TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አንደኛ ዓመት በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል። በዚህም መግለጫ የሰላም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ እንዲከበር ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቋል። በአከራካሪ ቦታዎች ተፈናቃዮች እንዲመለሱና በህገመንግቱ መሰረት ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ አቋም ይዞ ተግባር ላይ እንዳለ አመልክቷል። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ፤ መንግሥት በጦርነቱ የመጨረሻ…
" ለትግራይ ህዝብ ደህንነት የሚያሰጋ ነገር ከሌለ #ከመከላከያ_ሃይል ውጪ ያሉት የታጠቁ ሃይሎች ከትግራይ መሬት ከወጡ ትጥቅ ተሸክመን የምንኖርበት ምክንያት የለም  " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አንደኛ አመት በማስመልከት ከ " ትግራይ ቴሌቪዥን " ጋር ሰፊ ቃለመጠይቅ አድረገዋል።

በዚህም ቃለመጠይቃቸው ፥ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት የትግራይ ግዛትን የተቆጣጠሩት ኃይሎችን ማስወጣትና ፣ በትግራይ ግዛት በአማራ ሃይሎች የተመሰረቱት አስተዳደሮች የማፍረስ ጉዳይ የፌደራል መንግስት ግዴታዎች ናቸው ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " የፕሪቶሪያ ውል የቶክስ ድምፅ የማቆም ስምምነት ነው " ያሉ ሲሆን  ከዚህ አኳያ ስኬታማ ውልና ስምምነት ነው ብለውታል።

በቃለመጠይቁ ላይ  ' ስለመሬት ይገባኛል ' ጉዳይም አንስተው የተናገሩት አቶ ጌታቸው " በአማራ ክልል በኩል ሃቅ የሚመስል የመሬት ይገባኛል ጥያቄ እንዳለ አስመስሎ የሚቀርብ አለ። በኔ አረዳድ እንደዛ አይነት ጥያቄ የለም ነው የምለው " ሲሉ ተደምጠዋል።

በኢትዮጵያ #የፌዴራል_መንግስት_ተደራዳሪዎች በኩል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አጨቃቂዎቹን የምእራብ ፣ ሰሜን ምእራብን ደቡብ ትግራይ ማስተዳደር የለበትም የሚሉ እንደነበሩ የክልሉ አስተዳዳሪ አንስተዋል።

አቶ ጌታቸው " ለትግራይ ህዝብ ደህንነት የሚያሰጋ ነገር ከሌለ #ከመከላከያ_ሃይል ውጪ ያሉት የታጠቁ ሃይሎች ከትግራይ መሬት ከወጡ ትጥቅ ተሸክመን የምንኖርበት ምክንያት የለም " ያሉ ሲሆን " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የፈረምነው የትግራይ መሬት ቆርሰን ለመስጠት ሳይሆን ፤ በህገ-መንግስት መሰረት ይፈታ ስለተባለ ነው " ብለዋል። 

ከተፈናቃዮች መመለስ ጋር በተያያዘም የትግራይ ምእራባዊና ደቡባዊ አከባቢዎች እንዲሁም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስ ጉዳይ ቀደም ብሎ መፈፀም የነበረበት ተግባር እንደነበር ገልጸዋል።

" ይሁን እንጂ የፌደራል መንግስት ተፈናቃዮች እስከ ሰኔ 21/2015 ዓ.ም ወደ ቄያቸው ይመለሳሉ ብሎ የገባውን ቃል አልፈፀመም " ብለዋል።

የሰላም ስምምነት ትግበራው እንዲፋጠን ከአማራ ክልል አመራሮች ለመስራት ጥረት መደረጉን ያነሱት አቶ ጌታቸው " በፕሪቶሪያ ውል ላይ መደራደርና መገምገም ስለጀመሩ ዉይይቱ ተቋረጠ " ሲሉ ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈ በቃለመጠይቁ የሪፈረንደም ጉዳይም ተነስቶ ነበር።

አቶ ጌታቸው ሪፈረንደም ለማካሄድ የትግራይ ክልል ተወካዮች ምክር ቤት የግድ መቋቋም እንዳለበት ተናግረዋል።

" ከዚህ ውጭ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሪፈረንደም የማካሄድ ህገ-መንግስታዊ ስልጣን የለውም " ሲሉ አሳውቀዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሪቶሪያ ውል እንዳይፈፀም እግር እየጎተተ ነው የሚለው ንግግር የተጋነነ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ፤ #የአፍሪካ_ህብረት ግጭት ዳግም እንዳይነሳ በማረጋገጥና ውሉ በተማሏ መንገድ እንዲፈፀም ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አስገንዝበው " ሁሉም ልዩነቶች ሰላም ብቻ ነው መፈታት ያለባቸው ፣ ከጥይት ቶክስ #ለውይይት ቦታ መስጠት አለብን። ትግራይ የአውዳሚ ጦርነት መነሃሪያ እንድትሆን አንፈቅድም። " ብለዋል። 

አቶ ጌታቸው የጊዜያዊ አስተዳደራቸው ዋና ትኩረት የትግራይ ህዝብ #ደህንነት_ማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸው ፤ " የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀስ ማኛውም አካል ወይም ሃይል ተቀባይነት የለውም እንታገለዋለን። " ብለዋል።

በትላንትናው ዕለት የፌዴራል መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፦

-  የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአንዳንድ ነገሮች ወደኋላ እየቀረና የሰላም ስምምነቱን በተሟላ ሁኔታ ሳይፈፅም እያነከሰ ነው ሲል መተቸቱ ፤

- አከራካሪ የሚባሉ አካባቢዎችን በተመለከተ አቋም ወስዶ እንደሰራ እንደሆነ ፤ ክረምት ደርሶ የእርሻ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ፣ የአካባቢ ነዋሪዎች በመረጧቸው አካላት እንዲተዳደሩ፣ በመጨረሻም ደረጃ በደረጃ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ አቅጣጫ መቀመጡን እና ይሄንንም ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ማስታወቁ ፤

- የሰላም ስምምነቱ #በተሟላ_ሁኔታ_እንዲፈፀም ማድረግ ያለበትን ሁሉ ቢደረግም በዚያኛው ወገን እግር የመጎተት አዝማሚያ እንደሚታይ መግለፁ አይዘነጋም።
  
@tikvahethiopia