TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#YayesewShimeles ከጥቂት ወራት በፊት ታስሮ የተፈታው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በዛሬው ዕለት መታሰሩ ተሰምቷል። ጋዜጠኛ ያየሰው ዛሬ ሀሙስ በፀጥታ ኃይሎች ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣባያ መወሰዱን ጠበቃው ገልፀዋል። ጠበቃው አቶ ታደለ ገ/መድኅን የካ አባዶ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ፖሊስ መምጣታቸውን በተናገሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል። ጠበቃው አቶ ታደለ ፤ ያየሰው…
#Update

በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ላይ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ላይ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

ጋዜጠኛ ያየሰው የተጠረጠረው " ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል " መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።

ጋዜጠኛ ያየሰው ትላንት በአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያየሰውን ዛሬ አርብ ግንቦት 19 ፍርድ ቤት ያቀረበው ሲሆን የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቆበታል።

ጋዜጠኛ ያየሰውን ወክለው በችሎቱ የተገኙት ጠበቃው ታደለ ገብረመድህን፤ የተጠየቀው የምርመራ ጊዜ ውድቅ ተደርጎ ደንበኛቸው በዋስትና እንዲለቀቅ ጠይቀዋል።

የግራ ቀኙን አስተያየት ያደመጠው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፤ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን የምርመራ ጊዜ በ4 ቀናት አሳንሶ 10 የምርመራ ቀናትን ፈቅዷል።

በጽህፈት ቤት በኩል የተካሄደውን የዛሬውን የችሎት ውሎ ጋዜጠኛ ያየሰው በአካል ተገኝቶ መከታተሉን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#JawarMohammed

ኦፌኮ በብሄራዊ ምክክር ላይ አልሳተፍም ብሏል ?

አቶ ጃዋር መሀመድ (ምክትል ሊቀመንበር) ፦

" ትንሽ የግንዛቤ ችግር አለ። እኛ እንደ ኦፌኮ አንሳተፍም አይደለም ያልነው ቅድመ ሁኔታዎችን ነው ያስቀምጥነው። ብሄራዊ መግባባት (National Dialogue) የኦፌኮ አጀንዳ ነው።

... ስለዚህ ኦፌኮ የብሄራዊ ድርድርን ወይም የብሄራዊ መግባባትን አይፈልግም የሚለው የተሳሳተ አመለካከት ነው፤ እንፈልጋለን፤ አሁንም ቢሆን እንፈልጋለን ፤ አሁንም ቢሆን ለሀገራችን የሚጠቅመው እሱ ነው ብለን ነው የምናምነው።

ነገር ግን ብሄራዊ መግባባት ሲባል ፕሮሰስ አለው ፤ ብሄራዊ መግባባት በሁለት ደረጃ ነው በአንድ ሀገር ውስጥ ሊካሄድ የሚችለው።

አንዱ የፖለቲካ ልዩነቶች ወደ ጦርነት እንዳያመሩ የቅድመ ጦርነት ንግግር የሚባል ነው የፖለቲካ ልዩነቶች ፣ የፖለቲካ ሽኩቻዎች ሀገርን እና የፖለቲካ ኃይሎችን ወደ ጦርነት እንዳያስገቡ በንግግር እና በድርድር ለመፍታት የሚደረግ ብሄራዊ መግባባት አንድ አለ፤ ያ ሳይደረግ እድል አምልጦ ሀገር ወደ ጦርነት ከገባች በኃላ ደግሞ ጦርነት ቆሞ ከጦርነት በኃላ ለጦርነት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችም ሆኑ በጦርነት የተፈጠሩ ክስተቶች ለሌላ ጦርነት እንዳይጋብዙ ከስር መሰረቱ ለመፍታት የሚደረግ ክንውን ነው ፤ ይሄን መገንዘብ አስፈላጊ ነው።

ብሄራዊ መግባባት በጦርነት መካከል ሊካሄድ አይችልም። ሀገራችን በጦርነት መሀከል ነች፤ 2019/20 መጀመሪያ አካባቢ ቢሆን 2019/18 ጥሩ ጊዜ የነበረው ለውጡ እንደመጣ የመጀመሪያ ወራት መጀመር ነበረበት ያ አምልጧል አሁን ጦርነት ውስጥ ነው ያለነው።

ብሄራዊ መግባባት ሲባል የመጀመሪያው criteria ሁሉንም ያሳተፈ መሆን አለበት።

በተለይ ጦርነት ከተገባ ፣ ከሁሉም የበለጠ ብሄራዊ መግባባት ውስጥ መግባት እና መሳተፍ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባው በጦርነት ውስጥ የተሳተፉት ቡድኖች ናቸው። ጦርነት እየተካሄደ እነዚህ በጦርነት የተሳተፉ ቡድኖች ማሳተፍ አልቻልም። Legally ሆነ በ Security wise ማሳተፍ አይቻልም። ይህ ስለሆነ ዋናው እኛ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ብሄራዊ መግባባት ጥሩ ነው መንግስት ረጅም ጊዜ አልሰማም ብሎ አሁን የብሄራዊ መግባባት ማለቱ ጥሩ ነው ደስ ብሎናል ነገር ግን ይሄን ነገር በአግባቡ እንስራው ስለዚህ ጦርነት ይቁም ፤ ጦረኞቹ ሙሉ በሙሉ ይታረቁ አይደለም እያልን ያለነው ብሄራዊ መግባባቱ ላይ ሊታረቁ ይችላሉ ነገር ግን active fighting እንዲቆም ማድረግ በሰሜንም ፣ በትግራይ ድምበርም ፣ በቤኒሻንጉልም፣ በኦሮሚያም በተለያየ አካባቢ እየተደረገ ያለው ጦርነት መጀመሪያ መቆም አለበት... "

#ያንብቡ ➡️ https://telegra.ph/Jawar-Mohammed-05-27
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተከሰሰው ተማሪ በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ቤት ወሰነ።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ ግንቦት 19/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን በወንጀል ህግ ቁጥር 5391-ሀ ጥፋተኛ አድርጎታል።

አቃቤ ህግ የቅጣት ማክበጃ የወንጀል ህግ ቁጥር 84 እና 86 መሠረት አድርጎ በደረጃ 38 ይወሰንልኝ ብሎ አቅርቧል።

የተከሳሽ ብሩክ በላይነህ ጠበቃ ተከሳሹ ይኖርበት በነበረው አካባቢ ጥሩ ፀባይ የነበረውና በበጎ አድራጎት ክበባት ተሳታፊ እንደነበር የፅሁፍ ማስረጃ በማቅረብ እንዲሁም ወንጀሉን የፈጸመው በወጣትነት ስሜት በመነሳሳት መሆኑን በመጥቀስ የቅጣት ማቅለያ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን የቅጣት ሃሳብ ካዳመጠ በኋላ ተከሳሹ ጥፋተኛ ከተባለበት እና ከሚያስቀጣው (18 ዓመት) አንድ ዓመት በመቀነስ በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ጥር 23/2014 ዓ.ም የተገደለችው የ20 ዓመቷ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ ነበረች፡፡

መረጃውን ያደረሱን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ መርኪያ መንገሻ ናቸው።

More : @tikvahuniversity (ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ)

@tikvahethiopia
#Update

የ " ፍትህ መጽሔት " ማኔጂግ ዳሪክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ " የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በህዝብ ዘንድ አመኔታ ለማሳጣትና ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት ወንጀል " መጠርጠሩን መርማሪ ፖሊስ ዛሬ ለፍ/ቤት ገልጿል።

ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገን በተጠረጠረበት ሁከትና አመጽ ማስነሳት ወንጀል በምስክር ለማስመረጥና የምስክር ቃል ለመቀበል ተጨማሪ ማስረጃ ለመሰብሰብ እና የምርመራ ስራውን አጠናክሮ ለመቅረብ 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንዲሰጠው ችሎቱን ጠይቋል።

የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ መከላከያን መተቸት እምነት ማሳጣት አለመሆኑን ጠቅሶ ተከራክሯል።

በምስክር ማስመረጥ ለተባለውም ቢሆን ተመስገን አገር የሚያውቀው በመሆኑ ማስመረጥ ጥያቄው ተገቢ እንዳልሆነ ገልጿል።

ጠበቃው አክሎም ጋዜጠኛ ተመስገን የሚሰራበት ሚዲያ ፍቃድ ያለው ህጋዊ ተቋም እንደመሆኑ ወንጀል ሰራ እንኳ ቢባል በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ እንጂ በጊዜ ቀጠሮ ሊጠየቅ እንደማይገባ ተከራክሯል።

ፖሊስ በዩቱዩብ ቃለመጠይቅ እያደረገ ከሌሎች አካላት ጋር ሁከትና አመጽ የማነሳሳት ስራ እየሰሩ ነው ሲል ባቀረበው የመነሻ ምርመራ ሪፖርትን በተመለከተ ጋዜጠኛ ተመስገን ከ4 አመት ወዲህ ምንም አይነት ከማንም ጋር ቃለመጠየቅ እንዳላደረገ ጠበቃ ሄኖክ አብራርቷል።

 በሚሰሩበት ሚዲያ የሀገር መከላከያ ተቋምም ቢሆን ተተችቻለው በህዝብ ዘንድ እምነት አጣሁ ብሎ አለመቅረቡን  ጠቅሰው ቢቀርብ በመገናኛ ብዙሀን አዋጅ መሰረት በሚሰራበት ሚዲያ ማስተካከያ ከማድረግ እንደማይታለፍ መከራከሪያ ነጥቡ ጠቅሷል።

ያንብቡ ⬇️
https://telegra.ph/Tarik-Adugna-05-27

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
#ፌዴራል_ፖሊስ_ወንጀል_ምርመራ

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ሙሊሳ አብዲሳ የሰጡት ማብራሪያ ፦

" ህግ ማስከበር ሲባል ብሄርን አይለይም፤ ሃይማኖትን አይለይም ፤ የፖለቲካ status አይለይም ፤ የሚዲያ አክቲቪስት ማንም ማንም ይሁን የSocial Status ፣ ሃይማኖቱ ምንም መሰረት አያደግም።

ህግ ለሁሉም እኩል ነው። እንደ ፖሊስ ሞያዊ ነፃነቱን ጠብቀን የምርመራ ስራ ጥቆማ ሲደርሰን በየትኛውም አካል ላይ ህግ የማስከበር ስራ እየተሰራ ነው የሚገኘው።

እንደሚታወቀው በአሁን ሰዓት ብዙ የሚዲያ ተከታይ ያላቸው ሰዎች ብሄርን ከብሄር የሚያጋጩ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ ፣ ጥርጣሬን የሚፈጥሩ የህዝቦቻችንን ፣ አጠቅላይ የኢትዮጵያን ህዝብ አብሮነት የሚፈታተኑ እነሱ ጥቅም የሚያገኙበትን በሚዲያ ዘመቻ የሚያደርጉትን በሽብር ድርጊት ውስጥ የተሳተፉትን ሰዎች በማስረጃ ላይ ሆነን መረጃ በመሰብሰብ በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ወደ ህግ እያቀረብን ነው።

ስለዚህ የሆነ ሚዲያ ወይ ጋዜጠኛ የሆነ ምንም ቢሆን እንደ defense ሊቀርብ አይችልም። በወንጀል ውስጥ የተሳተፈ መረጃ የተገኘበት ማንኘውም ሰው ላይ እርምጃ ይወሰዳል፤ በህግ ይጠየቃል፤ ግልፅ በሆነ ነፃ በሆነ ፍርድ ቤት አቅርበን ምርመራ ስራ እንሰራለን።

ስለዚህ በአሁን ሰዓት የሚዲያ ስራ ላይ የተሳተፉ ሰዎች እሱን እየተጠቀሙ አጠቃላይ stability እንዳይኖር የሆነ title እየሰጡ እንደ ገቢ ምንጭ የኢትዮጵያ ህዝብ ያልተረዳው ነገር እነኚህ አክቲቪስት የተባሉ ታሰሩ የተባሉ ግለሰቦች እንደ ገቢ ምንጭ የሚጠቀሙት አይነት ነው ያለው።

በምርመራ እንዳገኘነው አንድ ግለሰብ ከ4 ዩትዩበሮች ጋር ውል አስሯል፣ ከአንዱ ዩትዩበር 25 ሺህ ብር ነው የሚከገለው በአንድ ጊዜ እስከ 100 ሺህ ነው የሚከፈለው፤ ይሄን ለማድረግ ተመልካች እንዲያገኝ ለማድረግ ብሄርን ከብሄር የሚያጋጭ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጭ ፣ ወይም የመንግስትን ተቋም ፣ ወይም የመንግስትን ተሿሚዎች በሚያሸማቅቅ መልኩ ግልፅ በሆነ መልኩ characterize በማድረግ title እየሰጡ እንዲህ እያደረጉ ተመልካችን፣ like , share በብዛት እንዲያገኙ ብዙ ነገር በማድረግ ይሄን መሰረት በማድረግ destabilize በማድረግ የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶችን፣ የሃሰት የውሸት ፕሮፖጋንዳዎችን በመልቀቅ ህዝቦች አብረው እንዳይኖሩ ሀገሪቱ በሰላም ተረጋግታ እንዳትኖር አጠቃላይ የማወክ ስራ እና ጥርጣሬ በሚፈጥር መልኩ ጥላቻን በውሸት ዘመቻ እያደረጉ ህዝቡ ላይ ይሄን እየጫኑ ለራሳቸውን የገቢ ምንጭ አድርገው ሀገሪቷን አደጋ ላይ ለመጣይ የሚሰሩ አካላት ናቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ይሄንን ደግሞ ፖሊስ ህግን መሰረት በማድረግ ፍርድ ቤት በማቅረብ የጊዜ ቀጠሮ በመጠየቅ በራሳቸው ፍላጎት በሚፈልጉት ጠበቃ ተወክለው በቤተሰቦቻቸው እየተጠየቁ ይሄን የምርመራ ስራ ፣ የህግ ማስከበር ስራ በደንብ እየተሰራ ነው።

ስለዚህ በአጠቃላይ ማንኛውም ሰው ከህግ በታች ነው።

ከህግ በታች እስከሆነ ድረስ ጥቆማ የቀረበበትን እንደፖሊስ ሙያን መሰረት አድርጎ የህግ የማስከበሩን ስራ ማንኛውም ሰው ላይ በየትኛውም ላይ ብዙ እሱን የሚከተል ሰው ሊኖር ይችላል ከዚህ በፊት እንደተደረገው ፣ የሃይማኖት ሰው ሊሆን ይችላል፣ ማንኛውም ሰው ሊሆን ይችላል ዋናው መሰረት የህግ ስህተት አለ ? ወይስ የለም ? የሚለው ነው። ስለዚህ እስካሁን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ስም ብዙ ነገሮች ተችለዋል በአሁን ሰዓት ግን የለየለት የሽብር ስራ ፣ የሽብር ፈጠራ ፣ ሀገርን የማፍረስ ስራ ፣ ህግ የሌለ እስከማስመሰል ፣ የፍትህ ተቋማት እርምጃ መውሰድ አይችሉም የሚያስብል ደረጃ ላይ ደርሶ ሀገርን የማፍረስ ተልዕኮ ላይ እየሰሩ ያሉት አካላት ላይ የህግ የበላይነት ለማስከበር ከምን ጊዜውም በላይ የፌዴራል ፖሊስ ከሌሎች የፍትህ ተቋማት ጋር በመሆን የምርመራ ስራን እየሰራ ይገኛል። "

@tikvahethiopia
#EHRC

ትላንት ለእስር የተዳረጉትን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ አጠቃላይ እስካሁን የታሰሩ ጋዜጠኞች / የሚዲያ አካላትን ቁጥር 16 አድርሶታል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ " የሚዲያ ባለሙያዎች መታሰራቸው ከመገናኛ ብዙሃን ህጉ ጋር የሚጻረርና መዘዙ ከመገናኛ ብዙሃን እና ሃሳብን ከመግለጽ የዘለለ በመሆኑ አሳሳቢ ነው " ብለዋል

ከመገናኛ ብዙሀን ህግ ጋር በተጻራሪ ከፍርድ በፊት ረዘም ላለ ጊዜ አስሮ ማቆየት፣ ታሳሪዎች ያሉበትን ቦታ አለመግለጽ እና መደበኛ ባልሆነ እስር ቤት ማሰር ሁኔታውን እንደሚያባብስ በመግለፅ ሁሉም የሚዲያ አካላት በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ኮሚሽኑ ሁኔታውን መከታተሉን እንደሚቀጥልም አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
" Galatoomaa Tour "

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ ወደ በሰኔ እና ሃምሌ ወር 2022 ወደ #ሰሜን_አሜሪካ እና #አውሮፓ እንደሚጓዙ ታውቋል።

አመራሮቹ ጉዟቸውን " Galatoomaa Tour " በሚል የሚያደርጉ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች ከደጋፊዎቻቸው ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጉዞውን በተመለከተ እስካሁን በሁለቱ ወራት የሚያዳርሷቸውን ከተሞች እና ቀናት ይፋ ከመሆን በዘለለ ለጊዜው በዝርዝር ይፋ የተደረገ መረጃ የለም።

@tikvahethiopia
ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ታሰረ።

ከጥቂት ወራት በፊት ታስሮ ከእስር የተፈታው የቀድሞ የአውሎ ሚዲያ ባልደረባ አሁን ላይ " አልፋ ቲቪ " የተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ መስራች እና አዘጋጅ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው በፀጥታ ኃይሎች መታሰሩን ጠበቃ ታደለ ገብረመድህንን ዋቢ አድርጎ አዲስ ስታንዳር አስነብቧል።

የጋዜጠኛውን መታሰር ባለቤቱ ሄለን አባተ አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል ፤ ትላንት የፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ ሰቦንቱ አህመድ በአዲስ አበባ ፖሊስ የታሰረች ሲሆን (በለቡ ፖሊስ ጣቢያ ነበረች) ዛሬ ወደ ቢሾፍቱ መወሰዷን የጣቢያው ዋና ዳይሬክተር ለሚ ታዬ መናገራቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ አስነብቧል።

ሰቦንቱ ትላንት በፖሊስ የተያዘችው አመሻሽ ላይ ከስራ ቦታዋ ስትወጣ ሲሆን በቁጥጥር ስር ያዋሏት ፖሊሶች የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመያዛቸውንም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

አክለውም፤ ትላንት ለቡ ፖሊስ ጣቢያ እያለች አነጋግረዋት እንደነባርና የተያዘችበት ምክንያት ምን እንደሆነ እንዳልተገለጸላት ፍርድ ቤትም እንዳልቀረበች ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ " አስታውቀዋል።

ጋዜጠኛዋ ዛሬ ወደ ቢሾፍቱ ከተማ እንድትወሰድ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
#ባልደራስ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሩ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በባህር ዳር ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል።

ፓርቲው አመራሩ በአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩን ነው ያመለከተው።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከጥቂት ወራት በፊት ከረጅም ጊዜ እስር መለቀቃቸው የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC ትላንት ለእስር የተዳረጉትን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ አጠቃላይ እስካሁን የታሰሩ ጋዜጠኞች / የሚዲያ አካላትን ቁጥር 16 አድርሶታል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ " የሚዲያ ባለሙያዎች መታሰራቸው ከመገናኛ ብዙሃን ህጉ ጋር የሚጻረርና መዘዙ ከመገናኛ ብዙሃን እና ሃሳብን ከመግለጽ የዘለለ በመሆኑ አሳሳቢ ነው " ብለዋል ከመገናኛ…
#EHRC

የፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛዋ ሳቦንቱ አህመድ እና የአልፋ ቲቪ የማህበራዊ መገናኛ መስራች እና አዘጋጅ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው እስር አጠቃላይ የታሰሩ የሚዲያ ሰዎችን ቁጥር 18 እንዳደረሰው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በኢትዮጵያ የሚድያ ህግ በመገናኛ ብዙኀን አውታሮች ተፈፅመዋል ለሚባሉ የህግ ጥሰቶች በምንም መንገድ ለፍርድ ሳይቀርቡ ማሰር ክልክል መሆኑን ገልፀው ሁሉም የታሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች ከእስር እንዲፈቱ በድጋሚ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ በፌደራል ፖሊስ አባላት ተያዘች።

" ሮሃ ሚዲያ " የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነችው መዓዛ መሐመድ ዛሬ ጠዋት በፖሊስ ተይዛ መወሰዷን የስራ ባልደረባዋ እና ጓደኛዋን ዋቢ አድርጎ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ " ዘግቧል።

የጋዜጠኛዋ እስር በኢትዮጵያ ከሰሞኑ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞችን ቁጥር 19 አድርሶታል።

ጋዜጠኛ መዓዛ የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ በለበሱ 2 ፖሊሶች እና የሲቪል ልብስ ባደረጉ 3 የጸጥታ ኃይሎች የተያዘችው በአዲስ አበባ ሰሚት ኮንዶሚኒየም ከሚገኝ የእርሷ መኖሪያ ቤት እንደሆነ ጋዜጠኛ ምስራቅ ተፈራ ገልጻለች።

የጸጥታ ኃይሎቹ መዓዛን ለ " ጥያቄ እንፈልጋታለን " በሚል ምክንያት ቢይዟትም ወዴት እንደሚወስዷት ለመናገር ፈቃደኛ እንዳልነበሩ ጋዜጠኛዋ ማስረዳቷን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር አስነብቧል።

ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ ከወራት በፊት ለእስር ተዳርጋ መፈታቷ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" አሜሪካ ዩክሬንን ከመደገፏ በፊት የትምህርት ቤቶቿ ደኅንነት ላይ ታተኩር " - ትራምፕ

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ የትምህርት ቤቶችን ደኅንነት ለማረጋገጥ የምታወጣው የገንዘብ ድጋፍ ለዩክሬን ከሚቀርበው እርዳታ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ይህ የትራምፕ ንግግር የተሰማው በቴክሳስ ግዛት በት/ቤት ውስጥ 19 ህጻናት 2 መምህራኖቻቸው በአንድ በታጠቀ ወጣት ከተገደሉ በኋላ ነው።

የጦር መሣሪያን በተመለከተ እየተካሄደ በሚገኝ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ትራምፕ፣ አሜሪካ ወደ ዩክሬን ቢሊዮን ዶላሮችን መላክ ከቻለች " በአገራችን ውስጥ ያሉ ልጆቻችንን ደኅንነት ለመጠበቅ እንዲውል የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን" ብለዋል።

" በአፍጋኒስታን እና ኢራቅ ትሪሊዮን ዶላሮችን ብናፈስም ጠብ ያለ ነገር ግን ያለም” ያሉት ትራምፕ " የተቀረውን ዓለም ከመገንባታችን በፊት በአገራችን ለልጆቻችን ደኅንነቱ የተጠበቀ ትምህርት ቤት ልንገነባ ይገባል” ሲሉ አክለዋል።

በዚህ ወር መግቢያ ላይ የአሜሪካ ም/ቤት ለዩክሬን ወታደራዊ እርዳታ የሚውል 40 ቢሊዮን ዶላር እንዲላክ ወሰኗል። ጦርነቱ ከተነሳ ጊዜ ጀምሮ 54 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን አጽድቋል።

ትራምፕ የጦር መሣሪያ ቁጥጥርን የተቃወሙ ሲሆን ሰላማዊ አሜሪካውያን ራሳቸውን "ከመጥፎ" ሰዎች እንዲከላከሉ ሊፈቀድላቸው ይገባል ብለዋል።

በጦር መሳሪያ ላይ ቁጥጥር ከማድረግ ይልቅ በት/ቤቶች ከላይ እስከ ታች የሚዘረጋ የደኅንነት ሥርዓት ሊኖር ይገባል ብለዋል።

በት/ቤቶች መግቢያ ላይ ብረት ነክ ነገሮችን የሚለዩ መሣሪያዎችን ማስቀመጥ እና ቢያንስ 1 የታጠቀ ፖሊስ እንዲኖር ማድረግን ጨምሮ የተጠናከረ ጥበቃ ሊኖር ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ እንዳይሆን እንቅፋት የሆኑት ዲሞክራቶች ናቸው ሲሉ ከሰዋል።

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia