TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ብአዴን⬆️

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ #በረከት_ስምኦን እና አቶ #ታደሰ_ካሳ አሁን ባላቸው ወቅታዊ አቋም የአማራን ህዝብ ጥቅም እንደማያስጠብቁ በመረጋገጡና በጥረት ኮርፖሬት ላይ በሰሩት #ጥፋት እስከ ሚቀጥለው የድርጅቱ መደበኛ ጉባኤ ድረስ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት #ታግደዋል፡፡

ነባር አመራሮች በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው መመሪያም #ተሽሯል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ በሚኖረው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አባል ያልሆነ አመራር #አይሳተፍም፡፡

📌ማዕከላዊ ኮሚቴው የሁለት ቀን ስብሰባውን ዛሬ አጠናቋል፡፡

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ህብተረሰቡ እንዳይጠቀማቸው የተከለከሉ የምግብ አይነት ዝርዝሮች፦

የከረሚላ ምርቶች

•ጆሊ ሎሊፖፕ
•አናናስ ከረሚላ
•ኮላስ ከረሚላ
•ኦሊ ፖፕ
•ቤስት ከረሚላ
•የስ ከረሚላ (ኮፊ ከረሚላ)
•ማሚ ሎሊ ፖፕ
•ሳራ ከረሚላ
•ጃር ሎሊ ፖፕ
•ጸሃይ ሎሊ ፖፕ
•ዩኒክ ሎሊ ፖፕ
•እንጆሪ ከረሚላ
•ብርቱካን ከረሚላ
•ይናቱ ሎሊ ፖፕ እና ሃላዋ ከረሚላ

የማር ምርቶች፦

•አፍያ የተፈጥሮ ማር
•ሪትም ማር እና በላይ ማር

የገበታ ጨው፦

•ዊዲ
•ሱላ
•ናይ
•ሃያት
•አቤት
•በእምነት
•እናት
•አባይ
•አባት፣ ሴፍ እና ጣዕም የገበታ ጨው

የለውዝ ቅቤ፦

•ደስታ
•አስነብ
•ኑኑ
•አቢሲኒያ
•ብስራት
•ፈሌ
•ሳባ፣ አዳ እና አደይ የለውዝ ቅቤ

የኑግ ዘይት፦

•አደይ አበባ እና ቀመር የኑግ ዘይት

አልሚ የህጻናት ምግቦች፦

•ምሳሌ የህጻናት ምግብ
•ኤልሞ የልጆች ምግብ
•ሂሩት የህጻናት አጃ
•ዘይነብ የህጻናት አጥሚት
•ተወዳጅ ገንቢ የህጻናት አጥሚት
•ተወዳጅ የህጻናት ሽሮ እና ፋሚሊ ሃይል ሰጭና ገንቢ የህጻናት ሽሮ

ቪንቶ፦

•ዴኮ
•እስፔሻል
•ዳና
•ቃና
•ላራ
•ዛጎል አቼቶ
•ናይስ አቼቶ
•አምቴሳ አቼቶ
•ማይ አቼቶ
•መስ አቼቶ እና ቫይኪንግ አቼቶ ምርቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው #ታግደዋል

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ታግደዋል

አራት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከግል ኮሌጆች ጋር በትብብር የማስተርስ ድግሪ መርሃ ግብር እንዳይሰጡ ማገዱን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ እግዳው የተጣለባቸው፦

√የጅማ ዩኒቨርሲቲ ABH ከሰተኘ ተቋም ጋር፣
√ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከዮም ኮሌጅ ጋር፣
√ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከናሽናል ኮሌጅና
√ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ ኮንቲነንታል የጤና ኢንስቲትዩት

@tsegabwolde @tikvahethiopia