TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አብዲ ኢሌ⬇️

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር ባቀረቡት #የዋስትና ጥያቄ ላይ ለመወሰን #ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በዛሬው እለት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመርን ጨምሮ፥ ወይዘሮ ራሃማ መሐመድ፣ አቶ አብድራዛቅ ሰህኒ እና አቶ ሱልጣን መሐመድ፥ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ተረኛ የወንጀል ችሎት መቅረባቸው ይታወቃል።

በዚህ ወቅትም የተለያየ የጤና እክል እንዳለባቸው በመጥቀስ፥ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ የዋስትና ጥያቄ ይፈቀድልን ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ የዋስትና ጥያቄውን በመቃወም በተጠርጣሪዎቹ ላይ ለሚያካሂደው ምርመራ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱም አቶ #አብዲ_መሐመድ_ዑመር በቀረበው የዋስትና ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ #ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

©EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም ዩኒቨርሲቲ...

ተማሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ የዋስትና ጥይቄ አንስተዋል፤ አሁን ባለው ሁኔታ ትምህርት ለመቀጠል እንደማይችሉ አንስተዋል፦

በዩኒቨርሲቲው አመራሮች የቀረቡ የመፍትሄ ሀሳቦች፦

√የቀረውን ጊዜ በፌደራል እና በመከላከያ ሰራዊት አማካኝነት ደህንነታችሁ ተጠብቆ ትምህርታችሁን ጨርሱ

√እዚህ ካሉ አባቶች፣ የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም ከሀገር መከላከያ ሰራዊት አመራሮች ጋር ተወያይተን ወደየመጣችሁበት እንላካችሁ

• ተማሪው ከላይ ባሉት ሁለት ሀሳቦች ላይ ያዋጣኛል በሚለው ሀሳብ ላይ ውይይት አድርጓል።

• የተማሪው ውሳኔ ወደየመጣንበት እንመለስ የሚል ሲሆን አመራሮች ውሳኔ ነገ ጥዋት ይሰጣል ብለው ስብሰባውን ዘግተውት ነበር፤ ተማሪው በበኩሉ ዛሬ ውሳኔ ካልተሰጠን ከአዳራሽ አንወጣም በማለት ውሳኔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። የተቋረጠውም ስብሰባ በተማሪዎች ጥይቄ እንዲቀጥል ሆኗል። የሀይማኖት አባቶች ተማሪውን ቆመው ተመማፅነዋል።

√ተቋርጦ የቀጠለው ስብሰባ አሁንም ቢሆን ለተማሪው #ውሳኔ ሳይሰጥ #ለነገ ተዘዋዉሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia