TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትግራይ #ኢሮብ

ከፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነቱ በኃላም ቢሆን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ የኢትዮጵያ፣ ትግራይ ኢሮብ ወረዳ 23 ት/ ቤቶች በኤርትራ ወታደሮች ስር ይገኛሉ።

በትግራይ ክልል ኢሮብ ወረዳ ተነፃፃሪ የሆነ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ባለባቸው አከባቢዎች ባሉ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በቀጣዩ ሃምሌ ወር 2016 ዓ.ም ለሚሰጠው አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና በመዘጋጀት ይገኛሉ።

ለፈተናው እየተዘጋጁ ያሉት ተማሪዎች በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ፤ ትግራይ ክልል በጊዜያዊ አስተዳደር ስር ያሉ ናቸው።

በወረዳው የትምህርት ፅህፈት ቤት ስር የሚታወቁ እና ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩት አንድ ሁለተኛ ደረጃ የሚገኙባቸው 23 ትምህርት ቤቶች ከ3 ዓመት በላይ #በኤርትራ_ወታደሮች_ቁጥጥር_ስር እንደሚገኙ በኢሮብ ወረዳ የትምህርት ፅህፈት ቤት ተገልጿል።

የትምህርት ቤቶቹ  መምህራን እና ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም ተብሏል። 
 
ቃላቸውን የሰጡ ተማሪዎች ፦
- ጦርነቱ ብዙ ነገሮች እንዳሳጣቸው
- አሁን በወረዳቸው ትምህርት ቤት የኢንተርኔት አቅርቦት ጨርሶ እንደሌለ
- ውሃ ፣ መብራት ፣ ትራንስፓርት የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት እንደሌለ ጠቁመዋል።

ተማሪዎቹ በቴክኖሎጂ ታግዞ ከሚፈተኑ ተማሪዎች ጋር ተፈኳኳሪ ለመሆን እንደሚከብድም ገልጸዋል።

ያም ሆኖ ግን አሁን ላይ የተገኘው ዕድል እንዳያመልጥ ለመፈተን ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

መምህራን በበኩላቸው ፥ በወረዳው ያሉት ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የክልሉና የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር እገዛ እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች ነፃ ወጥተው የዘወትር አገልግሎት እንዲሰጡ ትኩረት ማድረግ አለበት ብለዋል።

በወረዳው በጦርነት ምክንያት የትምህርት ሴክተር ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የወደመ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችም ምንም የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት በሌለበት ለመፈተን በዝግጅት ላይ መሆናቸው ግምት ውስጥ በማስገባት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የእገዛ እጃቸው እንዲዘረጉ የወረዳው የትምህርት ፅህፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል።

ይህንን መረጃ የትግራይ ቴሌቪዥንን ዋቢ በማደረግ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia