TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጎንደር ጉሙሩክ⬆️

999 #ሽጉጥ እና 30 #የክላሽ_ጠበንጃ ጎንደር ጉምሩክ ላይ ተያዘ። ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ነዳጅ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሳቢ ቦቲ መኪና በውስጡ ህገ ወጥ መሣሪያ ጭኖ ሲጓዝ በደረሠ ጥቆማ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን የጎንደር ጉምሩክ አስታወቀ፡፡

ጥቅምት 10/2011 ዓ.ም (ጎንደር) የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በቀን 03/02/2011 ዓ.ም ከሡዳን ወደ ጎንደር ሲጓዝ የነበረ ቤንዚን የጫነ ቦቲ መኪና ኮድ -3 87297 የፊቱ ተሳቢ ኮድ -3 27172 ኢት የሆነ ህገ ወጥ መሣሪያ ጭኖ ሲጓጓዝ ለጎንደር ጉምሩክ ቅርጫፍ ጽ/ቤት በደረሠ ጥቆማ በህግ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

የተያዘው የመሣሪያ ብዛትም ሽጉጥ 999/ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ/ ሲሆን የክላሽ ጠበንጃ ብዛት 30/ሠላሣ/ በመዳበሪያ ተጠቅሎ ከነዳጁ ጋር ተጭኖ መገኘቱን የጎንደር ጉምሩክ አስተውቋል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃም እሽከርካሪውና እረዳቱ በህግ ስር ተይዘው የሚገኙ ሲሆን የመኪናው ባለቤት ግን መቅረብ አለመቻሉን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ የጎንደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia