TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምዕራብ ጎንደር‼️

በምዕራብ ጎንደር ዞን #መቃ በተባለች አነስተኛ ከተማ በትንሹ 17 ሰዎች በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ነዋሪዎች #መታገታቸውን የዐይን እማኝ ተናገሩ። ከጎንደር ወደ ገንደውሐ በመጓዝ ላይ የነበሩ መንገደኞችን ያገቱት የመቃ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው ተብሏል። ታጋቾቹ ሌንጫ በተባለ ቀበሌ ጉባይ ጀጀቢት ወደተባለ ቦታ ተወስደዋል። ከታጋቾቹ መካከል ሁለት ልጆች የያዙ አንዲት እናት እንደሚገኙበት በቦታው የነበሩ የዐይን እማኝ ተናግረዋል። መቃ ከተማ በታገተው ተሽከርካሪ በመጓዝ ላይ እንደነበሩ የሚናገሩት መምህር ጋሻው ጌቴ «ትናንት ከጎንደር ተነስተን ወደ ገንደውሐ ከተማ ስንሔድ መቃ አካባቢ መኪናውን አግተው ከ17 ያላነሰ ሰው ነው ጉባይ ጀጀቢት ወደሚባል ቦታ ይዘውት የሔዱት» ብለዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር እና ጸጥታ ኃላፊ አቶ #ደሳለኝ_ጣሰው እገታው መፈጸሙን ቢያረጋግጡም ስብሰባ ላይ በመሆናቸው ተጨማሪ ማብራሪያ ሳይሰጡ ቀርተዋል።

በተለምዶ አባዱላ ተብሎ የሚጠራው የሕዝብ መጓጓዣ መቃ በተባለችው ከተማ ነዋሪዎች ሲታገት 20 ገደማ ሰዎች ጭኖ እንደነበር መምህር ጋሻው አስረድተዋል። ተሽከርካሪው መቃ ከተማ ላይ ሲደርስ መምህር #ጋሻው_ጌቴን ጨምሮ ሦስት ሰዎች ወርደው ወደ ሕዝብ በመቀላቀል ማምለጣቸውን የዐይን እማኙ አስረድተዋል። ኩነቱ በአካባቢው በተፈጠረው ቀውስ ሳቢያ የተከሰተ መሆኑን የተናገሩት መምህር ጋሻው እገታውን የፈጸመው «መቃ የሚባል ቀበሌ ሕዝቡ ነው» ብለዋል። የዐይን እማኙ እገታው በተፈጸመበት ወቅት «በጣም ብዙ ሰው ተደብድቧል። በጣም ብዙ ሰው ተመቷል» ሲሉ አስረድተዋል። «ሰዎቹ ይሙቱ ይዳኑ የሚታወቅ ነገር የለም። መኪናው ግን በመከላከያ ተይዟል የሚል መረጃ አግኝቻለሁ» ሲሉም አክለዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia