TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የደንብ ልብስ(ዩኒፎርም) #በነፃ ለማቅረብ በወሰነው መሠረት በዛሬው ዕለት #በፋሽን ዲዛይነሮች የተዘጋጁ ዲዛይኖች ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ አስተባባሪነት በባለሞያዎቹ በቀረቡ የዲዛይን ስራዎች ላይ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆች፣ የስነ-ልቦና ባለሞያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስተያየት ሰጥተውበታል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለKG ተማሪዎች ፤ ከ1ኛ-4ኛ ላሉ ተማሪዎች ፤ ከ5ኛ-8ኛ እና ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች በአራት ዘርፍ ዩኒፎርሞችን አዘጋጅቶ ለተማሪዎች በነፃ ለማቅረብ እየሰራ ነው፡፡

ለመጪው የትምህርት ዘመን የከተማ አስተዳደሩ ለ 600ሺ የመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ እና የደንብ ልብስ ለማቅረብ እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

Via @mayorofficeAA
🗞ቀን ሃምሌ 1/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia