TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ልክ ጎንደር እንደተደረገው በደብረብርሃን ከተማም ክልከላዎች ተጣሉ።

ደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ #ህጋዊ_መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ህጋዊ መታወቂያ ሳይዝ የተንቀሳቀሰ ግለሰብም ሆነ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ይውላል ተብሏል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት " የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ " እንዲቻል በሚል ክልከላዎችን መጣሉን አሳውቋል።

ክልከላዎቹ ምንድናቸው ?

1. በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት ተከልክለዋል።

2. በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00  ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

3. በከተማ አስተዳደሩ ለጸጥታ ማስከበር ተልዕኮ ከተሠጠው   የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

4. ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

5. በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ ተከልክሏል።

6. በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ ተከልክሏል።

7. በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገቢያዎች፣ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

8. የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ ተከልክሏል የልዩ ኋይል ፣ የፓሊስ ፣ የመከላከያ ሠራዊት ፣ የፌዴራል ፓሊስ ልብስ መልበስ ተከልክሏል።

9 . ያልተፈቀደ ስብሰባዎችን ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ያልተፈቀደ ሰልፍ ማድረግ ፣ መንገድ መዝጋት  ተከልክሏል።

10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ ተከልክሏል።

11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈሉ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስተው ወደ ከተማው የገቡ በከተማው በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንዲሰባሰቡ ማሳሰቢያ ተላልፏል። ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ ተከልክሏል።

12. ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ  እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል ተብሏል።

13. በከተማው ውስጥ ህጋዊ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው ህጋዊ መታወቂያ ሳይዝ የተንቀሳቀሰ ግለሰብም ሆነ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ይውላል።

14. በከተማው በተፈናቃይ ካምፕ የምትገኙ ተፈናቃይዎች በማንኛውም ሰአት ወቅታዊ ሁኔታው እስከሚስተካከለ ድረስ ከካምፕ ውጭ መገኘት ፈጽሞ ተከልክለዋል።

መረጃው ደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር የጸጥታው ምክር ቤት ኮማንድ ፖስት ነው።

@tikvahethiopia