TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somalia #SW ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር ተገደሉ። የሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ክልል ፍትህ ሚኒስትር ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር በባይዶዋ ከነ ልጃቸው በአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ተገደሉ። ሚኒስትሩ የተገደሉት ዛሬ ዓርብ ዕለት ከመስጂድ ሲወጡ በተፈፀመ ጥቃት ነው። በጥቃቱ ሌሎች 11 ሰዎችም ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም። የደቡብ ምዕራብ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲአዚዝ ሀሰን…
" አልሸባብ ዳግም ከፍተኛ ኪሳራ ተከናንቦ ወደ መጣበት ተመልሷል " - ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው

የሀገር መከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ለመግባት የሞከረው የአልሸባብ የሽብር ቡድን በጸጥታ ኃይሉ በተወሰደበት እርምጃ ዳግም ከፍተኛ ኪሳራ ተከናንቦ ወደ መጣበት መመለሱን ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን በሶማሌ ክልል በ5 ትናንሽ የጠረፍ አካባቢዎች ወደ አገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም ያደረገው ሙከራ በጸጥታ ሃይሉ ሙሉ በሙሉ መክሸፉን ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም የጸጥታ ኃይሉ ተቆርጠው የቀሩትን የሽብር ቡድኑ አባላትን የማጽዳት ዘመቻ ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀዋል።

ባለፉት ቀን ከኢፌዴሪ አየር ኃይል ጋር በመቀናጀት በተወሰደው ርምጃ የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ያዘጋጃቸውን የትጥቅና ስንቅ ዴፖዎች ማውደም ተችሏል፡፡ በዚህም በሽብር ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት ጠቁመዋል፡፡

ነገር ግን የሽብር ቡድኑ #ዛሬ_ሌሊት ላይ የተበታተነ ኃይሉን በማሰባሰብ ኢትዮጵያና ሶማሊያ በሚዋሰኑበት አካባቢ ወደ አገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም መሞከሮ ነበር።

ሆኖም የጸጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ የሽብር ቡድኑ ዳግም ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራዎችን ተከናንቦ ወደ መጣበት መመለሱን ነው ያብራሩት፡፡

እስካሁን ባለው መረጃም ከ150 በላይ የሽብር ቡድኑ አባላት መደምሰሳቸውንና የሽብር ቡድኑ ለአጥፍቶ መጥፋት ያዘጋጃቸው ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን ፣ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እንደተማረኩ አመልክተዋል።

#ENA

@tikvahethiopia