TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HumanRightsWatch

የኢትዮጵያ መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ ዘግቶ የቆየውን የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት ገደብ በፍጥነት እንዲያነሳ ዓለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሒውማን ራይትስ ዎች ጠይቋል።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫው እንዳስታወቀው ለሁለት ወራት የተዘጋው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ቤተሰብ እንዳይገናኝ አድርጓል፤ በአካባቢው የነፍስ አድን ሥራ በአግባቡ እንዳይከናወን አደናቅፏል ሲል ወቅሷል።

መንግስት በአካባቢው እየወሰደ ያለው ወታደራዊ ርምጃም መረጃ እንዳይወጣ አስተዋጽዖ ማድረጉንም መግለጫው አመልክቷል።

ከታኅሣስ 24 ቀን፤ 2020 ጀምሮ አንስቶ በምዕራብ ኦሮሚያ በቄለም ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ምሥራቅ ወለጋ ዞኖች የኢንተርኔት እና የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አገልግሎት መቋረጡን ነዋሪዎች ማመልከታቸውን ያተተው መግለጫው በጥቂት ዋና ዋና ከተሞች ብቻ የስልክ እና የመልዕክት አገልግሎት ብቻ እንደነበር አስታውቋል።

More https://telegra.ph/HRW-03-10

#HumanRightsWatch #DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HumanRightsWatch

በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ ወቅት ይሁነኝ ብሎ ኢንተርኔት ማቋረጥ አሊያም መገደብ ገዳይ ሊሆን ይችላል ሲል ሒዩማን ራይትስ ዎች አስጠነቀቀ። ድርጊቱ በርካታ መብቶችን ይጥሳል ብሏል። እነ ኢትዮጵያ ሕይወት ለማዳን በአፋጣኝ አገልግሎቱን እንዲመልሱ ጠይቋል።

ሒዩማን ራይትስ ዎች እንዳለው ኢትዮጵያ ፣ ባንግላዴሽ ፣ ሕንድ እና ምያንማር የኢንተርኔት ግልጋሎት ያቋረጡ ናቸው። በኢትዮጵያ በወለጋና ጉጂ ዞኖች የተቋረጠው ኢንተርኔት እና ስልክ ሥራ እንዲጀምር የጤና ባለሙያዎችና ፓርቲዎች ጭምር እየጠየቁ እንዳለ ይታወቃል።

https://www.hrw.org/news/2020/03/31/end-internet-shutdowns-manage-covid-19

#EsheteBekele Pic : #BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#HumanRightsWatch

የሁቲ ታጣቂዎች ኮቪድ-19ኝን ምክንያት በማድረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከሰሜናዊ የመን አስወጥተዋል እንዲሁም ገድለዋል ሲል ሂዩማን ራይተስ ዎች ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ወደ ሳዑዲ ድንበር የተባረሩት ስደተኞች በድንበሩ ጠባቂዎች ሌላ ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ የተወሰኑ ሰዎች ሲሞቱ በመቶዎች የሚቆጠሩት ወደ ተራራማ አካባቢ ሸሽተዋል ብሏል።

ድምፃቸውን ለመብት ተሟጋቹ ድርጅት የሰጡ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ለቀናት ያለምግብ እና ውሃ እንደቆዩ ተናግረው ከዚያ በኋላ ወደ ሳዑዲ መግባት ቢችሉም ንፅሕና በሌለው ሥፍራ ታጉረው እንደከረሙ ተናግረዋል።

ሕፃናትን ጨምሮ ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች አሁንም በየመን እና ሳዑዲ ተራራማ ድንበር አካባቢ ሊኖሩ እንደሚችሉ ድርጅቱ ገምቷል።

የሂውማን ራይትስ ዎች ጥናት ቡድን አባላት ናዲያ ሃርድማና የሳዑዲና የየመን ኃይሎች ኢትዮጵያውያኑ ላይ የፈፀሙትን ግፍ ወቅሰው የተባበሩት መንግሥታት ለጉዳዩ መፍትሔ እንዲሰጠው አሳስበዋል።

HRW:https://www.hrw.org/news/2020/08/13/yemen-houthis-kill-expel-ethiopian-migrants

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#HumanRightsWatch

በሪያድ ስደተኞች የማቆያ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች አስከፊ በሆነ አያያዝ ውስጥ እንደሚገኙ ሂዩማን ራይትስ ዋች ገለጸ።

ሕጋዊ የሆኑ ሰነዶች ሳይኖራቸው ሥራ ፍለጋ ወደ ሳዑዲ የገቡ እነዚህ ስደተኞች ተይዘው የሚገኙበት ማዕከል የተጨናነቀ ከመሆኑ ባሻገር በጥበቃዎች ማሰቃየት እንዲሁም ድብደባ እንደሚፈጸምባቸውም አመልክቷል።

የማዕከሉ ጥበቃዎች በጎማ በተሸፈነ ብረት በሚፈጸምባቸው ድብደባ ጉዳት እንደሚደርስባቸው የገለጸው ሂማን ራይትስ ዋች፤ በጥቅምት እና ኅዳር ወራት ውስጥ ቢያንስ ሦስት (3) ለሚሆኑ ስደተኞች ሞት ምክንያት መሆኑን በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። (BBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዓለም ስለማይናማር ምን አለ?

#Australia

የአውስትራሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ማራይዝ ፓይኔ ፤ በማይናማር ወታደራዊ ኃይሉ ስልጣን መቆጣጠሩ እና ሲቪል መሪዎች መታሰራቸውን የሚገልፁ ሪፖርቶች እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል። ወታደሩ የህግ የበላይነትን እንዲያከብር ፣ ችግሮችን በህግ ብቻ እንዲያስተካከል፤ በአስቸኳይ የሲቨል መሪዎችን እና ሌሎችንም ያለህግ አግባብ ያሰራቸውን አካላት እንዲለቅ ጥሪ አቅርበዋል።

#UnitedStates

አሜሪካ በማይናማር እየሆነ ያለውን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለች መሆኑን ገልፃለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጉዳዩ በጣም እንዳሳሰባቸውን ገልፀዋል፤ ወታደሩም ውሳኔውን በአስቸኳይ እንዲቀለብስ አሳስባዋል። የማይማር ወታደር ሁሉንም የሲቪል መሪዎች እንዲፈታ፣ የበርማን ህዝብ ፍላጎት እንዲያከብር (Nov 8 የተካሄደውን ምርጫ ማለታቸው ነው) አሳስበዋል። ብሊንከን አሜሪካ ከበርማ ህዝብ ጎም እንደምትቆም ገልፀዋል።

#UnitedNation

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሴክሬተሪ ጀነራል አንቶኒዮ ጉተሬዝ የማይናማር የሲቪል መሪዎች መታሰራቸውን በእጅጉ አውግዘዋል። ወታደሩ ስልጣን ጠቅልሎ መያዙ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል። ድርጊቱ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ሪፎርም ላይ ችግር ሊያስከትል እንደሚችልም ጠቁመዋል።

#India

የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማይናማር ጉዳይ እንዳሳሰበው ገልጿል። ህንድ በማይናማር የዴሞክራሲያዊ ሽግግር እንደምትደግፍ ገልፃ ፤ የህግ በላይነት እና የዴሞክራሲያዊ ሂደት መከበር አለበት ብላለች፤ በሀገሪቱ ያለውን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተለች እንደሆነ አሳውቃለች።

#Singapore

ሲንጋፖር በማይናማር እየሆነ ያለው ጉዳይ እንዳሳሰባት የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጻል። ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለች እንደሆነም ገልፃለች።

#HumanRightsWatch

የHRW የኤዥያ ዳይሬክተር ብራድ አዳምስ በአስቸኳይ ያላምንም ቅድመ ሁኔታ ሳን ሱቺ እና ሌሎችም ያለህግ አግባብ የታሰሩ አካላት እንዲፈቱ ጠይቀዋል። የወታደሩ ድርጊት በህዳር ወር የተካሄደውን ምርጫ እና የማይናማር ህዝብ የራሱን መንግስት የመምረጥ መብት የሚጋፋ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#HumanRightsWatch

በትግራይ ክልል የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች በኤርትራ ወታደሮች እና በትግራይ ሚሊሻዎች መደፈራቸውን ፣ መታሰራቸውን እና መገደላቸውን ሂዩማን ራይትስ ዋች አስታወቀ።

ሂዩማን ራይትስ ዋች ይህን ያሳወቀው ዛሬ ባወጣው አዲስ ሪፖርት ነው።

ከህዳር 2020 እስከ ጥር 2021 ድረስ የኤርትራና የትግራይ ሚሊሻዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን ስደተኞችን ያቀፉትን ህፃፅና ሽመልባ የስደተኞች ካምፖችን በመያዝ በርካታ ግፎችን ፈጽመዋል ብሏል ሂውማን ራይትስ ዎች።

ሂውማን ራይትስ ዋች ፤ "በትግራይ ክልል በኤርትራ ስደተኞች ላይ ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ ግድያ፣ መድፈር እና ዘረፋ ግልጽ የጦር ወንጀሎች ናቸው" ብላል።

ያንብቡ : https://www.hrw.org/news/2021/09/16/ethiopia-eritrean-refugees-targeted-tigray

@tikvahethiopia