TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መንገዶች ተከፍተዋል‼️

በአፋር የነበረው የመንገድ መዝጋት #አድማ #እንደተጠናቀቀና መንገዶች #እንደተከፈቱ ተገልጿል፡፡ ሶማሊ ነዋሪዎች የሚበዛባቸው ሶስት ቀበሌዎች ላይ እየተፈጠረ ያለውን #ግጭት ለማርገብ በሚል ከቀበሌዎቹ የአፋር ክልል ልዩ ሃይል #እንዲወጣ መደረጉን #በመቃወም ነበር የክልሉ ወጣቶች ተቃውሞ የጀመሩት፡፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴው ተጓዦችንም ሆነ ንብረቶቻቸው ላይ ምንም አይነት #ጉዳት_ያላደረሰ ነበር፡፡ከአዋሽ ወደትግራይ የሚወስደው መንገድ ትላንት ጠዋት 2 ሰዓት ላይ የተከፈተ ሲሆን ከመሃል አገር ወደምስራቅ ኢትዮጵያና ወደ ጂቡቲ የሚወስዱት መንገዶችም ተከፍተዋል፡፡

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቴዎድሮስ በእስር ላይ ይገኛል‼️

#ቴዎድሮስ_አዲሱ(ቴዲ ማንጁስ) በ80 ሺህ ብር ዋስ ቢፈቀድለትም #በሙስና_ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ ይገኛል፡፡

ቴዎድሮስ አዲሱ ከሀምሌ 28-30 ቀን 2010ዓ.ም በጀጅጋ እና አካባቢው ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥሮ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት ቢቀርብም ዐቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ምርመራውን ስላላጠናቀቀ እና በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቁ #ፍትሃዊ አለመሆኑንና የግለሰቡን ፍትህ የማግኘት መብት የሚጎዳ መሆኑን በማመን መዝገቡ እንዲዘጋ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በ80 ሺህ ብር ዋስ #እንዲወጣ ፈቅዶ ነበር፡፡

ሆኖም ግን ግለሰቡ በሌላ ወንጀል ከቀድሞው የሱማሌ ክልል ምክትል የትምህርት ቢሮ ኃላፊና ከኒያላ ኢንሹራንስ የጅጅጋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ጋር በመመሳጠር #በተጭበረበረ የኢንሹራንስ ዋስትና አፈጻጸም የቅድመ ክፍያ ቦንድ ከኢንሹራንስ እንዲጻፍ በማድረግ በውሉ ላይ ከተጠቀሰው ቅድመ ከፍያ ላይ ብር 15,306,303.3 ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ወጪ በማድረግ የወሰደ በመሆኑ ለትምህርት ቤቱ መፀሐፍቱን ሳያቀርብ ገንዘቡን ከጥቅም ተጋሪዎች ጋር በመከፋፈል ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል፡፡

መርማሪ ፖሊስ በቴዎድሮስ አዲሱ ላይ #በከባድ የሙስና ወንጀል የጀመረውን ምርመራው ለማከናወን የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት ተጠርጣሪው በእስር ቤት እንዲቆይ እና ለየካቲት 5 ቀን 2011 እንዲቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም ማረጋገጥ ከተቻለ ወታደራዊ ዕዙ ግዳጁን በሁለት ወር ውስጥ አጠናቅቆ ይወጣል፤ የማይረጋጋ ከሆነ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጭምር ሊታወጅ ይችላል!

በሃዋሳ ከተማ አሳቻ ሰዓትና ቦታ በመጠበቅ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶችና የሰዎች ማንንት ላይ ያተኮሩ ትንኮሳዎች ነዋሪው ተርጋግቶ እንዳይኖርና ስጋት ውስጥ እንዲገባ አድርጓል ሲሉ የከተማዪቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
 
ክልሉን እያስተዳደረ ካለው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አስፈፃሚ ዕዝ ጋር የከተማዪቱ ነዋሪዎች ተወካዮች በየተወያዩበት ወቅት ወታደራዊው ዕዝ እንዲያበቃና የመከላከያ ሠራዊትም ከከተማው #እንዲወጣ የጠየቁ ነበሩ።

በሌላ በኩል ደግሞ “የለም ሠራዊቱ መቆየት አለበት፤ ሰላም ያገኘነው ወታደራዊ ዕዙ፣ የመከላከያ ሠራዊትና ፌዴራል ፖሊስ ከተማዪን ከተቆጣጠሩ ወዲህ ነው” ያሉም ነበሩ። ሰላም ማረጋገጥ ከተቻለ ወታደራዊ ዕዙ ግዳጁን በሁለት ወር ውስጥ አጠናቅቆ እንደሚወጣ፤ የማይረጋጋ ከሆነ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጭምር ሊታወጅ እንድሚችል ዕዙ አስታውቋል።

Via #VOAamharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia