TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ📈 የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ አሻቅቧል። የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በምሥራቃዊ ዩክሬን ላይ “ወታደራዊ ዘመቻ” መጀመሩን መግለጻቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ቢቢሲ ዘግቧል። በዚህም ሳቢያ በ7 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ አሻቅቧል። ውጥረት እና ግጭቱ የሚቀጥል ከሆነ የነዳጅ ዋጋ ከዚህም በላይ…
የሩስያ እና ዩክሬን ፍጥጫ #እንደኛ ባሉ አዳጊ ሀገራት ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅእኖ ምንድነው ?

[በዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የቀረበ]

- #የምግብ_ዋጋ_መናር : ኢትዮጵያ ስንዴ የምትገዛባቸው ሶስት ዋና ዋና ሀገራት ሩስያ፣ ዩክሬን እና አውስትራሊያ ናቸው። በተለይ ሩስያ እና ዩክሬን በአለም ላይ ካለው የስንዴ ገበያ አንድ አራተኛውን ይሸፍናሉ። ዩክሬን 40 % የሚሆነውን የስንዴ ምርቷን ለመካከለኛው ምስራቅ እና እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አዳጊ ሀገራት በሽያጭ ታቀርባለች። ታድያ ይህ አቅርቦት በጦርነት ምክንያት ሲስተጓጎል የምርት/ምግብ አቅርቦት መስተጓጎሉ አይቀርም። ይህም በአንዳንድ ሀገራት የሚታየውን የዋጋ ግሽበት አባብሶ ህዝባዊ ቁጣ ሊቀሰቅስ ይችላል።

- #የነዳጅ_ዋጋ_መጨመር : የሩስያ እና ዩክሬንን ፍጥጫ ተከትሎ አሁን ላይ የነዳጅ ዋጋ ከ100 ዶላር በላይ እንዳሻቀበ የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ፣ ይህ ዋጋ ከዚህም በላይ በፍጥነት ሊጨምር ይችላል የሚል ግምት አለ። ሩስያ በአለም ላይ የተፈጥሮ ጋዝ እና ነዳጅ በማምረት ከፍተኛውን ድርሻ ከሚይዙ ሀገራት መሀል ትመደባለች። ታድያ ይህ ግጭት የአለም የነዳጅ ዋጋን እጅጉን እያናረው ይገኛል፣ ይህም በተለይ እንደ ሀገራችን ላሉ ነዳጅ ገዢ ሀገራት እጅጉን ፈታኝ ግዜ እንደሚያመጣ ግልፅ እየሆነ ነው።

- #የእርዳታ_መቀነስ : ብዙ ግዜ እንደሚታየው አንድ ቦታ ላይ ትልቅ ችግር ሲከሰት ትኩረት ወደዛ ይዞራል። ለምሳሌ በሶርያ፣ የመን፣ ኢራቅ፣ አፍጋኒስታን ወዘተ ችግሮች ሲከሰቱ ከረጂ ሀገራት የሚገኘው ድጋፍ እዚህም፣ እዛም ይከፋፈል እና ይቀንሳል። አሁን ደግሞ ሀገራችን በጦርነት እና ድርቅ ምክንያት ከፍተኛ አለም አቀፍ ድጋፍ የምትሻበት ግዜ ነው፣ ነገር ግን ይህ እየተባባሰ የመጣ ፍጥጫ ትኩረት እንዳያሳጣን ስጋት አለ።

@tikvahethiopia