TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥንቃቄ🚨

በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የሶማሌና አጎራባች ክልሎች የሜትዮሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል አሳውቋል።

በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል #ጥንቃቄ እንዲደረግ ተብሏል።

የማዕከሉ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን ሀ/ማርያም ለሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፥ " በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በሀገር ደረጃ የተሰራው ትንበያ እንደሚያሳየው በቀጣይ 10 ቀን ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር ይችላል የሚል ነው " ብለዋል።

" በጎርፍ ይጠቃሉ ተብሎ የሚጠበቁት በሰሜኑ ላይ #ከድሬዳዋ ጀምሮ #በጭናቅሰን እስከ #ጅግጅጋ ድረስ ነው " ብለዋል።

" በብዛት በኦሮሚያ ሃይላንድ በቀርሳ ፣ በቁልቢ ከፍታ ቦታዎች ላይ ከሚዘንበው ዝናብ ጋር ተያይዞ በተለይ #ድሬዳዋ ላይ ብዙ ዝናብ ከተማው ላይ ሳይዘንብ ጎርፍ የመምጣት እድል አለው። በተመሳሳይ #ጅግጅጋ ላይ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል " ሲሉ ገልጻዋል።

ዋቢ ሸበሌ፣ ከኢሚ፣ ጎዴ፣ ቀላፎ፣ ሙስታይል ወደታች ያለው አካባቢ ጎርፍ ሊመጣ የሚችልበት እድል ስላለ አሁን ላይ ባለው ሁኔታ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይፈልጋል ተብሏል።

@tikvahethiopia