TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " - ብፁዕነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት  የአደጋ ስጋት ላይ መሆናቸውን አሳወቀች። ቤተክርስቲያኗ ፤ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሚገኙት የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በ900 ዓመታት ውስጥ ብዙ መከራን…
" የላልይበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ቦታውም ቅዱስ ነው ህንጻውም #ሰላም ነው " - የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ

የአማራ ክልላዊ መንግሥት ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ " ላሊበላ ጉዳት ደረሰበት " በሚል በየማህበራዊ ሚዲያዎች የሚናፈሰው ወሬ መሠረት ቢስ ነው አለ።

የቅዱሱ ስፍራ ህንጻም ሰላም ነው ብሏል።

" የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ቀደምት ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስ ነው " ያለው ቢሮው " በዚህ የዓለም ቀደምት ቅርስ ስም ሐሰተኛ ፕሮጋንዳ እየነዙ፤ ሕዝብን እያደናገሩ አሸናፊ ለመሆን መሞከር ሞራላዊና ኅሊናዊ ኪሳራን እንጅ ድልን አያጎናጽፍም " ብሏል።

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በሚገኘው የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተደርጎ ከትናንት ጀምሮ የሚናፈሰው ወሬም መሠረት ቢስ ነው ሲል ሀልጿል።

" በላሊበላ ስም መቀደስ እንጅ የጥፋት ድግስ መደገስ አስፈላጊና ተገቢ አይደለም። " ያለው ቢሮው " የላልይበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ቦታውም ቅዱስ ነው ህንጻውም ሰላም ነው " ሲል አሳውቋል።

በላሊበላ አካባቢ በተለያየ ጊዜ ግጭት እያገረሸ የሰው፣ የንብረት ጉዳት እየደረሰ የሚገኝ ሲሆን ሰሞኑንም በቀጠናው የመንግሥት ኃይሎች እና የታጠቁ ኃይሎች ዳግም ግጭት ላይ ነበሩ።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአካባቢው በተፈጠረው ከፍተኛ የሰላም እጦትና ጦርነት  ምክንያት
የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ከፍተኛ #የአደጋ_ሥጋት ላይ መውደቃቸውን አሳውቃ ነበር።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት በከፍተኛ #የአደጋ_ሥጋት ላይ መውደቃቸውን የገለፁ ሲሆን ቅዱሱን ቅርስ ከስጋት ነጻ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ሁሉም አካል ወደ #ሰላም_መድረክ መምጣት እንዳለበት ጠቁመዋል።

" ይህ ካልሆነ ግን ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና   የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " ሲሉ አስገንዝበዋል።

ብፁዕነታቸው የቅዱስ ላሊበላ ቅርስና የአምልኮ ቦታ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባለድርሻ አካላት ቅዱሱ ቅርስ ከአደጋ ስጋት ውጭ እንዲሆን ዓለም አቀፍ ተቋማት የመንግስት አካላት እንዲሁም የቅዱሱ ቅርስ የጋራ ሀብትነት የሚያሳስበው ሁሉ በጉዳዩ ላይ በጎ ተጽእኖ በማሳደር ድምጽ እንዲሆን ጥሪ አቅርበው ነበር።

@tikvahethiopia