TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በየቤታችን እንወያይ!

የዚህች ሀገር ችግር ተመዞ አያልቅም። ከእናተው ጋር ሆኜ ብዙ እየሰማው እና እያየሁ እንደመዋሌ ላለፉት 3 ዓመታትም በየቀኑ እዚሁ ከናተው ጋር መረጃዎችን ስቀባበል ስውል እንደተረዳሁት ትልቁ ችግራችን ስለሰው ክቡርነት በሀገራችን ብዙ ስራ አልተሰራም። ዛሬ ዝርፊያው፣ ማሳደዱ፣ መግደሉ፤ ማፈናቀሉ...የምንሰማቸው ዘግናኝ ኢ ሰብዓዊ ወንጀሎች ሁሉ ሰው ምን ምንድነው የሚለውን በጥልቀት ካለመረዳት የመጣ ይመስለኛል። አንድን ሰው በሰውነቱ ካከበርነው ብሄሩን፣ ዘሩን፣ ቋንቋን፣ ማንነቱን...ሁሉንም እናከብርለታለን።

#በጥቅም ተደልለንም፤ በግለሰቦች ቅስቀሳም ወገናችንን የምንጎዳውም፤ ሰው የምናፈናቅለውም፤ ሰው የምንጠላውም #ሰውነትን በአግባቡ ስላልተረዳን ነው። መጀመሪያ ሰው እንሁን! ሰው ስንሆን የሌላው ሞት የኛ፤ የሌላው ስቃይ የኛ፤ የሌላው በደል የኛ ...ይሆናል! ሰውን ሁሉ እንደራሳችን ማየት ስንጀምር #ሰላም እንሆናለን።

ስለአንድነት፣ ስለነፃነት ፣ስለዴሞክራሲ ለማውራት በቅድሚያ እውነት እኛ #ሰውነት_ገብቶናል?? ብለን ልንጠይቅ ይገባል። ሁላችንም በሰውነት ጥላ ስር ከተከለልን የስቃይ እና የመከራ ጊዜው ያጥራል።

•እንደመነሻ ሀሳቤን ገልጫለሁ እናተስ ምን ትላላችሁ...?

ሀሳባችሁ ገፁ ላይ እንዲለጠፍ...👇

•በአማርኛ ፅሁፍ አጠር አድርጋችሁ ሀሳባችሁን ማቅረብ ወይም

•በድምፅ ከ4 ደቂቃ ያልበለጠ በጨዋ ቋንቋ የግል ምልከታችሁን ብቻ በ @tsegabwolde መላክ ይቻላል!

🔹ሚቀድመውን እናስቀድም! ከምንም ነገር በፊት ሰውነት ይቀድማል!! እውነት እኛ የሌላውን ስቃይ እንደራሳችን እናያለን?? ወይስ እኛን ሊያስለቅሰን የኛ ዘመድ ወይም የኛ ብሄር ሰው መሆን አለበት??
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም አዲስ ዓመት!

ውድ በዚህ ቤት #ሰውነትን አስቀድማችሁ የተሰባሰባችሁ የሀገራችን ልጆች እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

ሁላችን እንደምናስታውሰው 2013 በገባ በጥቂት ወራት በሀገራችን ጦርነት ተቀስቅሶ ደስታ የተሞላ፣ ሰላም የሰፈነበት፣ ብዙ እቅዶቻችን የምናሳካበት ብለን ያሰብነው ዓመት በጦርነት፣ ሰቆቃ፣ በዜጎች ሞት፣ በረሃብ፣ በጭንቀት፣በደህንነት ስጋት ተሞልቶ ተሰናብተነዋል።

በ2013 በጦርነት ምክንያት ቁጥራቸውን የማናውቃቸው ነገር ግን እጅግ በርካታ ዜጎቻችን ረግፈዋል፣ አንዳዶች እንደወጡ ቀርተዋል፣ ባላሰቡበት ተጨፍጭፈዋል፣ ሺዎች አካላቸው ጎድሏል፤ሴት እህቶቻችን ተደፍረዋል ተጠቅተዋል ሚሊዮኖች ተርበዋል ተጠምተዋል፣ሚሊዮኖች ከገዛ ቀያቸው ተፈናቅለው ተሰደዋል።

በትግራይ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያ (ወለጋ)፣ ቤ/ጉሙዝ...ምንም ከጦርነት ጋር ንክኪ የሌላቸው፣ ስለሚሆነው ነገር ፍፅሞ የማያውቁ ንፁሃን ዜጎቻችን፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ህፃናት ከነተስፋቸው አሸልበዋል፤በወጡበት ቀርተዋል፤እናቶች ልጆቻቸውን አንጠልጥለው ተሰደዋል፣አባቶች አልቅሰዋል፣አንብተዋል።

በዓመቱ ወንድም እህቶቻችሁን ያጣችሁ፣ የምትወዱትን የተነጠቃችሁ፣ እናት አባቶች ፅናቱን ብርታቱን ይስጣችሁ። አሁንም በችግር ላይ ላሉ ወገኖቻችን ፈጣሪ ይድረስላቸው።

እንደአንድ ሀገር ዜጋ ይህን አዲስ አመት የምንቀበለው በፍፁም የስሜት መረበሽ ውስጥ ቢሆንም ፈጣሪ ሁሉን እንዲያቀናው እንማፀናለን።

ዓመቱ የሰላም፣ግጭትና ሰቆቃ የማንሰማትበት፣ ከጎናችን ማንም የማይጎድልበት እንዲሆን እንመኛለን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤታችን፤ መሰብሰቢያችን ነው፤ በአዲሱ ዓመት ቤተሰባዊ ቅርርባችን ሚጠናከርባቸውን ሀሳቦች ለእናተ እንደምናቀርብ ከወዲሁ ቃል እንገባለን።

❤️ኢትዮጵያ እናታችን ተከብራ ትኑርልን❤️

@tikvahethiopia