TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Asset Recovery draft proc. Amharic from COM to HPR (1).pdf
#ኢትዮጵያ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ፤ " ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ስለማስመለስ " ምን ይላል ?

➡️ #ማንኛውም_ሰው በቀጥታ ሆነ #በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው አሁን ላይ ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ እና የንብረቱን ወይም የኑሮ ደረጃውን ምንጭ በተመለከተ ምክንያታዊ የሆነ የወንጀል ጥርጣሬ በኖረ ጊዜ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ #ይወረሳል

➡️ ህጋዊ ገቢ እንዳለው የሚያስረዳ የተመዘገበበት ስርዓት የሌለው ወይም ገቢው እነስተኛ በመሆኑ #ከግብር_ነጻ የሆነ ሰው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያለው ንብረት ወይም የኑሮ ደረጃው ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ህጋዊ ገቢ የማይመጣጠን እንደሆነ የዚህ አይነቱ የኑሮ ደረጃ ወይም ያለው ንብረት እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ለፍርድ ቤት ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ ይወረሳል፡፡

➡️ " በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ያፈራው ንብረት " ማለት ፦

° በራሱ ስም የሚገኝ ንብረት፣

° በራሱ ስም ባይሆንም ለራሱ ጥቅም ሲያዝበት ወይም ሲቆጣጠረው የነበረው ንብረት ፣

° የተጠቀመው ወይም ደግሞ ያስወገደው ንብረት፣

° በሽያጭ ፣ በስጦታ ወይም በማንኛውም ሁኔታ #ያስተላለፈውን ንብረት ይጨምራል፡፡

➡️ ዐቃቤ ሕግ " #ምንጩ_ያልታወቀ_ነው " ብሎ የጠረጠረውን ማንኛውንም ንብረት ዝርዝር እና የተገኘበትን አግባብ የሚያሳይ መግለጫ እንዲያቀርብ በፅሁፍ ጥያቄ የቀረበለት ማንኛውም ሰው ጥያቄው በደረሰው በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ለዐቃቤ ህግ ዝርዝር ማስረጃዎችን በማያያዝ በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርበታል።

➡️ የንብረቱን ምንጭ እንዲያስረዳ የተጠየቀው ሰው የንብረቱን ምንጭ ለማስረዳት የሚያቀርበው ማስረጃ ሀጋዊ መሆን አለበት።

ተጨማሪ ....

☑️ አንድ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ አውጥቶ የሚሰራ ነጋዴ ወይም ድርጅት ሕጋዊ ገቢው ተብሎ የሚገመተው ለተገቢው ባለስልጣን በወሩ ወይም በአመቱ ከንግዱ ያገኘሁት ብሎ ያሳወቀው የገቢ መጠን ሲሆን ወይም ተገቢው ታክስ የተከፈለባቸው ገቢዎች ሆነው ሲገኙና የታክስ ደረሰኝ ሲቀርብ ሲሆን ከዚህ ውጪ ህጋዊ ታክስ ያልተከፈለባቸው ገቢዎች ከህጋዊ ገቢ ውጪ ያፈራው ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ተብሎ ሊወሰን ይችላል።

☑️ ምንጩን ሲያስረዳ " ከውጪ የተላከለኝ ገንዘብ ነው " የሚል ማንኛውም ግለሰብ ገንዘቡ በሕጋዊ መንገድ #በባንክ_ሥርዓት ውስጥ ያለፉ ግብይቶች ወይም ክፍያዎች ስለመሆናቸው በተገቢው የባንክ ደረሰኝ አስደግፎ ማቅረብ የሚገባው ሲሆን ከዚህ ውጪ ያለው ግን እንደ ምንጩ ያልታወቀ ገቢ ተደርጎ ይቆጠራል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ #ምንጩ_ያልታወቀ_ንብረት ክስ የሚቀርብበት ጊዜ እና የገንዘብ መጠን ተደንግጓል፡፡

በዚህም አዋጁ ወደኋላ 10 ዓመታት ተመልሶ የሚሠራ ሲሆን ይህንንም ለመክሰስ የ5 ሚሊዮን የገንዘብ ገደብ ተቀምጧል፡፡

ይህ የገንዘብ ገደብ የተቀመጠበት ዋነኛው ምክንያት በአሁኑ ወቅት ላይ በሀገሪቱ ያለውን የሰው ሃይል ፣ የመክሰስ አቅም እና የፋይናንስ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት አነስተኛ የሃብት መጠን ያላቸውን ግለሰቦች በመተው ከፍተኛ ንብረት ያላቸውን ተጠያቂ ለማድረግ እንደሆነ ተብራርቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ሕጉ ወደኋላ (10 ዓመታት) ተመልሶ እንደመስራቱ በሀገሪቱ #ኢኮኖሚ#ማሕበራዊ እና #የፋይናንስ_ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ ያደርሳሉ ተብሎ የሚገመቱትን ግለሰቦችና ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶችን ተጠያቂ ማድረግ የተሻለ አማራጭ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ተብራርቷል።

አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ተጠያቂነት ያለምንም የገንዘብ መጠን ተፈጻሚ ይደረጋል።

ስለ ረቂቅ አዋጁ አጭር ማብራሪያ ⬇️
https://t.iss.one/tikvahethiopia/88313

ረቂቅ አዋጁ⬇️
https://t.iss.one/tikvahethiopia/88314

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM