥጥር ለማበጀት የተደረገ ነው።
 
ኃላፊው በሰጡት ቃል ፥ " መሸኛ አስገብተው መረጃዎችን እየተጠባበቁ ያሉትን ለማስተናገድ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቀናል " ብለዋል።

በጣም ባጠረ ጊዜ እንደሚጀመር አመልክተዋል።

" የገጠመን አንዱ ትልቅ ፈተና የነበረው (ለ15 ቀናት አካባቢ) አዲስ መዝጋቢ መመዝገብ ከባድ ሆኖብን ነበር፣ ቴክኒካል ችግር ተከስቶ። እሱን ፈትተናል " ያሉት አቶ ዮናስ " በዚህ ምክንያት አዲስ ተመዝጋቢ የሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የነበሩ ተገልጋዮች ቁጥራቸው ከፍ (አገልግሉቱን በመቋረጡ) ስላለ እሱን ማቅለል ስላለብን ነው። እሱን እንዳቀለልን እንጀምራለን " ሲሉ አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የአከራይ እና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀመር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መጽደቁ ይታወቃል፡፡

በዚህም አስተዳደሩ አዋጁን በመመሪያ በማስደገፍ ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅቶቹን ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ከሰኔ 1 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የግል ቤት አከራዮች ከተከራዮቻቸው ጋር ህጋዊ ሰነዶቻቸውን ይዘው በመቅረብ ምዝገባ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ቤት አከራዮች ፦

➡️ ህጋዊ የምዝገባ ውል ለመፈጸም ወደ ወረዳ ጽ/ቤቶች በሚሄዱበት ወቅት ቤቱ የራሳቸው ስለመሆኑ ወይንም ህጋዊ ተወካይ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተከራዮች ፦

➡️ ማንነታቸውን የሚገልጽ #መታወቂያ ወይም ሌላ ህጋዊ ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።

በስራ ሰዓት መመዘግብ የማይችሉ አከራይና ተከራዮች ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በስራ ቀን ማታ ከ12 ሰዓት በኋላ ህጋዊ የውል ምዝገባውን መፈጸም ይችላሉ።

#ENA
#Ethiopia
#AddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አዲስአበባ #መታወቂያ “ በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን ” - CRRSA ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው አዲስ አበባ ከተማ ለመጡ ተገልጋዮች የመታወቂያ አገልግሎት በቅርብ ጊዜ መሰጠት ይጀመራል ተብሎ ነበር። ነገር ግን እስካሁን አገልግሎቱ አልጀመረም። ነዋሪዎችም መቼ እንደሚጀምር ጠይቀዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቼ ነው አገልግሎቱ መስጠት የሚጀምረው ? ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት…
#አዲስአበባ #መታወቂያ

“ የትምህርት ቤት ምዝገባው ሲጠናቀቅ አገልሎቱን መስጠት እንጀምለራለን ” - CRRSA

ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው አዲስ አበባ ከተማ ለመጡ ተገልጋዮች የመታወቂያ አገልግሎት “በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን” መባሉን ከወራት በፊት ነግረናችሁ ነበር።

አሁንስ ጉዳዩ ከምን ደረሰ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ አገልግሎቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደምትሰጡ ከዚህ ቀደም ገልጻችሁ ነበር፤ ለመሆኑ ጉዳዩ ከምን ደረሰ? ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲን ዛሬ ጠይቋል።

የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ አለማየሁ በሰጡት ምላሽ፣ አገልግሎቱን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ ገልጸዋል።

“ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቀን ነበር ” ያሉት አቶ ዮናስ፣ “ ከተማ ውስጥ የትኛውም የየትምህርት ምዝገባ በልደት ካርድ መነሻ መሆን እንዳለበት አሰራር ዘርግተናል ” ብለዋል።

“ በዚህ መሠረት አሁን ባለው ሁኔታ ቢሮዎቻችን ይህንን አገልግሎት እየሰጡ ስለሆነ አብሮ ማስኬድ የማይቻል በመሆኑ ከትምህርት ቤት ምዝገባ በኋላ እንጀምራለን ” ሲሉ አክለዋል።

ከትምህርት ምዝገባ በኋላ መቼ እንደሚጀመር ቲክቫህ የጠየቃቸው አቶ ዮናስ፣ ከነሃሴ አጋማሽ 2016 ዓ/ም በኋላ እንደሆነ አስረድተዋል።

“ለዚህ የሚሆኑ ምቹ ሁኔታዎች አሉ” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ “ሁሉም ወረዳዎች (119ኙም) በአሁኑ ወቅት ዲጂታላይዝድ ሆነዋል። አዲስ አበባ የወረቀት መመታወቂያ ለአንዴና ለመጨረሻ ተሰናብታለች ሰኔ ወር ውስጥ” ነው ያሉት።

“ ምቹ ሁኔታዎች አሉ። የማጭበርበር አዝማሚያም ካለ እጅግ በጣም Rare ነው የሚሆነው። ከክልል ከተማ የሚመጡት ሰዎች አገግሎቱን ሲያገኙም ጥብቅ የሆን ቃለ መጠይቅ ይኖራል ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ በቃለ መጠይቁ ውስጥ የምናገኛቸው ጉድለቶች፣ ግድፈቶች ካሉ አገልግሎቱን ልንከለክልበት የምንችል ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል ” ብለዋል።

አቶ ዮናስ አክለው፣ “ ምክንያቱም ከክልል የሚቀርቡ መረጃዎችና መልቀቂያዎች ሀሰተኝነታቸው እየጨመረ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ እየሆነ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ ከፍተኛ ፍልሰት አዝማሚያው ምዝገባውን አግኝቶ ማስረጃውን ማግኘትም ጭምር ብቻ እንደሆነ አንዳንዱን ገምግመናል” ብለዋል።

“ በዚህ መልክ ተደራጅቶ እየተጠባበቀ ያለው ነዋሪ 47,000 ነው። ከዛ ውስጥ 40% ከአማራ ክልል፣ ኦሮሚያ ክልል 35%፣ ቀሪ የኢትዮጵያ ክልሎች 25% ሆኖ ተተንትኗል ” ነው ያሉት።

አክለው፣ “ ከእነዚህ ውስጥ ሃሰተኛ የሚያስመስሉ መሸኛዎች ያስገቡ መኖራቸውን አረጋግጠናል ” ብለዋል።

“ ጤነኛ የሆነ መሸኛ ይዞ የሚመጣ ደግሞ ይኖራል ” ያሉት አቶ ዮናስ፣ ህጋዊ የሆኑትን ለማስተናገድ ዝግጅታቸውን እንዳተጠናቀቁ፣ የት/ቤት ምዝገባ እንደተጠናቀቀ አገልግሎቱን መስጠት እንደሚጀምሩ አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia