TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሀዋሳ⬇️

በሃዋሳ ከተማ ባለፉት ጊዚያት በተለያዩ ግጭቶች ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፖች ተጠልለው የቆዩ ተፈናቃዮች ካሳለፍነው ቅዳሜ ጀምሮ ወደ መኖሪያ ቀያቸው አየተመለሱ መሆኑ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

📌ተፋናቃዮችን ወደ ቀያቸው ከመመለስ ጎን ለጎን የእርቅ ስራ አየተሰራ ሲሆን፥ #ሰፋ ያለ #የእርቅ ፕሮግራም #በቅርቡ የሚካሄድ መሆኑንም ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ደዴሳ⬆️

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ እና በአማራ ተወላጆች መካከል የነበረውን ግጭት ወደ እርቅ የሚመራ የአባቶች ሽምግልና ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡

በሎይጅጋንፎ ወረዳ በለው ደዴሳ ቀበሌ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ እና በአማራ ተወላጆች መካከል ግጭት ተፈጥሮ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ከሁለቱም ብሄሮች በኩል አስታራቂ የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች በተገኙበት #የእርቅ ስነ ስርዓት ተፈጽሟል፡፡

ነገ ደግሞ #ይቅር መባባላቸውን የሚያበስረው የእርቅ ስርአት ባህሉን መሰረት አድረጎ ይከናወናል፡፡

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር🔝

በጎንደር የሰላምና እርቅ ጉባኤ እየተካሄደ ነው። በአማራ እና ቅማንት ማህበረሰብ የተፈጠረውን ቁርሾ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ህዝባዊ #የሰላምና #የእርቅ ጉባኤ በጎንደር እየተካሄደ ነው፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር #ደመቀ_መኮንን እና የሐይማኖት አባቶች በተገኙበት መድረክ የሰላምና ጉባኤው በዛሬው ዕለት ሲካሄድ ይውላል፡፡

ዓላማውም በጎንደር በተለይም ማዕከላዊና ሰሜን ጎንደር ዞኖች ማንነትን መሰረት አድርገው የሚነሱ ግጭቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ #በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ነው፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ቅዱስ ፓትርያርኩ የተመረጡትን አባቶችን አልሾምም አላሉም  ፤ ወደ ትግራይም በተያዘው መርሀግብር ይጓዛሉ " - ቤተክርስቲያኗ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ በአንዳንድ ማኅበራዊ  ሚዲያዎች ላይ " ቅዱስ ፓትርያርኩ በቅዱስ ሲኖዶስ የተመረጡትን መነኮሳት አልሾምም ፤ ወደ ትግራይም አልሔድም " ብለዋል  ተብሎ እየተሰራጨ ያለው ዜና ፍጹም ሐሰት ነው አለች።

ቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ፓትርያርኩ " የተመረጡትን አባቶችንም አልሾምም አላሉም። በተያዘው መርሐ ግብር  መሠረትም ወደ ትግራይ ይጓዛሉ " ስትል አሳውቃላች።

ቤተክርስቲያንኗ " እንዲህ ዓይነቱ ሆን ተብሎ የሚሰራጭ የሐሰት ዘገባ ፤ #የእርቅ ሂደቱን የማደናቀፍ እና  የቅዱስ ፓትርያርኩንስም በሐስት የማጠልሽት የተለመደና ቀጣይ የሐሰተኞችና ስም አጥፊዎች ዘመቻ አካል ነው " ያለች ሲሆን " ይህን አይነቱን የሐሰትና የፈጠራ ወሬ በቅድስት እርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ላይ የሚነዙ  አካላትም ከዚህ ደርጊታቸው እንዲታቀቡ በጥብቅ እናሳስባለን " ብላለች።

@tikvahethiopia