TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

በአማራ ክልል የጦር መሳሪያ ምዝገባ ቀን ተራዝሟል።

የመሳሪያ ምዝገባው የተራዘመው ለሶስት ቀናት ማለትም እስከ ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ/ም ሲሆን በተለያየ ምክንያት ያላስመዘገቡ ግለሰቦች እድል ያገኛሉ ተብሎ ስለታሰበ ነው ተብሏል።

የተራዘመበት ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር በመኖሩ በበቂ ጊዜያት ማስመዝገብ ያልቻሉ እና በተሳሳተ መረጃ የተደናገሩ ግለሰቦች እንድል እንዲያገኙ በማሰብ ነው ተብሏል፡፡

ከምዝገባው በኋላ ሕገ ወጥ የመሳሪያ እንቅስቃሴ ላይ ቁጥጥር ስለሚኖር ሕዝቡ ያለውን መሳሪያ ያለምንም አይነት የመሳሪያ ገደብ ማስመዝገብ እና መታወቂያውን መያዝ እንደሚኖርበት ተገልጿል።

በቀጣይ የክልሉ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ከመሳሪያ አጠቃቀም፣ አያያዝ እና ኅላፊነት አንጻር ሥልጠና ይሰጣል ተብሏል፡፡

(የአማራ ክልል ሚሊሻ ፅ/ቤት)

@tikvahethiopia
#YayesewShimeles

ከጥቂት ወራት በፊት ታስሮ የተፈታው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በዛሬው ዕለት መታሰሩ ተሰምቷል።

ጋዜጠኛ ያየሰው ዛሬ ሀሙስ በፀጥታ ኃይሎች ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣባያ መወሰዱን ጠበቃው ገልፀዋል።

ጠበቃው አቶ ታደለ ገ/መድኅን የካ አባዶ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ከአዲስ አበባ ፖሊስ መምጣታቸውን በተናገሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል።

ጠበቃው አቶ ታደለ ፤ ያየሰው ላለፉት 2 ዓመታት ትምህርት ላይ ማሳለፉን አስታውሰው፤ በአሁኑ ሰዓት በጋዜጠኝነት ሥራ ላይ አይገኝም ብለዋል፤ በተያዘበት ወቅትም ለመያዙ ምንም አይነት ምክንያት እንዳልተሰጠው አስረድተዋል።

ያየሰው በአሁኑ ወቅት በ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኝ ሲሆን በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት ይቀርባል ብለው እንደሚጠበቅ ጠበቃው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#RICA

አሽከርካሪዎች በ5 በመቶ የኮሚሽን ክፍያ የሚሰሩበት የኤሌክትሮኒክስ ትራንስፖርት ሞባይል መተግበሪያ ስራ ሊጀምር መሆኑ ተሰምቷል።

ይህ አገልግሎት የሚጀምረው በሪካ ቴክኖሎጂ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲሆን ድርጅቱ የሞባይል መተግበሪያዎችን በማበልጸግ እና በማዳበር ፤ የበይነመረብ ግብይትን ማመቻቸት ላይ የሚሰራ ነው።

በዛሬው እለት ሪካ ድርጅቱ ስላበለጸጋቸው የሞባይል መተግበሪያ እና አገልግሎቶቹን በተመለከተ ትውውቅ አድርጓል።

ከመተግበሪያዎቹ መካከል ሪካ ትሪፕ እና ሪካ ሾፒንግ የተሰኙት በቅርቡ ስራ የሚጀምሩ ናቸው ተብሏል።

ሪካ ትሪፕ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ መተግበሪያ ሲሆን አሽከርካሪዎች እስከ ሐምሌ 10/ 2014 ዓ.ም ድረስ ያለ ኮሚሽን ክፍያ የሚሰሩበት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ከሐምሌ 10 በኋላ በ5 በመቶ የኮሚሽን ክፍያ እንደሚሰሩ ተገልጿል።

መነሻ ዋጋ 95 ብር እንዲሁም በኪ.ሜ 10 ብር ተመን አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቋል።

ሌላው ሪካ ሾፒንግ የተሠኘው የሞባይል መተግበሪያ ማንኛውም ግለሰብ እና ድርጅት ምርትና አገልግሎቱን ለሽያጭ የሚያቀርብበት እንዲሁም የሚሸምትበት የበይነመረብ ግብይት ስርአት ሲሆን ሐምሌ 10 ቀን 2014 አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሏል።

Via ኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

‘ US Embassy Addis Ababa ’ በሚል ስም ከ127 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የቴሌግራም ቻነል " አሜሪካ ኤምባሲ በጦርነት የተጎዳዉን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመደገፍና ከክፍለዘመን የዘለቀዉን የአሜሪካና የኢትዮጵያን ወዳጅነት ለማጠናከር ለ20 ሺህ ኢትዮጵያዉያን በአሜሪካ የስራ ዕድል ፈጥሯል " ብሎ መረጃ አጋርቷል።

የዕድለኞች የትራንስፖርት ፤ የመኖሪያ ቤትና የመኪና ወጪ በኤምባሲዉ እንደሚሸፈንም ጽፏል።

ስለዚህም የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን በቴሌግራም ቻነሉ አማካኝነት እንዲመዘገቡና ተመዝጋቢዎችም ሙሉ ስማቸዉን፤ ስልክ ቁጥራቸዉን እንዲሁም አድራሻና መሰል ግላዊ መረጃዎቻቸዉን እንዲልኩም ይጠይቃል።

ይህን በተመለከተ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እየተሰራጨ ያለድ መረጃ ሀሰተኛ እና ሰዎችን ለማጭበርበር እንደሆነ ገልጿል።

ኤምባሲዉ ለኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ አጣሪ ድረገፅ በሰጠው ቃል፤ በአሜሪካ የስራና የቪዛ ዕድሎችን በተመለከተ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተጋሩ መሆኑን አስታዉቋል።

" የአሜሪካ መንግስት በኢሜይል፤ ፌስቡክ ሚሴንጀር፤ ቴሌግራም ወይም ሌላ ማህበራዊ ትስስር ገጾች አማካኝነት ግላዊ መረጃዎችን አይጠይቅም " ሲል ኤምባሲው አስረድቷል

ትክክለኛ የስራ ዕድሎችን በድረ-ገጹ ላይ እንደሚለጥፍና ሰዎች ለአጭበርባሪዎች እንዳይጋለጡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኤምባሲዉ ጠይቋል።

Via Ethiopia Check

@tikvahethiopia
#JawarMohammed

አቶ ጃዋር መሀመድ (የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር) ከእስር ከተፈቱ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ " ኡቡንቱ ቲቪ " ለተሰኘ የማህበራዊ መገናኛ Exclusive ቃለ ምልልስ ሰጥተዋል።

በዚሁ ቃለ ምምልስ ወቅት አቶ ጃዋር ከተጠየቁት ጥያቄዎች አንዱ እሳቸውን በተመለከተ ሲናፈሱ የነበሩ አሉባልታዎችን እንዲያጠሩ ነው " አቶ ጃዋር ከገዢው ፓርቲ ጋር መስራት ጀምሯል፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝቷል የተፈታውም ለዚህ ነው ፤ አሁንም እየሰራ ያለው የመንግስትን ስራ ነው " ስለሚባሉት ጉዳዮች ግልፅ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ጃዋር መሀመድ ፦

" እኔም ሰማቸዋለሁ አሉባልታዎቹን ። እኔ ከማንም ጋር የግል ቁርሾ የለኝም። የታሰርኩትም ቢሆን በፖለቲካ ልዩነት እንጂ በግል ፀብ አይደለም።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር አልተገናኘንም፤ ሊያገኘኝ ከፈለገ ግን ሁሌም ዝግጁ ነኝ። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ብቻ ሳይሆን / ከዐቢይ ጋር ብቻ ሳይሆን ከመሮም ጋር፣ ከደብረፅዮንም ጋር ከሁሉም በአሁን ወቅት በሀገራችን ባለው ግጭት ውስጥ እየተሳተፉ ካሉ ኃይሎች ጋር ተገናኝቶ ሀገራችንን ከጦርነት አስወጥቶ ወደ ሰላም እና ልማት ለመመለስ እድሉ ከተገኘ ከማናቸውም ጋር ለመስራት፣ ከማናቸውም ጋር ለመተባበር ፣ ከማናቸውም ጋር ለመነጋገር በማንኛውም ቦታ እና ሁኔታ ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ።

እኔ ማልፈቅደው ግን ከማናቸውም ጋር አብሬ ጦርነት ማፋፋም አልፈልግም፤ ከማናቸውም ጋር።

ሁሉም በጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ይሁኑ በጦርነት ውስጥ እያልተሳተፉ ያሉ ምሁራን እና ሊህቃን ወደ ሰላም ጠረጴዛ መምጣት አለባቸው ብዬ አምናለሁ፤ ከአንዳቸውም ጋር ግላዊ ጠብ የለኝም።

ስለዚህ ገዥው ፓርቲ ሀገር እየገዛ ነው ያለው ፤ ሀገር እያስተዳደረ ነው ያለው ፣ ሀገሪቷ ለገባችበት ችግር ትልቁን ድርሻ የሚወስደው ገዢው ፓርቲ ነው፤ እንደመሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው ፤ ወደመፍትሄ የምንገባ ከሆነ የእነሱ ተሳትፎ፣ የእነሱ ፍቃደኝነት ወሳኝ ነው።

ስለዚህ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ አመራርም እንደ እዚህች ሀገር ዜጋም በሰላም ጉዳይ ላይ የሀገራችንን እጣፈንታ ወደፊት ማስተካከል ላይ ከገዢው ፓርቲም ጋር ሆነ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ሆነ፣ የተለያዩ ድርጅቶች ከሚመሩ ቅድም እንዳልኩት ከደብረፅዮን ሆነ ፣ ከፃድቃን ሆነው፣ ከመሮም ሆነ፣ ከገመቹ ሆነ፣ ከተፈራ ማሞ ሆነ ፣ ከይልቃል ከፋለ ጋርም ሆነ ከማንኛውም ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ፤ የሀገራችን አመራርም ለዚህ መዘጋጀት መቻል አለበት።

ሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ለምን ከእከሌ ጋር ተነጋገርክ፣ እከሌ ሳይጣን ነው እከሌ መልአክ ነው በማለት እንደማያዋጣ ላለፉት 4 ፣ ላለፉት 2 ዓመታት ግልፅ ሆኗል።

ስለዚህ አሁንም ደግሜ የምለው ከማንኛውም የፖለቲካ ኃይል ጋር ፣ ከማንኛውም የፖለቲካ አመራር ጋር ህዝባችንን አሁን ከገባበት መቀመቅ እና ሰቆቃ ለማውጣት መስራት ያስፈልጋል።

እዚህ ላይ ግልፅ ማድረግ የምፈልገው ከማኛውም ኃይል ጋር እንሰራለን እንደ ድርጅትም እንደ ግለሰብም እንደ አመራርም፤ ሀገራችንን እና ህዝባችንን ወደ ሰላም መንገድ ወደ ልማት እንዲመለሱ ባለኝ እውቀት እና ባለኝ ተሰሚነት መጥቀም እፈልጋለሁ።

ነገር ግን ለማንም ድርጅት ሆነ ግለሰብ መጠቀሚያ መሆን አልፈልግም ፤ ለማንም የጦር ማገዶ መሆን አልፈልግም ፣ የማንንም አንባገነናዊ አካሄድን፤ የማንም ጦረኛ አካሄድን መደገፍ አልፈልግም።

ወደ ሰላም መምጣት ከሚፈልግ አካል ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ፣ ይሄ ደግሞ ኩነኔ አይደለም ይሄ ትክክለኛ ነው ብዬ የማምነው ፤ ስለዚህ ጦርነቱ መቆም አለበት ጦርነት ቆሞ ወደ ድርድር መምጣት አለብን ቴክኒካል ነገሮች መነሳት አለባቸው ስለዚህ ለመነጋገር ጋሬጣ ሆነው ያሉ ነገሮች ተሰባብረው ድልድይ ተመስርቶ ሁላችንም ወደመነጋገር መግባት አስፈላጊ ነው። "

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ ፦

➡️ #አሜሪካ - በኒውዮርክ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። ሰልፉ በመሳሪያ የገዙ ጥቃቶችን ለማውገዝ የተካሄደ ነው። ሰልፉ የተካሄደው አንድ ወጣት በቴክሳስ ሮብ በሚሰኝ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 19 ህፃናት ተማሪዎችን እና 2 መምህራንን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ ከቀናት በኃላ ነው።

➡️ #ስፔን - በሰሜናዊ ስፔን ላ ሪዮጃ ክልል በባዮዲዝል ማምረቻ ፋብሪካ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 2 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

➡️ #የመን - በየመን አደን ከተማ ሰዎች በሚበዙበት በተጨናነቀ ገበያ ላይ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ 4 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል፤ እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዳለሁ ብሎ ብቅ ያለ የለም።

➡️ #ሱዳን - ከወራት በፊት በሱዳን የተካሄደውም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ አሁንም ያልበረደ ሲሆን ትላንትና በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በካርቱም ጎዳናዎች ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል። የጥቅምቱ መፈንቅለ መንግስት ሀገሪቱን ወደ ፖለቲካዊ ቀውስ አስገብቷል።

➡️ #ጣልያን - የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ የሩሲያው ፕሬዜዳንህ ፑቲን አሁን ላይ በዓለም የሚየው የምግብ ችግር "በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ነው " ብለው እንደነገራቸው ተናግረዋል። የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ከጀመረ አንስቶ ምዕራባውያን ሀገራት ሩስያ ላይ እጅግ ከፍተኛ የሚባሉ ማዕቀቦችን እየጣሉ እንደሆነ ይታወቃል። ለእነዚህ ማዕቀቦችም ሩስያ ምላሽ ከመስጠት ወደኃላ አላለችም።

➡️ #ቱርክ #ፈረንሳይ - የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ከፈረንሳይ ፕሬዜዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የስውዲን እና ፊንላንድ ለNATO አባልነት ባቀረቡት ማመልከቻ፣ በዩክሬን ሩስያ ጦርነት፣ በቀጠናዊ ጉዳዮች እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ተገናኝተው መክረዋል።

@tikvahethiopia
እናት የፓርቲ 4 አመራሮቹ የገቡበትን ማወቅ እንዳልቻለ ገልጿል።

ፓርቲው በአማራ ክልል መንግስት እየወሰደ ያለውን የሰሞኑን እርምጃ "አፈና" ሲል ገልጾ በዚህ ሂደት አመራሮቹ እንደታፈኑበት ገልጿል።

ፓርቲው በስም ገልጾ በፎቶ አስደግፎ በላከልን መግለጫ፦

1. አቶ ሙሉጌታ የሺጥላ:- የሰቆጣ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ መምህር፣ የእናት ፓርቲ የሳይንት ፪ ምርጫ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የነበረ መታፈኑንና ያለበትን ኹኔታ ማወቅ እንዳልቻለ።

2. አቶ ታደለ ጋሸ:- በአዊ ዞን፣ ጓጉሳ ሽኩዴድ/ቲሊሊ/ከተማ የፓርቲው ም/ሰብሳቢ ከባለቤቱ ዘንድ ክርስትና ለማስነሳት አንከሻ ጓጉሳ በሄደበት መታፈኑንና የት እንደገባ እንደማይታወቅ።

3. አቶ ምግባሩ አስማረ:- የእናት ፓርቲ የሞጣ ምርጫ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የነበረና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኛ ከሚሠራበት ቦታ ታፍኖ መወሰደኑንና በሞጣ ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰረ ነገር ግን የታሠረበትን ምክንያት እንዳልተገለፀ።

4. ወ/ሮ ስመኝ ታደመ በወላይታ ዞን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባልና ሶዶ አካባቢ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረች ከሥራ ቦታዋ መወሰዷና ቤተሰብም መጠየቅ እንዳልቻለ ፓርቲው አመልክቷል።

እናት ፓርቲ እኒህ አፈናዎች ፍጹም ፖለቲካዊና አምባገነናዊ ሥርዓትን ለማዋለድ የሚደረግ ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጾ መንግስት እነኚህን አመራሮቹን በጥርጣሬ ይዣቸዋለሁ ቢል እንኳ፦
➡️ያሉበትን ቦታ በማሳወቅ
➡️ቤተዘመድ እንዲጠይቃቸውና ከሥጋት ነጻ እንዲሆን
➡️ሕጋዊነትንና ሥርዓትን በተከተለ እንዲሁም በ48 ሰዓት ውስጥ ፍ/ቤት የመቅረብ መብታቸው ተከብሮ፣ ጠበቃ እንዲያቆሙ በመፍቀድ ማድረግ አለበት እንጂ እንደ አሸባሪ ቡድን ሰዎችን መሰወር ማቆም አለበት ሲል አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሀገራዊ ሰላም በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ በማስተላለፍ ውሳኔውን የሚያስፈጽሙ አባቶችን ሰይሟል። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ 23 የመወያያ አጀንዳዎችን አጽድቆ በመወያየት ልዩልዩ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ ጀምሯል። ዓመታዊው የግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም በጸሎት ከተጀመረ በኋላ በትላንትናው ዕለት በጠዋቱ መርሐ ግብር…
#Update

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቀጠለ ሲሆን ትላንት ግንቦት 18፣ 17 እና 16 በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክሯል።

በትላንት የጉባኤው ውሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ አባቶች ያስተላለፉትን መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያይቶበታል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ወቅታዊውን ችግር ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሰጧቸውን መግለጫዎች መመልከቱን ቃላቸውንም ከመገናኛ ብዙኃን ማድመጡ ተገልጿል።

በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ጉዳዩ የሃይማኖትና የቀኖና ልዩነት ሳይሆን #የፖለቲካ_ችግር መሆኑን በመረዳት ሰፊ ውይይት ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል።

ሌላው ጉባኤው የሃይማኖት ህጸጽ ተገኝቶባቸው ከቤተክርስቲያንና ምእመናን አንድነት በውግዘት የተለዩ ግለሰቦች ያቀረቡትን የይቅርታ ደብዳቤተመልክቶታል፡፡ በዚህም ምልዓተ ጉባኤው ይቅርታ ጠያቂዎቹ በቃል የተናገሩትን በመጽሐፍ የጻፉትን በተግባር ያደረጉትን የሊቃውንት ጉባኤ መርምሮ ለምልአተ ጉባኤው እንዲያቀርብ ወስኗል፡፡

በሰሜን አሜሪካና በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች በተከሰቱ ችግሮች ላይ ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን በተጨማሪ በቤተክርስቲያኗ የልማት ሥራ በጀት በሚያስፈልጋቸው አጀንዳዎች ላይ ውይይት አድርጓል። ጉባኤው በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሕክምና ዙርያም ውይይት አድርጓል፡፡

በግንቦት 17 ውሎው በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ልዩ ልዩ አጀንዳዎችን ተመልክቷል።

በሌላ በኩል ጉባኤው በግንቦት 16 ውሎ በተለያዩ ጉዳዮች ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።

በእስር ላይ ቆይተው የነበሩ የአ/አ ሀገረ ስብከት አገልጋዮች ያቀረቡትን አቤቱታ ተመልክቷል።

የብፁዓን አባቶች ምደባ ተከናውኗል እንዲሁም #በወቅታዊ ጉዳይ #ለመንግሥት በሚላክ ደብዳቤ ላይ ውሳኔ አስተላልፏል - telegra.ph/EOTC-TV-05-27-2

@tikvahethiopia