TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የኢትዮጵያና የቻይና ወዳጅነት ጠንካራና የማይበጠስ ነው " - የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ በአዲስ አበባ እያደረጉት ያለው ጉብኝት ቻይና በኢትዮጵያ ያላትን እምነትና ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ…
#ተጨማሪ

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ገዳይ ሚኒስትር ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

አቶ ደመቀ በህወሓት የጦርነት አስተሳሰብ ምክንያት ስለጠፋው የሰው ህይወትና ስለወደመው ንብረት በዝርዝር አስረድተዋል።

አቶ ደመቀ ፥ " የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው ሰኔ ወር ባወጀው የአንድ ወገን ሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ውሳኔ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ህወሓት ለሰላም ጥረት ደንታ ቢስ መሆኑን አሳይቷል " ብለዋል።

" ምንም እንኳን የፀረ-መንግስት እንቅስቃሴዎች ቢደረጉም ፤ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ላደረጉ ወዳጆች ምስጋና ይግባቸውና ዛሬ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለው ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ነው " ብለዋል። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ጦር ግንባር ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተከትሎ ጠላት ወደኃላ ሽሽት ላይ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።

አቶ ደመቀ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር እየተካሄደ ያለውን የኦሊሴጎን ኦባሳንጆን የሰላም ጥረት መደገፍ ቀጥለናል ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ችግሩ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።

ዋንግ ዪ በበኩላቸው ቻይና እንደ ወዳጅ ሀገር የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለች መሆኗን ገልፀዋል። የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ለመጫን የሚያደርጉትን ሙከራ እንደምትቃወም ተናግረዋል።

" ለማጨብጨብ ሁለት እጅ ያስፈልጋል " ያሉት ዋንግ ዪ ህወሓት የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበለትን የሰላም ሃሳብ መቀበል ነበረበት ብለዋል።

አገራቸው የኮቪድ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ከማጠናከር ባለፈ ከኢትዮጵያ ጋር በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በአቅም ግንባታና በልማት ትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

ቻይና የኢትዮጵያ መንግስት ሁኔታዎችን በቁጥጥር ስር እንደሚያውል እና መላው ኢትዮጵያውያንንና በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑ ቻይናውያንን ለመጠበቅ አቅም እንዳለው ታምናለች ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ፥ የዛሬው ጉብኝታቸው ቻይና የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ያለውን ሁኔታ እንደሚያረጋጋ እምነት እንዳላት የሚያሳይ እና ዜጎቿን ከአዲስ አበባ ከተማ የማስወጣት ጥሪዎችን በጭፍን አለመቀበሏን የሚያሳይ እንደሆነ ገልፀዋል።

በመጨረሻም በቻይናና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራና የማይበጠስ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስር ስለተፈቱ ግለሰቦች ምን አሉ ? ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፦ " ... ትላንት ክስ የተቋረጠላቸው የተሸነፉ ኃይሎች ክስ እንዲቋረጥ እና ከእስር ቤት እንዲወጡ ሲደረግ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል። ይህ ቁጣ የተቀሰቀሰው በሁለት ቡድኖች ነው። አንደኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ጭር ሲል የማይወድ ፣ ሁል ጊዜ እያጋጨ በሰበር ዜና ብር የሚሰበስብ፣ የት እንዳለ የማይታወቅ ካለበት ሆኖ ስንዋጋ…
#ተጨማሪ

ከእስር ስለተፈቱት ግለሰቦች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን ተናገሩ ?

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" ... ክስ የተቋረጠላችሁ ወገኖች ስላሸነፍን መበቀል እየቻልን ይቅር ማለትን ስለመረጥን ክስ አቋርጠን እናተን ሳይሆን ከእናተ ጀርባ ያለውን ህዝብ አክብረን የወሰን መሆናችንን አውቃችሁ ይህን እድል ሳታበላሹ እንድትጠቀሙበት ላሳስባችሁ እፈልጋለሁ።

ክስ ማቋረጥ ማለት ምህርተ መስጠት ማለት አይደለም። ክስ የተቋረጠለት ሰው በአግባቡ መጠቀም ካልቻለ መልሶ የክስ መዝገቡን መምዘዝ የሚቻል ስለሆነ።

በዚህ ጉዳይ ያዘኑ፣ የተቆጡ፣ የኢትዮጵያ ቁርጥ ቀን ልጆች እንዲገነዘቡ የምፈልገው የወሰድነው መድሃኒት ማስታገሻ አይደለም የወሰድነው መድሃኒት ፈዋሽ በመሆኑ የጎንዮሽ ጉዳት አለው ፤ ይጎረብጣል ያማል ! ለማዳን ብቻ ሳይሆን በጎንም የመጎርበጥ ባህሪ አለው።

ለጊዜው የሚያስታግስ ሳይሆን ለልጆቻችንም የድልና የአሸናፊነት መንፈስ የሚያላብስ ስለሆነ እንደኛ ደጋግማችሁ ስታስቡት ጠቀሜታው ጎልቶ ይታያችኃል እናም ደግማችሁ ለማሰብ ልባችሁና አእምሯችሁ እንዲከፈት ዋናው አላማ የምትወዷትን ሀገር ኢትዮጵያን አንድ አድርገን ለማፅናት ካለን ፍላጎት አንፃር ብቻ የመነጨ መሆኑን እንድትገነዘቡ ቢያንስ ቢያንስ ጉቦ በልተን እንዳለቀቅናቸው እንድታስቡ ላሳስባችሁ እፈልጋለሁ። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ድርድርን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አሉ ? ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦ " እስካሁን የተደረገ ድርድር የለም፤ እስከዚህ ደቂቃ ድረስ ፤ ስለድርድር ብዙ ሲወራ ሰማለሁ ግን እስካሁን ድርድር አላደረግንም፤ አላደረግንም ማለት እስከነአካቴው ድርድር የሚባል ነገር አይኖርም ማለት አይደለም። ድርድር ፣ ውይይት ማለት ችግር ተወግዷል ማለት ሳይሆን ችግር ለማስወገድ አማራጭ Alternative መንገድ አለው…
#ተጨማሪ

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስለ ድርድር የተናገሩት ፦

" ... አንድ የእስራኤል ፕሬዜዳንት በአንድ ወቅት ያሉትን ማስታወስ ፈልጋለሁ፤ እኚህ ፕሬዜዳንይ እስራኤል እየተዋጉ ከሀማሶች ጋር ከሂዝቦላህ ጋር ይደራደራሉ።

በነገራችን ላይ TPLF ከኦነግ ጋር ይደራደር ነበር፣ ደርግ ከሻዕቢያ እና TPLF ጋር ይደራደር ነበር ድርድር ማለት እርቅ ማለት አይደለም። ድርድር ውስጥ ብዙ የሚገኙ ነገሮች አሉ። ከምሳሌ ... ምሳሌው ይቅርብኝ ግን አሉ ጥቅሞች።

እናም እኚህ የእስራኤል ፕሬዜዳንት በጦርነት ጊዜ ምንም የሰላም ጫላንጭል እንደሌለ ሰላም ተስፋ እንደሌለው አስበን ጨክነን እንዋጋለን ፤ በድርድር ጊዜ ተጋጭተን እንደማናውቅ ጦርነት የሚባል እንዳልነበር በሰከነ መንፈስ እንደራደራለን ሁለቱንም የምናደርገው ለእስራኤል ጥቅም ነው ብለዋል።

እኛ በውጊያው ጊዜ የነበረን አቋም እና ሂደት ለምክር ቤት መግለፅ አይጠበቅብኝም አቋማችን ግልፅ ነው። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ምንም የማንደራደር መሆኑ ግልፅ ነው።

አሁንም የምናደርገው የዛ ተገላቢጦሽ ሆኖ መታየት አለበት። ታስታውሳላችሁ በዝግ ስንወያይ ኢትዮጵያን አፍርሰው እነዚህ ሰዎች አዲስ አበባ አይገቡም ብያቹ ነበር በቲቪ አልተላለፈም ያ ውይይት ነበራችሁ ብዙዎቻችሁ ያኔ የተወያየነው ነገር ነው ተፈፅሞ ያየነው።

አሁንም #በድርድር የሚባል ነገር ካለ በዛው sprint ማየት ጥሩ ነው። የሰላም አማራጭ ካለ ፤ TPLF ቀልብ ከገዛ በጦርነት እንደማያዋጣው እንደማያሸንፍ ከተገነዘበ እኛ በደስታ ነው የምናየው። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba📍 በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ፤ የቦሌ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ሃላፊ በህገ ወጥ ንግድ ምክንያት የታሽገን የንግድ ቤት እከፍትልሃለሁ በሚል 100 ሺ ብር #ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ መያዙን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ። የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ፤ የንግድ ፅ/ቤት ሃላፊው አቶ አለማየሁ ዋንዴቦ ታሽጎ የነበረን የንግድ ቤት በህገ ወጥ መንገድ ለመክፈት ተስማምቶ…
#ተጨማሪ

የቦሌ ክ/ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊው አቶ አለማየሁ ዋንዴቦ 100 ሺህ ብር ጉቦውን የተቀበሉት ታሽጎ የነበረውን " አቤኔዘር የተሽከርካሪ እጥበት አገልግሎት ድርጅት " ን አስከፍታለሁ ፤ የንግድ ፈቃዱንም እንዲታደስ አደርጋለሁ በማለት ነው።

የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንዳለው ከሆነ፤ የድርጅቱ ባለንብረት በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ታሽጎ የነበረው ድርጅታቸው እንዲከፈትና ንግድ ፈቃድ እንዲታደስላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ መነሻ በማድረግ የስራ ኃላፊው 100,000 ብር ጉቦ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በኃላም 22 ጎላጎል ህንጻ በሚገኘው ካፌ ውስጥ ብሩን ሲቀበሉ #እጅ_ከፍንጅ ተይዘዋል ፤ አሁን ላይም ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ፖሊስ አስረድቷል።

#AMN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Tigray, #Mekelle 📍 ትላንትና በጉዞ ላይ እንደነበሩ የተነገረላቸው አስፈላጊ የሆኑ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶችን የጫኑት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሸከርካሪዎች የትግራይ ክልል መዲና መቐለ ደርሰዋል። ሁሉም (50ውም) ተሸከርካሪዎች በሰላም ነው መቐለ የደረሱት። ምን ይዘዋል ? ➡️ 1,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ እና ጥራጥሬ ፤ ➡️ 700 ሜትሪክ ቶን የጤና ፣ የተመጣጠነ ምግብ…
#WFP #USA #Ethiopia #TigrayRegion

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ወደ ትግራይ ክልል #ተጨማሪ ኮንቮይዎችን ለመላክ ዝግጁ መሆኑና ፍቃድም እንዳለው ገልጿል።

ቀጣዩ የሰብዓዊ እርደታ ኮንቮይ በተቻለ ፍጥነት በሰላም እንዲሄድ በአፋር ክልል ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፥ አሜሪካ ትላንት በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ ፤ ከ1,700 ሜትሪክ ቶን በላይ ነፍስ አድን ሰብአዊ እርዳታ ትግራይ መግባቱ መልካም ዜና ነው ብላለች።

የእርዳታው እንዲደስ ትብብር ያደረጉትን የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች እና የአፋር ክልል አስተዳዳሪዎችን እንደምታደንቅም ገልፃለች።

በተጨማሪም ፤ አሜሪካ የትግራይ ኃይሎች ከአፋር ክልል ኤሬብቲ መውጣታቸውን እንደምትደግፍ ገልፃ ከሌሎችም የአፋር አካባቢዎች የትግራይ ኃይሎች ቢወጡ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብላለች።

አሜሪካ በትላንት መግለጫዋ የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ባለስልጣናት አሁን በታየው ለውጥ ቀጥለው ግጭቱን በድርድር፣ በዘላቂነት መፍታት የሚችሉበት መንገድ ማግኘት አለባቸው ብላለች።

ይህ እንዲሆንም በትግራይ ክልል መሠረታዊ አገልግሎቶች መመለስ እንዳለባቸው እና አካታች ፖለቲካዊ አካሄድ መተግበር እንዳለበት ገልጻለች።

የአሜሪካ መግለጫ : https://www.state.gov/delivery-of-humanitarian-assistance-in-tigray/

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ እጅግ አስከፊ በነበረበት ወቅት በኮንትራንት ተቀጥረው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የጤና ባለሞያዎች ፦ " እኛ በጤና ሚኒስትር በኩል በኮቪድ ላይ በኮንትራት ተቀጥረን የምንሰራ ባለሙያዎች ነን። ኮቪድ ከጀመረ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ ሆስፒታሎች ስናገለግል ቆይተናል። የጤና ሚኒሰትር እና ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቋሚነት…
#ተጨማሪ

" የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሃገራችን ከተከሠተበት ጊዜ ጀምሮ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በኮንትራት የተቀጠርን ባለሙያዎች ተፈላጊውን ውጤት አስመዝግበናል።

ወረርሽኙን በሚገ’ባ ተቆጣጥረን ጉዳቱን ቀንሰናል።

የኮንትራት ጊዜያችን ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ሲያበቃ ማሠናበቱ አስቸጋሪነቱን በማመን (ወረርሽኙ ስላልተገታ እና የባለሙያዎችን ሞራል ለመጠበቅ) ጤና ሚኒስቴር አምኖበት ሐምሌ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ለየክልል ጤና ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ በ2014 በጀት ዓመት ቋሚ ቅጥር እንዲያዝልን ገልጾ ነበር።

ነገር ግን ላለፉት 11 ወራት የክልል ጤና ቢሮዎች ወደ ቋሚ ቅጥር አላዛወሩንም። ከሥራ ያሠናበቱም ክልሎች አሉ። ለምንጠይቀው የመብት ጥያቄም ተገቢ መልስ አልተሠጠንም።

አሁንም አበርክቶታችን ታይቶ በ2015 በጀት ዓመት የቋሚ ቅጥር በጀት ተይዞልን ቅጥር ይፈጸምልን ዘንድ እንጠይቃለን! "

[ በኮቪድ19 መከላከል በኮንትራት የተቀጠርን ባለሙያዎች ]

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ገንዘባችንን ተበላን " ገንዘባችንን ተበላን ያሉ እጅግ በርካታ ወጣቶች የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመልዕክት መቀበያን @tikvahethiopiaBOT አጨናንቀዋል። እኚሁ አባላት ገንዘባችን ተበላን ያሉት እራሱን ' FIAS 777 ' እያለ በሚጠራው ድርጅት ነው። ይሄ FIAS 777 የሚባለው " በኮሚሽን የሚሰራ ስራ " በማለት የበርካቶችን ገንዘብ ሲቀበል ነበር። ስለዚህ FIAS 777 ከዚህ በፊት…
#ተጨማሪ

በ " FIAS 777 " በሚል የሚንቀሳቀሱ አካላት አጭበረበሩን ካሉት መካከል እጅግ በጣም በጥቂቱ ፦

📩 " 40000 ብር ተበልቻለሁ "

📩 " በFIAS እኔም 30 ሺህ ብር ተብልቻለሁ "

📩 " እኔም ገንዘቤን ተበልቻለሁ ፤ ተበድሬ ነበር የገባሁት በሰዎች ጉትጎታ ኤጀንቶቹም አድራሻቸውን አጥፍተዋል "

📩 " በFIAS 777 የተዘረፉ በሚያውቋቸው ኤጀንቶች ላይ ክስ ለመስረት እያተዘጋጁ ነው "

📩 " ዘንድሮ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ የምመረቅ ዘንድሮ ነበር ነገርግን ከቤተሰብ ለመመረቂያ ልብስ ብር አስልኬ fias777 ለተባለ አጭበርባሪ platform ልኬ ምንም ብር ሳይገባልኝ በሉት። ከተቻለ እርምጃ እንዲወሰድበት አሳስባለሁ። በተጨማሪ ሌሎች የማጭበርበሪያ መንገዶችን ለምሳሌ ፦ HDU, DH አና የመሳሰሉ platform እየተጠቀሙ ስለሆነ ማንም እንዳይጭበረበር "

📩 " የመንግስት ያለህ እኛ የFIAS ተጠቃሚወች ድርጅቱ ሀገረ መንግስቱ እውቅና የሰጠው ነው ተብለን ነው የገባንበት ሊንኩ ከተዘጋ ጀምሮ ገንዘብ ገቢና ወጭ እሚያደርጉልን ኤጀንቶች ቴሌግራም አካውንታቸውን ድሌት አርገው ከኛ ጋ የተጻጻፋትን አጥፍተው ነው ውሀ ሽታ የሆኑት በመቶ ሽወች የሚቆጠር ገንዘብ vIP Upgrade ያደረጉ ልጆች እያበዱ ነው። "

📩 " እዚህ ኢትዮጵያ ሲያስተባብሩ የነበሩት ይታወቃሉ ፤ ልብስ ለብሰው በአደባባይ ሲታዩም ነበር ፤ እንዴት እና ገንዘቡን የት እንዳደረሱት ይጠየቁ "

📩 " 30 ሽህ ብር አንድ ብር ሳላወጣ ተበልቻለው ባንክ የከፈልኩበትን ደረሰኝ ማቅረብ እችላለሁ "

📩 " በሰው በሰው ገብቼ 30 ሺህ ብር ተበልቻለሁ ፤ ስለድርጅቱ አንዳች ነገር አላውቅም "

📩 " እሄ website በ internet ነው እሚሰራው ግባ ብሎ በማላቀዉ ነገር fias 777 lay ኣስገብተዉ አሁን ላይ እስከ100 ሺህ ሚገመት ብር ከሰዉ ኣስበድረው ኣስበልተውኛል:: የ bank full መረጃ አለኝ "

📩 " ህጋዊ በመምሰል በጦርነት እና በዚህ በኑሮ ውድነት የሚሠቃየውን ሚስኪኑን ማህበረሰባችንን ዘርፎ ስለጠፋው fias777 ስለሚባል ድርጅት መናገር ፈልጋለሁ። አብዛኛው ሰው ትርፋ አገኛለሁ በሚል መንፈስ ከሰው በመበዴር፣ መሬት በመሸጥ፣ ቋሚ ንብረቶቹን ሳይቀር በመሸጥ ለዚህ ድርጂት መጀመሪያ አካባቢ ከ1000 እስከ 30,000 ብር ገቢ ያዴረጉ ሲሆን አሁን በቅርቡ ሊዘጉት አካባቢ ዴግሞ እስከ 180,000 ብር ድረስ ለዚህ ድርጅት ገንዘባቸውን ገቢ በማድረግ ገንዘባቸው የውሀ ሽታ ሁንዋል "

(ውድ ቤተሰቦቻችን ፦ ይህ ከብዙ በጥቂቱ ከተላኩት ውስጥ የቀረበ ሲሆን አብዛኛው ሰው በሰው በሰው መግባቱን እና አሁን ስራውን እንሰራለን የሚሉ አካላት መጥፋታቸውን የሚጠቁም ነው ፤ ተበላ የተባለው ገንዘብም እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው። የሚመለከተው አካል ገንዘብ ገቢ በተደረገባቸው አካውንቶች መሰረት ሰዎችን ተጠያቂ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።)

ከዚህ በፊት በኦንላይን በሚሰራ ስራ በርካታ ትርፍ እናስገኛለን እያሉ ስለሚንቀሳቀሱ አከላት ጥንቃቄ እንዲደረግ መልዕክት መተላለፉ የሚዘነጋ አይደለም ፤ አሁንም በሌላ ስም የሚንቀሳቀሱ አሉ ጥንቃቄ ይደረግ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሰራተኛ ማህበር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄዱን ገለፀ። ጉባኤው ትናንትና እና ዛሬ ነው የተካሄደው። ትላንህ ጉባኤው በማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኪያ ለማ፣ በአየርመንገዱ የሰዉ ሀብት ም ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘነበወርቅ ገ/ጻድቅ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን የማህበሩ የስራና የኦዲት ሪፓርቶች፣ የማህበሩ የ2022/2023…
#ተጨማሪ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤን በሚመለከት ቲክቫህ ኢትዮጵያ አንድ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መመልከት ችሏል።

ይኸው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠ ነው።

ትዕዛዙም ፤ " በኢትዮጵያ አየር መንግድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ሊቀመንበር በሆኑት በተጠሪ ጥሪ ተደርጎ በስካይ ላይት ሆቴል እየተከናወነ ያለ ጠቅላላ ጉባኤ ካለ ከዛሬ 8/11/2014 ዓ/ም 6:05 ጀምሮ ከዚህ ፍርድ ቤት ተለዋጭ ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ድረስ ጠቅላላ ጉባኤው እንዳይከናወን ታዟል። የእግድ ትዕዛዝ ትዕዛዙ ለሚመለከታቸው ይድረስ " ይላል።

ትዕዛዙ የተሰጠው 4 የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ፤ በተጠሪ የማህበሩ ሊቀመንበር ኢ/ር ተሊላ ደሬሳ ላይ ባቀረቡት አቤቱታ አማካኝነት ነው።

የማህበሩ ዋና ፀሀፊ ትላንት እና ዛሬ ጠቅላላ ጉባኤውን በስኬት መጠናቀቁን ያሳወቁ ሲሆን ዛሬ ምንም አይነት የእግድ ደበዳቤ እንዳልደረሳቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጉባኤው ታግዷል፣ አልተካሄደም በሚል የሚሰራጨው መረጃ ውሸት ነው ብለዋል።

ግለሰቦቹ የማህበሩን ንብረቶች በመበዝበዝ ላልተገባ ጥቅም በማዋላቸው የማህበሩ ምክር ቤት እና ጠቅላላ ጉባኤ ያባረራቸው እና ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያሉ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

4 ስራ አስፈጻሚ አባላት ጠቅላላ ጉባኤን ማገድ አይችልም ያለው ማህበሩ ፤ የማህበሩ ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቅላላ ጉባኤው እንደሆነ መታወቅ አለበት፤ በዚህም መነሻነት ነው የሚመለከታቸው ከፍተኛ የድርጀቱ መሪዎች በጉባኤው ላይ የተገኙት ፤ ጉባኤው ስኬታማ ነበር ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጉራጌ ዞን ምክር ቤት #በክላስተር_ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አድርጓል። የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ፤ ዛሬ ሐሙስ ባካሄደው አስቸካይ ጉባኤ ከሌሎች የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር በክላስተር ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አደርጓል። የጉራጌ ዞንን በደቡብ ክልል ስር ከሚገኙ ሌሎች 4 ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ ጋር በማዳመር የጋራ ክልል ለመመስረት የቀረበው…
#ተጨማሪ

" መንግስት የዞኑ ህዝብ በም/ቤት ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ ጥያቄ #በድጋሚ ሊያይ ይገባል " - የጉራጌ ዞን ም/ቤት

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር የቀረበውን #በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሐሳብ በአብልጫ ድምፅ #ውድቅ አድርጎታል።

የዞኑ ህዝብ በም/ቤቱ ያፀደቀው ህገመንግስታዊ ጥያቄ መንግስት በድጋሚ ሊያይ ይገባል በሚል ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ የክላስተር ውሳኔውን ምክረ ሀሳብን ውድቅ ያደረገው።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ህዳር 17/2011 ዓ.ም. ባደረገው ጉባኤ ዞኑ ራሱን ችሎ ክልል ለመሆን ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

የደቡብ ክልልን ለሁለት የሚከፍለውን የክልልነት አደረጃጀት በም/ቤቱ ባለማጽደቅ የጉራጌ ዞን #ብቸኛው ሆኗል።

ቀሪዎች የደቡብ ክልል 10 ዞኖች እና ስድስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ ላይ ሁለት ክልል የመመስረት ውሳኔን በምክር ቤቶቻቸው ማጽደቃቸው ይታወሳል። 

ፎቶ ፦ የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል መፈፀሙን ፖሊስ ገልጿል። በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቦሌ አራብሳ ኮምዶሚኒየም በሁለት ህፃናት ላይ እጅግ አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል። የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ሲሆን ፤ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ የምትሰራ አንዲት ግለሰብ ክርስቲያን መላኩና ወንጌላዊት መላኩ የተባሉ…
የፖሊስ መልዕክት !

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ የሰጡት ቃል ፦

" ምንም በማያውቁት ጉዳይ በህጻናቱ ላይ የተፈጸመው ይህ አሰቃቂ ወንጀል ሁሉንም በእጅጉ አሳዝኗል።

ወላጆች የሚቀጥሯቸው የቤት ሠራተኞችን ማንነት ጠንቅቀው ማወቅ ይገባቸዋል።

እንደ ቤተሰብ ሆነው የሚኖሩ የቤት ሠራተኞች እንዳሉ ሁሉ እንደዚህ አይነት አሰቃቂ ወንጀል የሚፈጽሙም ስላሉ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። "

#ተጨማሪ_መረጃ

• በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ ሁለት ታዳጊ ልጆቻቸውን ያጡት ወላጆች በከባድ ሐዘን ውስጥ ይገኛሉ።

• ወንጀሉ በተፈጸመበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችም በእጅጉ ተረብሸው ነው የሚገኙት።

• ፖሊስ በወንጀሉ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ ነው።

- ተጠርጣሪዋ ህጻናቱን አንቃ እና ስለት ተጠቅማ በአስቃቂ ሁኔታ መግድሏ የሚያመላክቱ መላምቶች አሉ።

- ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳት ለማወቅ ምርመራዎች እየተካሄዱ ነው።

- በወንጀሉ የተጠርጠረችው ግለሰብ በቤት ሠራተኛነት ግድያው ለተፈጸመበት ቤተሰብ ስታገለግል ቆይታለች።

• ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን የፈጸመችው ወላጆች የሌሉበትን ሰዓት ጠብቃ ነው።

መረጃው ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ የአማርኛ አገልግሎት ከሰጡት ቃል የተወሰደ ነው።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በነገው ዕለት የ2015 የትምህርት ዘመን ይጀምራል።

በዚሁ ዕለት ትምህርት ሚኒስቴር 5 ዓመታት ሲያዘጋጅ የቆየው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መተግበር ይጀምራል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባው የአዲሱ የትምህርት ስርዓት ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ በሚገኙ 80 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሙከራ ደረጃ ይሰጣል።

#ለማስታወሻ - የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ፦

- ከኢንተርናሽናል እና የማህበረሰብ  ትምህርት ቤቶች ውጭ ስርዓተ ትምህርቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ባሉ የግል እና  የመንግስት ትምህርት ቤቶች ይተገበራል።

- ግብረ ገብ ፣ አገር በቀል ዕውቀት ፣ ሙያና የቀለም ትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ምርትና ተግባር፣ ጥናት እና ምርምር ትኩረት ተደርጎባቸው ይሰጣሉ።

- ከ1ኛ - 6ኛ ክፍል የግብረ ገብ ትምህርት ይሰጣል።

- ለ7ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ራሳቸውን የቻሉ የትምህርት ዓይነቶች ሆነው ይሰጡ የነበሩት ኬሚስትሪ ፣ ባዮሎጂ እና ፊዚክስ " ጄኔራል ሳይንስ " ተብለው ይሰጣሉ። ጆግራፊና ሂስትሪም ተቀናጅተው የሚሰጡ ይሆናል።

- ከ1ኛ - 6ኛ ክፍል ላሉ የክፍል ደረጃዎች ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ ይሰጣል፤ ከ7ኛ ክፍል -12ኛ ክፍል ያሉት ደግሞ ሁሉም ተማሪ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ይማራል።

- ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ያሉት ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ይወስዳሉ።

- 3ኛ ክፍል ላይ ተጨማሪ ቋንቋዎችን መስጠት ይጀመራል፤ በክልሎቹ ውስጥ በስፋት የሚነገረውን #ተጨማሪ_ቋንቋ በመምረጥ ተማሪዎቹ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲወስዱት ይደረጋል።

-  አጠቃላይ ፈተና በክልል ደረጃ 6ኛ ክፍል ላይ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ላይ ይሰጣል።

- የ7ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች " ኬሪየር ኤንድ ቴክኒካል ኤጁኬሽን " የተባለ ትምህርት ይሰጣቸዋል። የእርሻ ትምህርት፣ አካውንቲንግ፣ ቢዝነስና ጀነራል የሆነውን የሥራና ክህሎት ትምህርት በሙያ ትምህርት ተካቶላቸው ይሰጣቸዋል።

- 11ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ላይ ጤና ፣ ግብርና፣ የእርሻ ትምህርት፣ ማኒፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን ፣ ቢዝነስ ፣ አካውንቲንግ የመሳሰሉት የሙያ ትምህርትነቶችን እንዲማሩ ይደረጋል። 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከእነዚህ የሙያ ትምህርቶች ውስጥ የመረጡትን ይወስዳሉ።

- የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍልን እንዲሁም ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ያሉ የተመረጡ 5 የትምህርት አይነቶችን መጸሐፍት ዝግጅት ትምህርት ሚኒስቴር ያከናውነዋል ፤ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያለውን የትምህርት መፀሐፍት ክልሎች በራሳቸው ባህልና አካባቢያዊ ሁኔታ ቃኝተው ያዘጋጁታል።

መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ / ኢፕድ የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ም/ ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ በኦሮሚያ ያለው ጦርነት በዜጎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል አሉ። አቶ ጃዋር ፤ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በጮቢ እና በሜታ ወልቂጤ (ምዕራብ ሸዋ)፣ በነቀምቴ (ምስራቅ ወላጋ)፣ ቢላ፣ ናጆ፣ ማንዲ (ምዕራብ ወለጋ) በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል ብለዋል። ንፁሃን በሚደረገው የተኩስ…
#ተጨማሪ

አቶ ጃዋር መሀመድ ከኢትዮጵያ ቀውስ ጋር በተያያዘ ‘ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ’ ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ እየመረጡ መጮሃቸው ነው ብለዋል።

" ባለፉት አራት አመታት በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የጦር ወንጀሎች እና የዓለም አቀፍ የሰብአዊ ህግ ጥሰቶች በተደጋጋሚ ተፈጽመዋል " ያሉት አቶ ጃዋር ፤ በዓለም አቀፉ ህበረሰብ ምንም አይነት ትኩረት አልተሰጠም ፤ ሌላው ቀርቶ የተለመደውን ‘ በጣም ያሳስበናል ’ የሚሉ ነገሮችን አይሉም " ሲሉ ነቅፈዋል።

" አልፎ አልፎ ሽፋን ይሰጡ የነበሩትም አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂውማን ራይትስ ዎች እንኳን ተስፋ የቆረጡ ይመስላሉ " ሲሉ ገልፀዋል።

" እየመረጡ መጮህ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም አያመጣም። " ያሉት አቶ ጃዋር መሀመድ " ወይ ለአጠቃላይ ሀገራዊ የሰላም ሂደት እንሰራለን ወይም ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ሲቀጥሉ እንመለከታለን። " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ነገ የሚወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ... የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት የተናገሩት ፦ " በእጣው ብቁ የሚሆኑት የ20/80 (ስቱዲዮ ፣ ባለ 1 እና ባለ 2) ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) በመመሪያው መሠረት ዝቅተኛውን የ60 ወራት ቁጠባ መጠን እንዲሁም የባለ 3 መኝታ ነባርና አዲስ ተመዝጋቢዎች (2005) ዝቅተኛውን የ84 ወራት ቁጠባ መጠን ያሟሉ።…
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት ዕጣ #ዛሬ_ከሰዓት ይወጣል።

ይኸው እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአዲስ አበባ ነዋሪ የሚጠብቀው የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ ይተላለፋል ።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ/Addis TV የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት በቀጥታ ስርጭት እንደሚያስተለልፈው ቀደም ብሎ አሳውቋል።

እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለፃ ፤ ዛሬ ዕጣ የሚወጣባቸው በ20/80 18,930 ቤቶች እና በ40/60 6,843 ቤቶች በድምሩ 25, 791 ቤቶች ሲሆኑ ከፍተኛ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረው የባለ ሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎችን ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት #ተጨማሪ 300 (ሶስት መቶ) ቤቶችን ቀሪ ስራዎችን በማከናወን ለነባርና ለአዲሰ ተመዝጋቢዎች በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጁ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከደቂቃዎች በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት በይፋ ይካሄዳል።

ይኸው የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ ይሰራጫል።

ዛሬ ዕጣ የሚወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፦

👉 በ20/80 18,930 ቤቶች
👉 በ40/60 6,843 ቤቶች
👉 አጠቃላይ 25, 791 ቤቶች

እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለፃ #ተጨማሪ 300 (ሶስት መቶ) ቤቶችን ቀሪ ስራዎችን በማከናወን ለነባርና ለአዲሰ ተመዝጋቢዎች በዕጣ ለማስተላለፍ ዝግጁ ተደርጓል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ የዕጣውን አወጣጥ ሥነሥርዓት ተከታትለን የምናሳውቅ ሲሆን የሚመቻችሁ በአዲስ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት መከታተል እንደምትችሉ ለመጠቆም እንወዳለን።

@tikvahethiopia