TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሩስያ ከዚህ ቀደም ማንኛውም አይነት #የግብረሰዶም እንቀስቃሴን #ሕገወጥ እና #ጽንፈኛ በማለት ፈርጃ የነበረችው ሩስያ አሁን ደግሞ የግብረሰዶም እንቅስቃሴን #የአክራሪነት እና #የሽብር ድርጊት ዝርዝር ውስጥ አካታዋለች። በዚህም ማንኛውም ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም እንቅስቃሴ በሩስያ በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ዝርዝር ውስጥ ተካቷል። ውሳኔው የተደረሰው የሩስያ የፍትህ ሚኒስቴር የቀረበለትን አቤቱታ…
#Russia #Putin

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ምሽት ላይ የሩስያ ፖሊስ ሞስኮ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ባሮችን እና የምሽት መዝናኛ ክለቦችን ሲያስስ ነው ያደረው።

አሰሳው ከግብረሰዶማውያን ፕሮፓጋንዳ ቁጥጥር ጋር የተያያዘ ነው።

በሩስያ ማንኛውም አይነት የግብረሰዶማውያን እንቅስቃሴ ማስተዋወቅ ወይም ፕሮፖጋንዳ መስራት በህገወጥነት መፈረጁ ይታወሳል።

ፖሊስ በቅዳሜ ምሽት አሰሳው በየባሩና በየምሽት ክለቡ እየገባ ጥብቅ ፍተሻ አድርጓል።

በወቅቱም ስማርት ስልኮች፣ ላፕቶፖች፣ የቪድዮ ካሜራዎች ተወርሰዋል።

በየመሸታ ቤቶቹ የተገኙ ሰዎች ዶክመንታቸው በፖሊስ ሲፈተሽ አድሯል።

የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ፤ የታገደውን የግብረሰዶማውያን እንቅስቃሴ ፖሮፖጋንዳ ሲያሰራጭ እንደነበር በተጠረጠረ አንድ በስም ባልገልጸው የምሽት ክለብ ውስጥም አሰሳና ፍተሻ መደረጉን ገልጿል።

ታስ እንደዘገበው ደግሞ " Men Travel " የተባለ የጉዞ ኤጀንሲ ኃላፊ ከፀረ ግብረሰዶማውያን ህግ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ሰውየው በሩስያ አዲስ አመት ወቅት ወደ ግብፅ " መደበኛ ያልሆኑ የወሲብ እሴቶችን " የሚደግፉ ደጋፊዎችን ጉዞ ሊያዘጋጅ እንደሆነ በመጠርጠሩ ነው።

የሩስያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓለም አቀፍ የግብረሰዶማውያን እንቅስቃሴን " የፅንፈኞች እና አክራሪዎች እንቅስቃሴ " በማለት በህገወጥነት ፈርጆ ካገደ ሰሞኑን አንድ አመት ደፍኗል።

ሩስያ የግብረሰዶም እንቅስቃሴን የአክራሪነት እና የሽብር ድርጊት ዝርዝር ውስጥም ያካተተች ሲሆን የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት በሀገሪቱ እውቅና የለውም።

በሌላ በኩል ፥ ባለፈው ቅዳሜ የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፤ ጄንደር አፊርሚንግ ኬር (የአንድን ሰው የጾታ ማንነት መደገፍ እና ማረጋገጥ) ወይም ጾታ መቀየር ህጋዊ የሆነባቸው ሀገራት ዜጎች የሩስያ ልጆችን በጉዲፈቻ እንዳይወስዱ የሚያግድ ህግ ላይ ፈርመዋል።

በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ፑቲን ሰዎች ልጅ እንዳይወልዱ የሚያበረታታ ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ / ስርጭትን የሚያግድ ህግ አፅድቀዋል።

#TikvahEthiopia
#Russia #TASS

@tikvahethiopia