TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢሬቻ2011

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ #ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦሮሞ ህዝቦች እንኳን በፍቅርና #በአንድነት ለሚከበር የኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን ብለዋል፡፡

ኢሬቻ የገዳ ስርዓት አካልና የምስጋና የሰላም ቀን ነው፣ የኦሮሞ ምኞት ፍቅር፣ ብልጽግና፣ ባህሉ ደግሞ አብሮነት ነው፤ ኦሮሞ ለምለም ይዞ ለፈጣሪ #ምስጋና ያቀርባል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የኦሮሞ ህዝብ የሚተዳደርበት #የገዳ ስርዓት ለዘመናዊ ዴሞክራሲ መሰረት የሆነና ታናሽ ታላቅን አክብሮ ከተላቅ የሚመር፣ ታላቅ ደግሞ ታናሽን በማብቃት ስርዓትን የሚያስቀጥል ስርዓት መሆንም ዶ/ር ዐቢይ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘንድሮን የኢሬቻ በትግል የተገኘውን ለውጥ የሚናስቀጥልበት፣ በፍቅር፣ በአንድነትና በእኩልነት አገር የሚንመራበትና የገዳ ልምዶችን የሚንቀስምበት ጊዜ በመሆኑ ደስታችንን ድርብ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ዐቢይ የዘንድሮ ኢሬቻ ባህላችንንና አንድነታችንን የምናጠናክርበት፣ የአባገዳዎች መልዕክት #የምንሰማበትና የምንተገብርበት ይሆናል የሚል ተስፋም አለን ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል በፖለቲካ አለላካከት #ልዩነቶቻቸን ሳይገድቡን በፍቅርና በአንድነት አብሮ ለመስራት የሚንመራረቅበት እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡

አሸናፊ ሀሳብ በመያዝ አንድነታችንን አጠንክረን፣ ለሰላም፣ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር፣ ለፌዴራሊዝምና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አብረን መስራት አለብን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ሰላማችንን ማስጠበቅ በእጃችን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሰላማችንንና ባህላቸን በመጠበቅና በማስጠበቅ አገርን መገንባት አለብን፤ በኢሬቻ በዓል ላይ ሰላማችንን በማስጠበቅ ለዓለም ምሳሌ መሆን አለብንም ብለዋል፡፡

ዘመኑ በፍቅርን አቅፈን ጥላቻን የምናሸንፍበት ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአፊኒ ባህላዊ ስነ ስርዓት!!

"በሀገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል #የወጣቱ ሚና ከፍተኛ መሆን አለበት" – የሲዳማ ብሄር የሀገር ሽማግሌዎች
.
.
.
በኢትጵያ የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል የወጣቱ ሚና ከፍተኛ መሆን እንዳለበት የሲዳማ ብሄር የሀገር ሽማግሌዎች አሳሰቡ፡፡ በብሄሩ አመታዊው የአፊኒ ባህላዊ ስነ ስርአት #በሶሬሳ_ጉዱማሌ በሃዋሳ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

ሲዳማ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ተዋዶ እና ተፍቅሮ #በአንድነት የመኖር እሴቱን ጠብቆ የኖረ ነው ያሉት የሀገር ሽማግሌዎች ወጣቱም ይህን አኩሪ ባህል ሊጠብቀውና ማንኛውም ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ሊያቀርብ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ በበኩላቸው የሲዳማ ብሄር በአቃፊነቱ እንጂ በጥላቻ አይታወቅም ስለዚህም ከሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር በአንድነት ለመኖር የዘመናት ባህሉ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ወጣቱም የአባቶቹን ምክር በመስማት ሊተገብር ይገባል ያሉ ሲሆን ይህ መሰል ባህላዊ ስርአት ሌሎችም እንደተሞክሮ ሊጋሩት እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶችም የሀገር ሽማግሌዎችን ምክርና ተግሳፅ በስርአቱ መሰረት በመቀበል ለሀገራዊ ለውጡ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ fbc ገልፀዋል።

በወጣቱ ስም በሃዋሳም ሆነ በዞኑ የሚነሱ የሰላም መደፍረሶችን በመከላከል ህግና ስርአት እንዲከበር የበኩላችንን እንወጣለን ብለዋል ተሳታፊዎቹ፡፡

ክልል የመሆን ጥያቄ እና ሙሰኞችን የማጋለጥ ሂደት በሰላማዊ መንገድ እንደሚታገሉ ተናግረዋል።

በአፊኒ ስርአት የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶቹ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ቃል በመግባት አጠናቀዋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ #በጳጉሜ_ወር ለሀገር ሰላም እና አንድነት በመላው ዓለም በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፀሎት እና ምህላ ወስኗል። ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፥ ቋሚ ሲኖዶሱ 5ቱን የጳጉሜ ቀናት በፀሎትና ምህላ እንዲታሰብ መወሰኑን ገልፀዋል።…
"...ቋሚ ሲኖዶስ በወሰነው መሰረት ህዝበ ክርስቲያኑ #በአንድነት እና #በፍቅር ሊፀልይ ይገባል" - ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት የውጭ ጉዳይ መምሪያ የበላይ ኃላፊና የድሬዳዋና ጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶክተር) ፥ ቋሚ ሲኖዶስ በወሰነው ውሳኔ መሰረት ከጳጉሜ 1 እስከ 5 ድረስ ባሉት ቀናት በአንድነት እና በፍቅር መፀለይ እንደሚገባ ገልፀዋል።

"ምዕመናኑ በአምስቱ ዕለታት #ስለሀገር ሰላም፣ #ፍቅር እና #አንድነት፣ በፀሎት እና በምዕላ በትጋት ጊዜውን እንዲያሳልፍ ጥብቅ መመሪያ የተላለፈ መሆኑን በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ለየአብያተክርስቲያናቱ እና ገዳማቱ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ላሉ ሁሉ እነዚህን ዕለታት በፀሎት እና በምዕላ እንዲያሳልፍ ተወስኗል" ሲሉ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶክተር) ለEOTC ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia