TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የደሴ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅ የከተማዋን ሰላም ሊያስጠብቁ እንደሚገባ የደሴ ከተማ አስተዳደር ገልጿል። ነዋሪዎች በሚነዙ ሀሰተኛ ወሬዎች፣ መረጃዎችና አሉባልታ አትደናገሩ ብሏል። ማንኛውም የተለየና አጠራጣሪ ነገር ሲመለከቱ ነዋሪዎች ለጸጥታ ኃይል በማሳወቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ተጠይቋል። ከተለያዩ አከባቢዎች ለመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ነገር…
#Update

#ደቡብ_ወሎ

በደቡብ ወሎ ከታች ቀበሌ እስከ ዞን ድረስ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ህዝቡን እንዲረጋጋ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በዞኑ ባሉ ወረዳዎች ውስጥ የሀገር መከላከያን ልብስ በመልበስ መከላከያ በመምሰል በአቋራጭ መንገዶች ሲጓዙ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

በአሉባልታ ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች ወደ ዞኑ እየገቡ መሆኑን የገለፀው የደቡብ ወሎ ዞን ከሰሜን ወሎ ዞን ጋር በመሆን መመለስ ያለባቸውን ተፈናቃዮች እና ሰሌዳ አልባ ተሽከርካሪዎችን የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

#አምባሰል_ወረዳ

በአምባሳል ወረዳ ሀሰተኛ አሉባልታ ሲነዙ እና ህብረተሰቡን በማወክ ዘረፋ ሊፈፅሙ ተዘጋጅተው የነበሩ 9 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል።

መላው ነዋሪ በሀሰተኛ ወሬና አሉባልታ ሳይደናገጥ በፍፁም መረጋጋት አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቦለታል።

#ሐይቅ

በሐይቅ ከተማ " ከዚህ ቀደም ህወሓት ቀብሮት የነበረ ከባድ እና ቀላል መሳሪያ ተገኘ " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የከተማው ፖሊስ አሳውቋል።

የህብረተሰቡን ሰላም ለማወክና አካባቢው እንዳይረጋጋ እንዲሁም ተከታይ ለማብዛት ሲሉ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

" ምንም ባላያችሁበትና ባላረጋገጣችሁበት አዲስ አበባ ቁጭ ብላችሁ በሀሰተኛ መረጃ ህዝብ የምትረብሹ ኃላፊነት የጎደላችሁ የማህበራዊ አንቂ ነን የምትሉ ግለሰቦች፣ ዩትዩበሮች ከድርጊታችሁ ታቀቡ " ያለው የሐይቅ ፖሊስ ይህን የፈፀሙት ላይ በህግ እንዲጠየቁ እየሰራው ነው ብሏል።

ነዋሪዎች በሀሰተኛ መረጃ ይስደናገጡ በተረጋጋ ሁኔታ የአካባቢውን ሰላም በንቃት እንዲጠብቁ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia