TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

ለ530 የፌዴራል ታራሚዎች #የገና_በዓልን ምክንያት በማድረግ #ምህረት መደረጉን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታወቀ። የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠልና የፓለቲካ ምህዳር ለማስፋት ለታራሚዎቹ ምህረት መደረጉን ነው ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ያስታወቀው።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዱዓ እና ምህላ እየተደርገ ነው!

የሰዎች ህይዎት ላይ እየደረሰ ያለው በደል #እንዲቆም ምህላ እና ዱዓ እየተደረገ መሆኑን የሀይማኖት አባቶች አስታወቁ። በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በተፈጠረው #ግጭት ምክንያት በሰዎች ህይዎት እየደረሰ ያለው ጉዳት #ምህረት እንዲያገኝ ነው #ምህላ እና #ዱዓ እየተደረገ የሚገኘው። በሁለቱ ዞኖች እየተስተዋለ ያለውን የሰዎች #ሞት#መፈናቀል እና #መሰደድ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የኦርቶዶክስ እና የእስልምና ሀይማኖት አባቶች አውግዘዋል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"መኖር ማለት አለመሞት ከሆነ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እየኖረ ነው። ግን መኖር ማለት እራስን መሆን፣ ለዓላማ መቆም፣ ህሊናን አለመዘንጋት፣ ፍርድን አለማጓደል፣ ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌላው እራስን መስዋዕት ማድረግ ብሎም አርአያ የሚሆን ነገር ጥሎ ማለፍ ከሆነ ስንቶቻችን ነን በህይወት ያለነው?" ዶክተር #ምህረት_ደበበ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህዝብ ተወካዮች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት በምክር ቤቱ ተገኝተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ። @tikvahethiopia
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ከፓርላማ አባላት በርካታ ጥያቄ ተነስቶላቸው በአሁን ሰዓት ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

ከፓርላማ አባላት መካከል አቶ ክርስቲያን ታደለ መንግስት በእነ አቶ ስብሃት ነጋ ላይ የተነሰረተውን ክስ ያቋረጠው ከህግ አግባብና ከህገመንግስቱ በሚጣረስ መልኩ ስለሆነ ማስተካከያ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

አቶ ክርስቲያን ፥ " መንግስት መጀመሪያ ዜናውን ሲነግረን በ #ምህረት ነው የተፈቱት ያለ ሲሆን እነ አቶ ስብሃት ነጋን የመሰለ ሰው በሰው ልጆች ላይ ግፍ ፈፅሟል፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ የተጠረጠረን ወይም የከሰሰውን ሰው በምህረት መልቀቅ እንደማይችል ሲረዳ በፍትህ ሚኒስትሩ በኩል ይቅርታም ምህረት አይደለም የክስ ማቋረጥ ውሳኔ ነው በሚል ማብራሪያ ሰጥቷል " ሲሉ አስታውሰዋል።

አክለውም ፥ " መንግስት የሰራውን ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀውን ስህተት ለማረም እድል አለው " ያሉት አቶ ክርስቲያን " ይህን እድል ለመስጠት ነው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን የምጠይቀው። እነዚህ ሰዎች እኔ በምወክለው የአማራ ህዝብ ተደራጅተው ያደረሱበት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት የህሊና መጉሳቆል ለመዘርዘር በቂ ጊዜ የለኝም " ብለዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር ያሳለፈው የክስ ማቋረጥ ውሳኔ ከህግ የሚጣረስ በመሆኑ ውሳኔውን ውድቅ በማድረግ ክሱ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስትና በም/ቤቱ በአሸባሪነት በተፈረጀው ህወሓት መካከል ድርድር እየተደረገ እንደሚገኝ በተለያየ ሚዲያ እየተሰማ መሆኑን ያነሱት የፓርላማው አባል፦

• ምን ያህል እውነት ነው ?
• እውነት ከሆነ ማን ከማን ጋር ነው እየተደራደረ ያለው ?
• በማን አደራዳሪነት ?
• ህወሓት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ ስለሆነ መንግስት የሚያደርገው ድርድር ከህጋዊነቱ እንዴት ይታያል ?
• የድርድሩ ማህበራዊ፣ ህጋዊ እና ሞራላዊ ቅቡልነት የሚረጋገጠው ድርድሩ ግልፅ እና አሳታፊ ሲሆን ነው ድርድሩ በኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ቀጥተኛ ተጎጂ በሆኑት የአፋር እና የአማራ ህዝብ የሚያሳድረው ስሜቱ ተጢኗል ወይ ? ሲሉ ጠይቀዋል።

እንዲሁም በጦርነቱ የደረሰው ውድመት በአማራ እና አፋር ለማካካስ የፀደቀው የድጎማ በጀት አንድ ተቋምን ጠግኖ ወደነበረበት የሚመልስ ባለመሆኑ ባለበጀት ክልሎች እና የፌዴራል መንግስት በልዩ ሁኔታ ሀገር ለማዳን ሲሉ ከፍተኛና ቀውስ ላስተናገዱ ክልሎች ለምን በበቂ ሆኔታ በጀት መደገፍ አልቻሉም ? ሲሉ ጠይቀዋል።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ፤ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር እና ከምዕራብውያን ሀገራት ጋር ያላት ወቅታዊ የዴፕሎማሲ ግኝኑነት ምን ይመስላል ? ሀገራዊ የሰህንበት ሁኔታው ባልተቀለበሰበት ሁኔታና በተለያዩ ምክንያቶች በቂ ወታደራዊ አመራሮች ባልተፈሩበት ሁኔታ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮኖችን በአምባሳደርነት መሾሙ ያለው ተገቢነት ላይ ማብራሪያ ይሰጥ ሲሉ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia