TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ታግዶ የቆየው የነዋሪነት መታወቂያ #የጠፋባቸው ነዋሪዎች ምትክ አገልግሎት ከፊታችን ሰኞ ይጀምራል።

የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አገልግሎቱ ከሰኞ ታህሳስ 24 ጀምሮ ለመጀመር ዝግጅት እንዳጠናቀቀ አረጋግጧል።

ኤጀንሲው ፤ በቀድሞ አሰራር ፖሊስ ግለሰቦች በነዋሪነት የተመዝገቡ ነዋሪ መሆናቸው በተቋሙ ሳይረጋገጥ የጠፋ ሰነዶችን ማስረጃ ሲሰጥበት የነበረበት አሰራር ግለሰቦች በሃሰተኛ የእምነት ቃል የነዋሪነት መታወቂያ ሳይኖራቸው ማስረጃውን በማውጣት በተለያዩ ቦታዎች ማስረጃውን እየጠተቀሙ እያጭበረበሩ መሆኑን የፖሊስ ምርመራ በተለያዩ ግዝያት ማረጋገጡን ገልጿል።

አሁን ካለው  ጥብቅ የነዋሪነት መታወቂያ  አሰጣጥ ቁጥጥር ስርዓት አንፃር ማንኛውም የጠፋበት ምትክ ጠያቂ  ነዋሪዎች ቀድሞ ነዋሪ መሆናቸውን ከሚኖሩበት የወረዳ ጽ/ቤቶች ማረጋገጫ ለፖሊስ ሲያቀረቡና ከፖሊስ የጠፋ ሰነድ #ማስረጃ_ሲሰጣቸው _ብቻ አገልግሎቱን እንደሚያገኙ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ኤጀንሲው ፤ የጤና እክል ያለባቸው እንዲሁም ለአቅመ ደካሞች ልዩ ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

@tikvahethiopia